በጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለ
ዛሬ የካቲት 30 የልደታ ፍርድ ቤት የዋልድባ መነከሳት ባቀረቡት “የሰብዓዊ ጥሰት በማረሚያ ቤቱ ተፈፅሞብናል ፍርድ ቤቱ ተትዕዛዝ ይስጥልን!” ብለው ያቀረቡትን አቤቱታ ሰምቶ የማረሚያ ቤቱን ምላሽ ለመስማት ሲኾን ማረሚያ ቤቱም ምላሽ የሚለውን በደብዳቤ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡ ፍርድ ቤቱ ማረሚያ ቤቱ የሰጠውን ምላሽ እንደተመለከተው እና ውሳኔ እንደሚሰጥ አሳውቋል፡፡ አባ ገ/ኢየሱስ ኪዳነ ማርያም “የተከሰስነውም የታሰርነው አንድ ላይ ቢኾነም እኔን ያለምንም ምክንያት ወደ ዞን አምስት በተለምዶ ጨለማ ወይም ቅጣት ቤት ወደሚባለው አዘዋውረውኛል፡፡ ተቀጥቼ ከኾነ ጥፋቴ ተነግሮኝ፤ ቅጣቴ ምን ያህል ቀን እንደኾነ አውቄ ቅጣቴን ልቀበል፤ ያለምንም ጥፋት ዝም ብዬ ነው፡፡ እየተሰቃየኹ ያለኹት ብዙ በደል ደርሶብናል፡፡ ከአመት በላይ ልብስ ሳንቀይር ቆይተን በቅርብ ቀን አንድ ምዕመን ልብስ አምጥቶልኝ እኔ ለመቀየር ችያለሁ፡፡
ነገር ግን አባ ገ/ሥላሴ ከተያዙ ጀምሮ ምንም ልብስ ቀይረው አያውቁም። ሰዎች ልብስ ሲያመጡ ማስገባት አይቻልም፡፡ እያሉ እያስመለሱ ከአንድ ዓመት በላይ በአንድ ልብስ ብቻ ሳናወልቅ ቆይተናል፡፡ ኹለታችንም አብረን በአንድ ዞን የነበርነው ያለምክንያት በታትነውናል፡፡ ሰዎች ሊጠይቁን ሲመጡ የተለያየ ዞን በመኾናችን ጠያቂዎቻችን እክል እየገጠማቸው ነው፡፡ ወደነበርኩበት ዞን ልመለስ” ብለው ጠይቀዋል፡፡
ዳኞቹም፡- “ልብስ ለምን አይገባም?” ብለው የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ሲጠይቁ መልስ መስጠት ባለመቻላቻው “ልብስ ማነው የሚያመጣላችሁ?” ብለው ዳኞች ሲጠይቁ ችሎቱን ሲከታተሉ ከነበሩት ወጣቶች መካከል ለአንዳቸው የሚኾን የምንኩስና ልብስ ገዝተው ይዘው ነበር፡፡ ልብሱን ሲያቀርቡ ዳኞቹ፡- “ጠባቂዎቹን ፈትሹና ስጧቸው!” ቢልም ፍቃደኛ አለመኾናቸውን ሲያሳዩ ዳኞቹ በቁጣ “ተቀበሉና ፈትሻችሁ ስጡ!” በማለት ሲያዙ የማረሚያ ቤቱ ኃላፊ ወታደራዊ ሰላምታ በመስጠት ወደ ዳኞቹ ተጠግቶ ሊናገር ሲል ዳኞቹ፡- “የተባልከውን ብቻ አድርግ! ምንም ሌላ አያስፈልግም!” በማለት ልብሱ ተፈትሾ ለአባ ገ/ሥላሴ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ፍርድ ቤቱም ያቀረቡትን አቤቱታ እና የተሰጠውን መልስ አይተው ውሳኔ ለመስጠት ለመጋቢት 5 ቀን 2010ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ መጋቢት 18 መደበኛ የክስ የሚቀጥል እና ምስክር እንደሚሰማባቸው ይታወቃል፡፡
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ፣ 1641-793-8229 ወይም 1641-715-8596 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው ። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።
Gonder &gojam wotat yekasa yebeley lejoch hero/jegnawoch