Hiber Radio: የአማራ ወጣቶች ንቅናቄ የብአዴንን መግለጫ የገዳይ ወኪል በሆነው አመራር የወጣ ነው ሲል አወገዘ

የአማራ ወጣቶች ንቅናቄ በወልዲያና አካባቢው ሰሜን ወሎ በሕወሓት የአጋዚ ወታደሮች በንጹሃን ላይ የተደረገውን ጭፍጨፋ አስመልክቶ የሕወሓት ተላላኪ የሆነው ከፍተናው የብአዴን አመራር ነብሰ ገዳኦችን ትቶ መብቱ በተረገጠው ሕዝብ ላይ አነጣጥሮ ያወጣው መግለቻ በአባላቱ ጭምር ተቀባይነት ያላገኘ መሆኑን ገልጾ የብአዴንን መግለጫ አወግዞ የትግል ጥሪ ማስተላለፉን ለህብር/ዘሐበሳ በላከው መግለቻ ገለጸ።

በቅርቡ የተቋቋመው የአማራ ወጣቶች ንቅናቄ የብአዴንን መግለጫ አውግዞ ያወጣውን አስከትለን እናቀርባለን።

ከአማራ ወጣቶች ንቅናቄ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ

                        የሃሰት መግለጫ እውነትን ሊሽር ከቶም አይችልም!

አማራ ራሱን መስዋዕት በማድረግ ሃገሩንና   ከጠላት በመከላከከል ያቆየ የታላቅ ታሪክ ባለቤት ነው።
አማራው ከሁሉም የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ጋር በአጥንትና ደም ተዋህዶ በፍቅር በሰላምና በአብሮነት የኖረ  ደግ
ማህበረሰብ መሆኑም ይታወቃል:: ኢትዮጵያ በወያኔ ባርነት ስር ከወደቀች ጊዜ ወዲህ በሃገራችን ውስጥ በስፋት
በተዘረጋው የጎሳ ፖለቲካ የጥላቻ ማዕከል ተደርጎ እጅግ የበዛ የተናጥል ጥቃትን ሲያስተናግድ ቆይቷል:: አማራው
በማንነቱ እየተጠቃ ለችግር ቢጋለጥም በብሔሩ ተደራጅቶ የጥላቻ ጦርነት በከፈቱበት አናሳ የትግራይ ወያኔዎች
አድራጎትን በመናቅ ለሃገራዊ አንድነቱና ለማህበራዊ አብሮነቱ በጽናት መቆምን መርጦ ቆይቷል::
ጥላቻ ያሰከራቸውና የበታችነት ስነልቦና ያሳበዳቸው የትግራይ ወያኔዎች የዘመናት አብሮነታቸውን በግዜያዊ
ስልጣንና ጥቅም ለውጠው በትብብር ሰላሙን ሲያውኩትና ሃብቱን ሲበዘብዙት ቆይተዋል::ትዕግስቱን በፍርሃት
የመነዘሩት ወያኔ ትግሬዎች መስመር አልፈው በክልሉ መብቱን ለመጋፋት ያደረጉትን ሙከራ ሲቃወምና ሲመክት
ቆይቷል::በዚህም ሰሞኑን በወልድያ ቂም አርግዘው ለበቀል በመሰማራት የንጹሃን ወገኖቻችንን ሕይወት በሰውበላ
የአግአዚ  ታጣቂዎች ጨፍጭፈዋል:: ከወልድያም ባሻገር በአጠቃላይ የሰሜን ወሎ አጎራባች ወረዳዎች በሚኖረው
ሕዝብም ላይ ተመሳሳይ ፋሽስታዊ እርምጃቸውን አካሂደዋል::
በወልድያ የተፈጠረው ችግር መነሻና መድረሻው ሕወሀትና ጀለሌዎቹ ቢሆኑም ፥የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ
ንቅናቄ (ብአዴን) ባወጣው ድርጅታዊ መግለጫ የአማራውን ሕዝብ ተጠያቂ አድርጏል፥፥ የአማራ ወጣቶች ንቅናቄ ባለው
ጠንካራ ድርጅታዊ አወቃቀር በብአዴን ውስጥ ካሉት ዉስጥ አዋቂወች ባገኘነው መረጃ መሰረት ይህን የአማራውን
ህዝብ የሚዘልፍ መግለጫ አባላቱ የማያውቁትና የማያምኑበት ጥቂት በበላይ መዋቅሩ ውስጥ በተሰገሰጉ ተንበርካኪ
ቅጥረኛ የህወሃት ሎሌዎች ሆን ተብሎ መላውን የድርጅቱን አባላት በህዝብ ለማስጠላት ታቅዶ የተደረገ መሆኑን
ኣሳውቀውናል።
ስለሆነም ከዚህ በኋላ በበርካታ ሚሊዮን የሚገመትውን የብአዴን ኣባላት አሳልፈን ለትግራይ ወያኔ
ባርነት የምንሰጥበት ጊዜ ባለመሆኑ ያቀረቡትን ቅሬታ በሚገባ ገምግመን ድርጅታቸውን የማይወክል መሆኑን
አምነንበታል። ስለዚህ የአማራ ወጣቶች ንቅናቄ ከብአዴን ወጣት አመራር ኣባላት ጋር በኣማራው ህልውና ላይ
ጠንክረን ለመስራት ብርቱ ትግል ለማድረግ ቆርጠን መነሳታችንን ለአማራው ህዝባችንና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ
ለማሳወቅ እንወዳለን።
እውነተኛ አማራ አይደለም ተነጋግሮ ተያይቶ መግባባት አለበት!
አያቶቹ በገነቧት ሃገሩ ኢትዮጵያ ላይ አማራው በክብር ይኖራል!
የአማራ ወጣቶች ንቅናቄ

ከአማራ ወጣቶች ንቅናቄ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው ጋር ስለ ንቅናቄው በቅርቡ አድርገነው የነበረው ቃለ መጠይቅ እነሆ፦

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *