በእስራኤል በስህተትና በግፍ በተገደለው ኤርትራዊ ወጣት ሳቢያ ታላቅ ቁጣ ቀሰቀሰ ፣የኤርትራ መንግስት ግድያውን አውግዟል

Israel_palestinian_clashes_01

በታምሩ ገዳ

ከዛሬ አራት አመት በፊት ከትውልድ አገሩ ኤርትራ ባሕር እና የብስ አቋርጦ ወደ “ተሰፋይቱ ምድር” እስራኤል ለተሻለ ኑሮ ሲል የተሰደደው የ29 አመቱ ሃብቶም ዘረሁን በቀጣሪዎቹ ዘንድ “ተግባቢ ፣ ለመሻሻል የሚጥር እና በጣም ተወዳጅ ወጣት ነበር ።” እንደ አሱሶትድ ፕሬስ ዘገባ ሃብቶም የሰራ ቪዛውን ካሳደሰ በሁዋላ እስራኤል ውስጥ ያጠራቀማው ገንዘቡን ይዞ በኤርትራ የሚገኙ ቤተሰቦቹን በቅርቡ ለመጠየቅ እቅድ ነበርው ።

ይሁንና ሰው ያስባል አግዚአብሔር ይፈጽማል እንዲሉ ባለፈው እሁድ ጥቅምት 18 2015 እኤእ አመሻሹ ላይ እስራኤል (ቤርሳባ ውስጥ) አንደ ፈለሰጤማዊ እስራኤል በአንድ አውቶቡስ ማቆሚያ አካባቢ አንድ የእስራኤል ወታደር መሳሪያውን ነጥቆ እና ተኩሶ ገደሎ ፣ 10 አቁሰሎ እራሱ (ገዳዩም) በጸጥታ ሃይሎች የተገደለበት ገጠምኝን /ግጭትን በአቅራቢያ የታዘበው ወጣቱ ሃብቶም ከግርግሩ ለማምለጥ ሲጣጣር የተመለከተው አንድ የእስራኤል የጥበቃ ሰራተኛ ሃብቶምን “ከአሸባሪዎች አንዱ ይሆናል “በማለት በጥይት ተኩሶ የዘርረዋል።ከደረሰበት ጉዳት ሳቢያ ሰውነቱ በደም የታጠበው ሃብቶም አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ሊሰጠው ሲገባ (በትንሹ አንድ ፖሊስን ጨምሮ) በሰፍራው የነበሩ የተወሰኑ ሰዎች የጥላቻ ቃላት በመጠቀም ፣ በመተፋት እና ከአካባቢው የነበሩ ቁሳቁስ(ወንበር ሳይቀር) በማነስት የደበድቡታል። በጸታ ሃይሎች እና በሰላም ወዳዶች ጣልቃገብነት ከሰፈራው የተወሰድው ምስኪኑ ሃብቶም ሃኪም ቤት እንደደረሰም ብዙ ሳይቆይ እሰከ ወዲያኛው አሸልቧል።

ያ እሩቅ እላሚው እና የ 29 አመቱ ሃብቶም በድንገት መሞት የአስራኢል፣የኤርትራ እና የፍልስጤም ፖልቲከኞችን አናቁሯል ። የሰብእዊ መብት ተሟጋቾችንም በእጅጉ ኣሳዝኗል። የእስራኤል ጠ/ሚ/ር ቢኒያም ናቲናያሁ በደረሰው ደንገተኛ አደጋ የተሰማቸውን ሃዘን ለሟች ቤተሰቦች በላኩት መልክት የገለጹ ሲሆን “አገራችን እስራኤል በሕግ የበላይነት ታምናለች።” ያሉት ጠ/ሚ/ሩ ድርጊቱንም የፈጸሙ ወገኖች በአስቸኳይ ለፍርድ እንደሚቀርቡ ቃል ገብተዋል። የወንጀለኞቹ ማንንነትን ለማጣራት የቪዲዮ ምስል ምርመራ በመካሄድ ላይ ሲሆን እስከ እሁን ድረስ ግን አንድም ተጠረጣሪ አልተያዘም ተብሏል።

የፈልስጤም ራስ ገዝ ከፍተኛ ባለሰልጣን የሆኑት ሃና አሽራዊ “የእስራኤል ባለሰልጣናት ሕዝቡን ጥላቻ እና ወንጀል እየመገቡት ለእንደዚህ አይነቱ ድርጊት ደረሰዋል” በማለት ሃላፊነቱ የባለሰልጣናቱ መሆኑን ተናግረዋል።የኤርትራ ማሰታወቂያ ሚ/ር በበኩሉ ሰኞ ጥቅምት 19 /2015 አኤአ ባወጣው መግለጫው “ ይሂ ጭካኔ እና ዘግናኝነት የተሞላበት የግደያ ድርጊት በእስራኤል በሚገኙ 10ሺዎች ሰላማዊ ዜጎች ላይ ከህዝብ እይታ ውጪ እለት ተእለት የሚፈጸምባቸው እርምጃ አንዱ አካል ነው።ኤርትራዊያን ዜጎች ካለፉት ጥቂት አመታት ወዲህ በሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎች እየተወናበዱ ለፖሊቲካ ፍጆታ እና ለእስራኤል ርካሽ የጉልበት ሰራተኛነት ተዳርገዋል።” በማለት የተላቪቭ መንግስትን ኮንኗል።

የመብት ተሟጋቹ ሁማን ራይት ዎች አንዲሁ “ ሃብቶም ጥገኝነት ፈለጋ ወደ እስራኢል ተሰዶ በእስራኢል ደህነቶች እና በጋጠወጦች መገደሉ ተቀባይነት የለውም ።” ሲል ተቃውሞውን አሰምቷል ። አሚንስቲ ኢንተርናሽናልም “ሃብቶም የሞተው ቆዳው በመጥቆሩ ብቻ ነው፣ገዳዮቹም ባስቸኳይ ለፍርድ ይቅረቡ ።” ብሏል ።

