Hiber radio: የመንግስት ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የወሰዱት የሀይል እርምጃ ዓለም አቀፍ ውግዘት ገጠመው፣በአዲስ አበባ መሬት ዝርፊያ ስማቸው በቀዳሚነት የሚነሳው ወ/ሮ አዜብ መስፍን የማስተር ፕላኑን በመቃወም የተገደሉ ተማሪዎችን ጉዳይ አናናቁ ፣ዕቅዱን ጀምረነዋል እንጨርሰዋለን ሲሉ ዝተዋል፣ኢትዮጵያ በአወዛጋቢው ሕዳሴ ግድብ ላይ የተጀመረው ድርድር ይራዘምልኝ ስትል ጠየቀች፣ኢትዮ-ኬኒያ በጋራ ድንበሮቻቸው ላይ የጸጥታ እና ውጥረት የማብረድ ስራ ሊሰሩ መሆናቸውን አሳወቁ፣አገዛዙ በኦሮሚያ በማስተር ፕላን ስም የጀመረው የመብት ረገጣ የድርቁን አደጋ ትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየርና ሕዝቡን ለመከፋፈል ሊጠቀምበት እየሞከረ መሆኑ ተገለጸ ፣ ቃለ መጠይቅ ከኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ እና ከፓርቲው ዓለም አቀፍ የድጋፍ ቡድን ሰብሳቢ አቶ ነጌሳ ኦዶ ጋር በወቅታዊው የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞና የተወሰደው የግፍ እርምጃ ላይ ወቅታዊ ዘገባና ሌሎችም አሉን
የህብር ሬዲዮ ህዳር 26 ቀን 2008 ፕሮግራም <…የተማሪዎቹ ጥያቄ የዴሞክራሲ ጥያቄ ነው።የመብት ጥያቄ ነው። ተማሪዎቹ ቤተሰቦቻቸው ሲቸገሩ ሲፈናቀሉ ከመሬታቸው ሲነሱና ሲቸገሩ ያዩ ናቸው።ብሶት ነው ያስነሳቸው።በምንም መንገድ በዚህ አካባቢ ሌላው አይኑር …
Read More