ሸንቁጥ አየለ
ካንዱ ክልል ሀገርህ አይደለም ብሎ ያባርርሃል::ግራ ሲገባህ መጠለያ ካምፕ ብለህ ትጠለላለህ::የሚደርስልህ እና የሚጠይቅህ ታጣለህ::እናም ሰሚ ካለ ብለህ ምናልባት በስልጣን ላይ ያሉ አካላት ሰበአዊነት ተሰምቷቸዉ ጉዳዬን ቢከታተሉልኝ ብለህ ጥያቄ ለማቅረብ ሰብሰብ ትላለህ::ያኔ ያለ እርህራሄ በመሳሪያ ይደበድቡሃል::ልክ አንዳች የሌላ ሀገር ወራሪ ጦር የመጣ ይመስል በጭካኔ እያሳደዱ ይገሉሃል::
አሁን በሀማሬሳ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ የሆነዉ ይሄ ነዉ::በሚሊዮን የሚቆጠር ኢትዮጵያዊ ሶማሌ ክልል ሀገርህ አይደለም ተብሎ እንዲፈናቀል ተደርጓል::የተፈናቀለዉ ህዝብ ኢትዮጵያዊ እንዳልሆነ እና ሰዉ እንዳልሆነ የተፈናቀለዉም በጎሳ ግጭት እንደሆነ የአለም ህዝብ እና ቀሪዉ ኢትዮጵያዊ እንዲያምንበት ሲባል የተፈናቀለዉ የዚህ ጎሳ ነዉ::
ያፈናቀለዉ ደግሞ የዚያ ጎሳ ነዉ::የተባረረዉ ከእከሌ ጎሳ ሀገር ነዉ ተብሎ ይሰበካል::ሶማሌ ክልል ለኦሮሞ ሀገሩ እንዳልሆነ::ሶማሌ ክልል ለኢትዮጵያዉያን ሀገራቸዉ እንዳልሆነ::ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ እንዳልሆነ:: ወያኔ ጉዳዩን የኦሮሞ እና የሶማሌ ግጭት ነዉ ብሎ ከመሃል እራሱን አስፈንትሮ በማዉጣት እጁን በዉሃ ታጥቦ ቁጭ ይላል::የሚጠይቅ ጥቂት ነዉ::ወያኔዎቹም ሁሌም ፈገግ ብለዉ አዲስ የተንኮል ደባቸዉን ይቀጥላሉ::
ሰብዓዊነት እንደ ምንም ይረገጣል::ታላቁ ኢትዮጵያዊነት እንደ ምናምንቴ ርጋጭነት ተጥሏል::ሰዉ ሲያልቅ በጎሳዉ ኢንዲጠራ ከጎሳዉም ባነሰ የተጋጩት የዚህ አካባቢ ጎሳዎች በዉሃ እና በሳር ተጣልተዉ ነዉ እየተባለ ይቀለዳል::ቆየት ተብሎም ይባላል::ሶማሌዉ ኦሮሞዉን ያሳደደዉ ከሀገሩ ነዉ:: ስለዚህ የኦሮሞዉ ከሶማሌ ክልል መባረሩ አግባብ ነዉ ብሎ ወያኔ ገደምዳሜ መግለጫ ይሰጥበታል:: እናም ኢትዮጵያዊነት እና ሰዉነት ከታላቁ ማማ ላይ ወርደዉ ይፈጠፈጣሉ::
አሁን በበሀማሬሳ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ብዙዎች እንደ ተራ ነገር በጅምላ የጥይት ጭፍጨፋ ተጨፍጭፈዋል::የኢትዮጵያ ህዝብ አሁን ዝም ብሎ ያያል::ኦሮሞ ነን የሚሉ ፖለቲከኞች ብቻ ይጮሃሉ::ሌላዉ እንደ ማያገባዉ እና ኢትዮጵያዊ እንዳልተጎዳ ዝምታን ይመርጣል:: አማራዉ በሚሊዮን ሲያልቅ የኦሮሞ ፖለቲከኞች አንዳች ሰማያዊ መና ከሰማይ የወረደላቸዉ ይመስል ፊታቸዉ ላይ ፈገግታ እየፈነጠቀ ጭጭ ይላሉ::እረ ኢትዮጵያዊነት ተደፈረ: እረ ሰበአዊነት ተዋረደ የሚል የለም:: እንግዲህ ሁሉም ለየራሱ ሊጮህ ወስኗል እና ሰበአዊነት እና ኢትዮጵያዊነት ከምንም በታች ሆነዋል::
ጉራጌዉ በመላ ሀገሪቱ ተንቀሳቅሶ የመነገድ እጣ ፋንታዉ እንዲሸማቀቅ ተደርጓል::በእኛ ሀገር መጥቶ ሀብት አፈራብን ይባላል::መሃል ሸዋ ላይ ደብረዘይት ላይ ያፈራዉ ሱቅ በዘረኝነት አይን እየተለካ ጉራጌ ዘረፈን እየተባለ ጉርምምርምታዉ ብዙ ነዉ:: ቅማንቱ እና አማራዉ ጎንደር ላይ አብሮ እንዳይኖር የቤት ስራዉ በሚገባ ተሸርቧል::
አኘዋኩ ከወንድሞች ከነዌሮች ጋር አብሮ እንዳይኖር አስተምማማኝ የቤት ስራዉ ተሰርቷል::አማራ ከብዙ ብሄሮች ጋር እንዲቆራረጥ አስፈላጊዉ ቅድመ ስራ ሁሉ ተሰርቷል::የጊዜ ጉዳይ ነዉ እንጂ ኦሮሞዉ እና ሲዳማዉ ተፋጠዉ ይገኛሉ::ወላይታዉ ከሲዳማዉ ; ሲዳማዉ ከጌዴዎዉ እንዲሁ በአይነ ቁራኛ ይተያያሉ::ደቡብ ክልል ምክር ቤት ዉስጥ የሚሰበሰቡት የተለያዩ ዞኖች በታላቅ ጥርጣሬ እና ጥላቻ ይተያያሉ::ምክንያቱም እያንዳንዱ ዞን የሚወክለዉ የተለያዩ ጎሳዎችን ነዉ እና:: አንዱ ጎሳ ሌላዉን አያምንም::ይሄን ሀቅ ደቡብ ክልልን በደንብ ተዘዋዉሮ ያዬ ወይም በደቡብ ክልል የኖረ ኢትዮጵያዊ ብቻ ያዉቀዋል::
አሁን ኢትዮጵያ የምትባል ታላቅ እና ብዙ የተደከመባት ሀገር አይደለችም ያለችዉ::አሁን ያሉት የጎሳዎች ስብስብ ናቸዉ::ኢትዮጵጵያዊ አይደለንም ብለዉ የተነሱት የትግራይ ወንበዴ ወያኔዎች አሁንም ኢትዮጵያን የሚመሯት በትግራይነታቸዉ እንጅ በኢትዮጵያዊነታቸዉ አይደለም::ፖለቲከኛ እና ምሁር ነን የሚሉ ኢትዮጵያዊያንም በሚያሳዝን ሁኔታ የትግሬ ወንበዴ ወያኔዎችን ስብከት ተቀብለዉ ከታላቁ የኢትዮጵያዊነት ማማ ላይ እንዘጭ ብለዉ እየጎሳቸዉ መደብ ላይ ቂጥጥ ማለትን መርጠዋል::
ሀገር ሀላፊነት ይጠይቃል::ሀገር በሃላፊነት ይሰራል::ሀገር የደከሙባትን ማክበርን ይጠይቃል:: የተደናበሩት ምሁር ነን ባይ የየጎሳዉ ፖለቲከኞች ግን ትከሻቸዉን እየሰበቁ አጸ እንትና ከዚህ ብሄር ስለሆነ እነሱ የሰሩት ሀገር አይጥመንም እያሉ በድንቁርና ከወያኔ ጋር በወያኔ ሀሳብ እየተስማሙ ነዉ::ሀገር መስራት ጀግንነት እና መስዋ ዕትነት መክፈልን ይጠይቃል:: የአለም ህዝብ ሁሉ ታሪክ የሚነግረን ይሄንኑ ነዉ::የተሰራን ሀገር ማክበር እና ያን ሀገር ወደ በለጸገ ዲሞክራሲያዊነት መዉሰድ ሲገባ የተሰራዉን ካልናድን ባይ ጎሰኛ በኢትዮጵያ ምድር እንደ ቅንቅን ተፈልፍሏል::እንደ እፉኝት ባህሪ የተላበሱ ናቸዉ እና የቀደመ እናት እና አባታቸዉን ታሪክ አፍርሰዉ ካልሆነ ታሪክ የሰሩ አይመስላቸዉም::
ሀገር ከሰፈር እና ከቀበሌ ብሎም ከክልል ይበልጣል::ይሄ ተራ ቀመር ነዉ::ግን ወያኔ ይሄን አልሰበከም እና የሰበከዉ ሁሉ እዉን ሆኖለታል:: ትግራይ ከኢትዮጵያ እንድትበልትለት የተንጠራራዉ ወያኔ ይሄን ሀሳቡን እዉን ለማድረግ የየጎሳዉ ፖለቲከኞች በዚሁ በወያኔ ቀመር እንዲታነቁ እና እንዲተላለቁ በደንብ ሰርቷል::
ዛሬ በበሀማሬሳ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ጩኸት በርክቷል::ጩህቱ የኢትዮጵያዉያን ሁሉ ጩህት ነዉ::ግን ኢትዮጵያዉያን አይሰሙም::የኦሮሞ ጩህት ብቻ ይመስል ሁሉም በአርምሞ ዉስጥ ነዉ::በየጎሳዉ የበደል እየዬ ዉስጥ ነዉ::
ወያኔ በዚህ ሁሉ መሃል አስካሪ አልኮሉን እየጠጣ ይደንሳል::ይጨፍራል::የወያኔ የፖለቲካ ህሳቤ ቀላል የሚባል አይደለም:: የጎሳ ፖለቲካ እጅግ ጉልበት ያለዉ ታሳቢ ያነገበ ነዉ::በመጠፋፋት: በመበዳደል: በመበቃቀል እና ባለመተማመን ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ቀላል ጉልበት የለዉም:: ወያኔ የተለያዩ ጎሳዎች በጋራ የጋራ ሀገር እንዳይኖራቸዉ: ወይም ስለጋራ አንድነታቸዉ እንዳያስቡ በደንብ በረጋግዶ የልዩነት ወንዝ ቆፍሮ ታላላቅ ዥረት አድርጎታል::