በዛሬይቱ እስራኤል ወስጥ ከ 34ሺህ በላይ ኤርትራዊያን እንደሚኖሩ ዘገባዎች ይገልጻሉ ። በሰሞኑ የእስራኤሎች እና የፈልስጤሞች ግጭት ከ 44 በላይ ፈልስጤሞች ሲገደሉ ከ 9 በላይ እስራኤሎችም ሕይወታቸውን አጥተዋል። ሁኔታው ያሰጋቸው የተመድ ዋና ጸሃፊ ባን ኪ ሙንም ውጥረቱን ለመዳኘት ወደ ሰፍራው ለማቅናት ተዘጋጅተዋል። የተቃዋሚው አኦፈር ሻለህ ሊቀመንበር የሆኑት ያሽ አቲድ”ተጠርጣሪ ግልሰብ በጸጥታ ሃይል ተመቶ ከቆሰለ በሁዋላ አደገኛነቱ አናስተኛ መሆኑ እየታወቀ አንድን ግለሰብ(ሃብቶምን) ከወደቀበት እያቃሳተ ሳለ ለሞት እስኪያበቃው ድረስ በቡድን መደብደብ ፍጹም ተቀባይነት የለውም ፣ይህንንም ህግ ማንኛውም የእስራኤል ወታደር ጠንቅቆ ያውቀዋል።”ብለዋል።

መርቲዝ የተባለው ፓርቲ ዋና ጸሃፊት የሆኑት ዚሃቫ ጋለን “የመከላከያ ሚ/ሩ በቅርቡ ሲቪሎች ሁሉ የጦር መሳሪያ ይታጠቁ ማለታቸውእና የትምህርት ሚ/ሩ ደግሞ (እንደ ካው ቦይ) ሸጉጥ ታጥቀው ፎቶ መነሳታቸው ምን ያህል ከእውነታው እርቀን በ እብደት አለም ውስጥ እንዳለን ያመላክታል።”በማለት የወቅቱ ፖለቲከኞችን በጽኑ ኮንነዋል።የጺዮናዊነት ሕብርት የተሰኘው ቡድን የሚወክሉት ማክ ናችማን ሻይ በበኩላቸው “ይህ እረዳት የሌለው ፍጡር (ሃብቶም) ከመሬት ላይ ተንጋሎ ሳለ ደብደቦ መግደል ሰበዊነት አይደለም ፣የ አይሁዳዊያን ባሕሪም አይደለም ።” በማለት የአገሪቱ ዋናው አቃቢ ህጉ በግድያው ዙርያ ልዩ ማጣራት አንዲያካሁዱ በደብዳቤ ጠይቀዋል።እለታዊው የእስራኤል ጋዜጣ ዮዲት “ሃብቶም የተገደለው ያለ አንዳች ጥርጥር በቆዳው ቀለም ልዩነት ሳቢያ ነው። “ሲል አስነብቧል። ደርጊቱን ፈጽመዋል ተብለው ከተጠረጠሩት መካከል አንዱ እንደሆነ አና “ዱዱ”በሚል ሰም አንዲጠራ የጠየቅው ግለሰብ ለእስራኤል ጦር ሃይል ራዲዮ በሰጠው እማኘነት “ግለሰቡ(ሃብቶም) አሸባሪ አለመሆኑን ባውቅ ኖሮ ጫፉን አልነካውም ነበር። አሁን ግን በእጃችን ህይወቱ ያለፈው ግለሰብ(ሃብቶም) ነጹህ ሰው መሆኑን ከተረዳሁ በሁዋላ እንቅልፍ መተኛት ተሰኖኛል” በማለት መጸጸቱን ተናግሯል።

ሃብቶምን ከወርበሎች ለመታደግ ጥረት አድርጎ እንደነበር የሚናገርው መርሰኮ የተባለ መንገደኛ በበኩሉ ለቻናል 10 ቴሊቪዥን በሰጠው አስተያየት “ቁም ነገሩ ግለሰቡ (ሃብቶም) አሸባሪ ይሁን አይሁን አይደለም ግለሰቡ መንቀሳቀስ አቅቶት ተኝቶ እየተዪ በሰሜታዊነት ተደብድቦ መሞቱን በአይኔ በመመልከቴ ውስጤ ተጎድቷል ፣እንቅልፍም እርቆኛል።” በማለት በሁኔታው የሰነልቦና መታወክ እንደገጠምው ገልጿል። የሟች ሃብቶም አለቃ የሆኑት ሳጂ ማላቺ እንዲሁ በበኩላቸው ሃብቶም ወደ ደቡባዊ እስራኤል (ቤርሳባህ )የተጓዘው የሰራ ፈቃዱን ለማስደስ አንደ ነብር አወስተው “ ”ጭምት እና ሃላፊነቱን ዘወትር ለመወጣት የሚጥር ታታሪ ሰራተኛ ነበር። ሃብቶም በማያወቀው ሰፍራ እና ባለጠበቀው ሰአት ሀይወቱ እንደቀላል ነገር በማለፉ ልቤን ክፉኛ ነክቶታል ።”ሩቅ አልሞ በ ጽጥታ ሃሎች ተተኩሶበት እና በወርበላዎች ተደብደቦ በአጭሩ ለቀረው ሰራተኛቸው እና ወዳጃቸው ለነበረው ሃብቶም ያላቸውን ፍቅር እና ሃዘናቸውን ገልጸዋል። ፈጣሪ ነፍሱን ይማረው !!!!።

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *