Hiber Radio: አወዛጋቢውን የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበር በዚህ ወር እንዲያካልሉ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች መመሪያ ተሰጠ፣በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞው ተጠናክሮ ቀጥሏል፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና ሕዝቡ ጥያቄ ስላልተመለሰ ትግሉ ይቀጥላል ብለዋል፣የአቶ አንዳረጋቸው ጽጌ የጤንነት ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን አንድ ታዋቂ እንግሊዛዊ የጤና ባለሙያ አሳሰቡ፣በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው ረሃብ የዓለማ አቀፉ የግብርና ተቋምን በእጅጉ አሳስቦታል፣ በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ባልታወቀ ሁኔታ የሞተው ወጣት ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ፣አገዛዙ ሙስሊሙና ክርስቲያኑን ለማጋጨት አዲስ ዶክመንተሪ ፊልም አውጥቶ የሙስሊሙን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ከሽብር ጋር አመሳሰለ፣ አልሽባብ በኢትዮ ኬነያ ድንበር ላይ በርካታ ወታደሮችን መግደሉን እና መማረኩን ገለጸ እና ቃለ መጠይቅ ከዶ/ር መረራ ጉዲና ፣ ከጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ጋር እና ሌሎችም አሉን
የህብር ሬዲዮ ጥር 8 ቀን 2008 ፕሮግራም <…አዲሱ የፈጠራ ፊልምን ዶክመንተሪ አልለውም ሙስሊሙና ክርስቲያኑን ለማጋጨት ብለው በከንቱ የደከሙበት ነው …የኢትዮጵያ ሙስሊምና ክርስቲያን ከሃያ አምስት ዓመቱ የወያኔ ስልጣን በፊት ለረጅም ዘመን …
Read More