ያም ሆኖ ግን ከዛሬ ይልቅ የነገዉ የኢትዮጵያዉያን ትርምስ እና ትርምስምስ እጅግ አሳሳቢ ነዉ::በየጎሳቸዉ መደብ ላይ ወያኔ ያስቀመጣቸዉ ሀይላት ግን ይሄ አይታያቸዉም::ሁሉም ልባቸዉ በበቀል አርግዟል እና አቀርቅረዉ መሬት በቁጭት እየጫሩ ነዉ::ከሚሰሙት እሪታ ይልቅ ነገ በሌሎች ጎሳዎች ላይ የሚፈጽሙት በቀል ልባቸዉ ዉስጥ በደንብ ሲጮህ ይሰማቸዋል እና አሁን ጆሯቸዉ የማያደምጥ ነዉ::ልባቸዉም የማያስተዉል::ወያኔም በዚህ ጉዳይ ታላቁ አትራፊ ሆኖ ጭፈራዉን ቀጥሏል::
ማንህ ጀግና ይሄን ወንዝ የምትሻገር? ማነህ ዠግና ይሄን ሁሉ የወያኔ የጥላቻ እና የልዩነት ወንዝ ወደ አንድ የሀገር ምንጭ የምትለዉጥ? እንዴት ካልክ መልሱ ግልጽ ነዉ:: ይሄ የሚሆን በጦር ነዉ::ይሄ የሚሆን በዉጊያ ነዉ::ለመሆኑስ ማንህ ዥግና ይሄን ሁሉ በየጎሳዉ መደብ ላይ የተቀመጠ የፖለቲካ ጎናዴ ሁሉ በክንድህ የምትሰበስብ?
ማን ነህ ዠግና የኢትዮጵያን ህዝብ ወደ ክብር ማማ ላይ የምትስብ? ማነህ ዠግና የኢትዮጵያ ህዝብን የኢትዮጵያዊነት ሀላፊነቱን ካልተወጣ ገና ወደ ጥልቅ አዘቅት ዉስጥ ተያይዞ እንደሚሰጥም የምታስረዳ እና የምታሳምን ብሎም ከጎንህ የምታሳልፍ? ማን ነህ ዠግና እንደ ታላቁ ንጉሰ ነገስት እንደ አጼ ቴዎድሮ “የኢትዮጵያ ባል እኔ ነኝ” ብለህ ተነስተህ የልዩነት ዛፍን ሁሉ ሰባብረህ በአንድ የምትሰበስብ? ማነህ ዠግና በኢትዮጵያ ላይ ያንዣበበዉን የሞት ዳመና በብሩህ ተስፋማ ብርሃን የትተካ?
ኦ ኦ ……ጥያቄዬን ለዛሬ ላቁመዉ::በሀማሬሳ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ የተሰማዉን ጩህት ሁሉ ግን ኢትዮጵያዉያን ሁሉ በጋራ ጩሁት::ቢያንስ የሚያስተባብራችሁ እና አብራችሁ እንድትጮሁ የሚያደርጋችሁ ብታጡም በልባችሁ ጩሁ::ይሄ ጩህት በመላ ሀገሪቱ ነዉ::በመላዉ አማራ አካባቢ:በመላዉ ኦሮሞ አካባቢ: በሶማሌ አካባቢዎች: በአፋር: በጋምቤላ: በደቡብ: በያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ጓዳ ሁሉ ነዉ::
በመሃል ኢትዮጵያ: በሰሜን ኢትዮጵያ: በደቡብ ኢትዮጵያ: በምዕራብ ኢትዮጵያ: በምስራቅ ኢትዮጵያ ሁሉ ነዉ:: ይሄ ጩህት በየአካባቢዉ ሲሰማ ምናልባት የሰዓታት ወይም የወራት ልዩነት ሊኖር ይችል ይሆናል እንጅ ይሄ ጩህት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ነዉ::እናም ይሄ ጩህት ሁሉም ቦታ አለ::
እንግዲህ የምናምን ሰዎች ወደ እግዚአብሄር እንጩህ::የማታምኑም ወደምታምኑበት ጩሁ::ከቻላችሁም ህዝባችሁን ለማዳን በመልካሙ መንገድ ተሰባሰቡ:: ወያኔን ለመጣል እና በኢትዮጵያ ያለዉን ግፍ ለመፈወስ ያለዉ ብቸኛ አማራጭ ከወያኔ የተሻለ ሀሳብ ታጥቆ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ለመፈወስ መነሳት መፍትሄ ነው::ይሄ ለሚያሳምናችሁ ብቻ ማለቴ ነዉ::