
የህብር ሬዲዮ ጥር 15 ቀን 2008 ፕሮግራም
<…የአውሮፓ ፓርላማ ውሳኔ ሕግ ነው አገራቱ ተግባራዊ የሚያደርጉት ትልቅና ጠንካራ ውሳኔ ነው።ይሄ በኦሮሞ ትግል ውጤት የተገኘ እንጂ አውሮፓውያኑ ዝም ብሎ ስለፈለጉ ብቻ የሆነ አይደለም። ሌላውም በኦሮሞ እንደታየው በመግለጫ ብቻ ሳይሆን በተግባር ስራ መስራት አለበት።ተቃውሞን በመግለጫ ብቻ ጥቅም የለውም…ሰራዊቱም የተነሳውን ተቃውሞ እንደ ሀኪሙ፣መምህሩ፣ሰራተኛው ሁሉ ጊዜው ሲደርስ ይቀላቀላል። ሰራዊቱ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ አመራሩም ተቃውሞውን ይቀላቀለቀል ያ አስቀድሞ ታስቦበት የተሰራበት ስትራቴጂ ነው ።ጊዜው ሲደርስ ሁሉም ይታያል…> ጃዋር መሐመድ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ዳይሬክተር የአውሮፓ ፓርላማን ውሳኔ መሰረት አድርገን በወቅታዊ ጉዳይ ለጠየቅነው ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
የአርበኞች ግንቦት ሰባት የኦርላንዶ ፍሎሪዳ የገቢ ማሰባሰቢያ በተመለከተ (ቆይታ ከዝግጅቱ አስተባባሪዎች ጋር)
<<…ሰራዊቱ ብሄራዊ መነሳሳት ሲኖር ሁሉንም ወገን የሚያሳትፍ አጀንዳ ተቀርጾ ሕዝባዊ እምቢተኝነቱም ሆነ የትጥቅ ትግሉ ተጠናክሮ ሲቀጥል ከሕዝቡ ጎን ይሰለፋ።በጭቆና ውስጥ ያለ በዘረኛና ባልተማሩት የወያኔ የጦር ጄኔራሎች የሚመራ ሰራዊት እነሱ እንዳሰቡት አብሯቸው በአንድ ላይ የሚቆም አይደለም። …ዛሬ በኦሮሞ አካባቢ የሚደረገው ትግል በሁሉም አካባቢዎች ሕዝቡ ለመብቱ እምቢ ለወያኔ አልገዛም ብሎ መንቀሳቀስ አለበት። ለዚህም ንቅናቄያችን…> አቶ ነአምን ዘለቀ የአርበኞች ግንቦት ሰባት የውጭ ግንኙነት ሀላፊ በኦርላንዶ ፍሎሪዳ ተገኝተው ካደረጉት ንግግር መካከል ሰራዊቱን በተመለከተ ከተናገሩት የተወሰደ(ቀሪውን ያዳምጡት)
በቬጋስ የሚገኘው የታክሲ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን እንዲፈርስ የተጠየቀበትን የኦዲት ሪፖርት መሰረት አድርጎ የተደረገ ውይይት (ቀሪውን ያዳምጡት)
በቱኒዚያ ውስጥ ሰሞኑን የአንድ ስራ አጥ ወጣት ራሱን በኤሌክትሪክ ሽቦ ላይ ተንጠልጥሎ መሞትን ተከትሎ ያገረሸው አመጽ እና ያስከተለው ፖለቲካዊና ማህበራዊ ቀውስ (ልዩ ዘገባ)
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
በኢትዮጵያ ሰራዊቱ በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ትግል የሚቀላቀልበት ጊዜ ሲመጣ ትግሉን ይቀላቀላል ሲል ጃዋር መሐመድ ገለጸ
የአውሮፓ ፓርላማ ውሳኔ የአገር ቤቱ ጠንካራ ትግል ውጤት መሆኑ ተገለጸ
የአውሮፓ ሕብረት ፓርላማ በኢትዮጵያው አገዛዝ ላይ ያሳለፈው ጠንካራ ውሳኔ በተግባር እንዲውል ኦነግ ጠየቀ
የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባለቤት የእንግሊዝ መንግስት ክህደት መፈጸሙን ገለጹ
በኢትዮጵያ እየታየው ያለው ያለመረጋጋት እና የደህንነት እጦት ምዕራባዊያን ኢንቨስተሮችን እንዳያሸሽ አስግቷል
በአዋሳ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ
በኢትዮጵያ ውስጥ ለተንሰራፋው ድርቅ እና ርሃብ አለማቀፋዊ በቂ ማላሽ መታጣቱ የበጎ አድራጊ ድርጅቶችን በእጅጉ ስጋት ውስጥ ከቷቸዋል
የነገረ ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው በጠበቃና በቤተሰብ ሳይጎበኝ ሌላ ተጨማሪ ጊዜ ለፖሊስ ተፈቀደ
ግብጽ ኢትዮጵያዊያን ሰደተኖችን ከአገሯ አባረረች፣ታንዛኒያ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞችን ወደ እስር ቤት መወረወሯ ታወቀ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።