Hiber Radio: ለኔቫዳ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሚወዳደረው ትውልደ ኢትዮጵያዊው አሌክሳንደር አሰፋ የምርጫ ቅስቀሳውን ጀመረ ፣ለደጋፊዎቹ ጥሪ አድርጓል

 

አሌክሳንደር አሰፋ

(ህብር ሬዲዮ)በዘንድሮ ምርጫ ለኔቫዳ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ የዲማክራቲክ ፓርቲ ዕጩ ሆኖ የሚወዳደረው ትውልደ ኢትዮጵያዊው አሌክሳንደር አሰፋ ይፋ ለምርጫ መቅረቡን አሳውቆ የምረጡኝ ቅሰቀሳውን የጀመረ ሲሆን ለመራጩ ሕዝብ ድምጹን እንዲሰጠው፣የምርጫ ዘመቻው የተሳካ እንዲሆን የተቻለውን ድጋፍ ሁሉም እንዲያደርግለት ጥሪ አስተላለፈ።

በኔቫዳ በክላርክ ካውንቲ የ42ተኛውን ዲስትሪክት ወይም አውራጃ በመወከል የዲሞካራቲክ ዕጩ ሆኖ የቀረበው አሌክሳንደር አሰፋ ባለፈው ዓመት በዲሞክራቲክ ፓርቲ ስር የተቋቋመው የትራንስፖርትና የቱሪዝም ሰራተኞች  ቡድን ሊቀመንበር ሲሆን ላለፉት ወራት በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር ሕዝቡ ምርቻን ጥቅም አውቆ በመብቱ እንዲተቀምና እንዲመዘገብ አስቀድሞ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ መቆቱን መዘገባችን ይታወሳል።

አሌክሳንደር አሰፋ በዘንድሮ ምርጫ ለመራጮቹ አጠር ያለ የመጀመሪያ ይፋ ተወዳዳሪነቱን ማሳወቂያና  የምርጫ ቅስቃሳ መልዕክቱን በቪዲዮ ያቀረበ ሲሆን ሰራተኞች የልፋታቸውን ዋጋ  የሆነውን ተገቢውን ክፍያ እንዲያገኙ ፣ጥራት ያለው ትምህርት ያለ አድልዎ ለሁሉም እንዲደርስና በሌሎችም ጉዳዮች ምን ለማድረግ እንዳሰበ በዚህ መልክቱ ይፋ አድርጓል። ደጋፊዎቹ የቻሉትን ድጋፍ እንዲአደርጉ የጎ ፈንድ ሚ አካውንት የከፈተ ሲሆን ከመልክቱ አስከትሎ ያለውን ሊንክ በመጫን የበኩልዎን መርዳት እንዲችሉ ይፋ አድርጓል። የመልዕክቱን ሙሉ ቃል ያድምጡት

የጎ ፈንድ ሚ ሊንኩ እነሆ https://www.gofundme.com/58j44lk

በኔቫዳ በክላርክ ካውንቲ የ42ተኛውን ዲስትሪክት ወይም አውራጃ በመወከል የዲሞካራቲክ ዕጩ ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ ለምርጫ የቀረበው አሌክሳንደር አሰፋ ዌብ ሳይት ለተጨማሪ መረጃ እነሆ፦ http://www.assefa4thepeople.com/

ህብር ሬዲዮ ከዚህ ቀደም ከአሌክሳንደር አሰፋ ጋር አስቀድሞ ቃለ መጠይቅ ማድረጉ ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *