አርበኞች ግንቦት ሰባትን ጨምሮ አራት ጸረ ወያኔ ታጣቂዎች የጋራ ንቅናቄ መሰረቱ ፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሊቀመንበር ታጋይ ሞላ አስገዶም ም/ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል

 

በኤርትራ የሚገኙ ታጣቂዎች እና የአዲሱ አገር አድን ንቅናቄ ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና ም/ሊቀመንበሩ ታጋይ ሞላ አስገዶም
በኤርትራ የሚገኙ ታጣቂዎች እና የአዲሱ አገር አድን ንቅናቄ ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና ም/ሊቀመንበሩ ታጋይ ሞላ አስገዶም

አርበኞች ግንቦት 7ን ጨምሮ በኤርትራየሚገኙ ዋና ዋና አራት ጸረ ወያኔ ታጣቂ ድርጅቶች የጋራ ንቅናቄ መስርተው ስያሜያቸውን <<የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ>> የሚል አዲስ ድርጅት መመስረታቸውንና ለአዲሱ የጋራ ንቅናቄ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሊቀመንበር፣ ታጋይ ሞላ አስገዶም ም/ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸውን ያሰራጩት መረጃ ገልጻል።

በጋራ ንቅናቄ የመሰረቱት ታጣቂ ድርጅቶች የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲአዊ ንቅናቄ፣የአማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣የአፋር ድርጅቶች የጋራ ንቅናቄ እና አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ሲሆኑ በጋራ ለመሰረቱት “የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ” (የአገር አድን ንቅናቄ) ከሊቀመንበሩና ም/ሊቀመንበሩ በተጨማሪ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴና ልዩ ልዩ መምሪያዎች መቋቋማቸውን ይሄው መረጃ ይገልጻል።

የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ ከአራቱም ታጣቂ ድርጅቶች የተውጣጣ አንድ አገር አድን ሰራዊት ማቋቋማቸውን ገልጸው ሌሎች ድርጅቶችም ጋር የተጀመረው ውይይት መቀጠሉን ጠቁመዋል።

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *