ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ የበዓል ዋዜማ ኮንሰርቱን እንዳያቀርብ መደረጉን ተከትሎ በማህበራዊ ሚዲያ በዜማዎቹ ምሽቱን ለማሳለፍ እንቅስቃሴ ተጀመረ

Teddy_social_media_conceret_07

ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ለኢትዮጵአ አዲስ ዓመት ዋዜማ ሊያቀርብ የነበረውን ኮንሰርቱን በአገዛዙ ባለስልታናት የቀጥታና የተዘዋዋሪ ቻና እንዳአካሂድ መደረጉን ተከትሎ በሚሊኦን የሚቆጠሩ አድናቂዎቹ ከአገር ውስጥና ከውጪ በዕለቱ የዋዜማውን ምሽት በቴዲ ሙዚቃዎች በቀጥታ ለማሳለፍና ለድምጻዊው፣ለፍቅር ያላቸውን ድጋፍ ለስርኣቱ አፈና ቦታ እንደማይሰጡ ለማሳት የተለያዩ ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያው ጥሪ አቀረቡ።

ያልተደራጁ ነገር ግን በየበኩላቸው በሚያቀርቡት ጥሪ የበዓሉን ዋዜማ በአካል የተከለከለውን ኮንሰርት በማህበራዊ ሚዲያው በስፋት በጋራ ሚዚቃዎቹን በማዳመጥ የቀጥታ ስርጭት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር አርብ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ እንዲሆን ጥሪ እያደረጉ ሲሆን ድምጻዊ ቴዲ አፍሮም መረጃው ደርሶት የቀጥታ ስርጭት እንዲከታተል በየገጻቸው ጥሪ አቅርበዋል።

<<ቴዲ አፍሮን ያለስፖንሰር ~ አርብ ምሽት!>> በሚል ከአድናቂዎቹ አንዱ በማህበራዊ ሚዲያው ከአገር ቤት በመጻፍ ከሚጠቀሱት የትነበርክ ታደለ የተጀመረው ጥሪ ብዙዎችን አስከትሎ የቴዲ አፍሮ የበዓል ዋዜማ የሙዚቃ ዝግጅት በሶሻል ሚዲያው በአገር ቤት ያለ ስፖንሰር በፍቅር ስለ ፍቅር እየቴዜመ የአገርና የወገን ተቆርቋነት የሚያደርሰውን አፈና አልፎ ስርጭቱ ያለ ከልካይ ይቀርባል የሚለው የማህበራዊ ሚዲያው ጥሪ እየተስፋፋ ነው።

ለአርብ ምሽት የቴዲ አፍሮ የማህበራዊ ሚዲያው ኮንሰርት መነሻ የሆነውን የትነበርክ ታደለ ከአገር ቤት ያቀረበውን ጥሪ ሙሉውን ተከትሎ ቀርቧል።
ቴዲ አፍሮን ያለስፖንሰር ~ አርብ ምሽት! (የትነበርክ ታደለ) ከልጅነታችንም በምንወደው ነገር እያስፈራሩን ነው ያሳደጉን! የኛ የምንለውን እየነጠቁን “አርፈህ ቁጭ በል! ያለዝያ አታገኛትም!” እያሉ አሳደጉን። ይሄው አድገንም አልቀረልንም። ለቴዲ አፍሮ የሰጠነው ፍቅር ከነሱ ላይ የቀነስነውን መስሏቸው ወሰዱት! ነጠቁን!

ለበአል ዋዜማ ሰብሰብ ብለን የሆድ የሆዳችንን እያወጋን (እየዘመርን~እየዘፈን~እየጨፈርን) አዲሱን አመት እንዳንቀበል አንዴ ስፖንሰሮችን ሲገላምጡ አንዴም ፈቃድ ሲከለክሉ ይሄው ህዝብ የወደደውን ይህን ሰው “ቤትህ ተከተት!” ተብሎ ትእዛዝ ወጣበት።

እኔ በጣም ግርም ይለኛል! አሁን አፍሪካ “ጭለማ” ትባል? ምን በወጣትና? የትኛው የአፍሪካ ሀገር ነው አንድን ዘፋኝ እግር ለእግር እየተከታተለ፣ አመት ካመት ሳይሰለች መከራ የሚያበላ? የቱ ሀገር ነው አንድን ዘፋኝ በህዝብ ፊት ዘፈኑን እንዳያቀርብ እንቅፋት የሚሆን? ጨለማ? ሆ!ሆ!

ስንት በዝሙት የረከሱ፣ በሀሺሽ የደነዘዙ፣ በወንጀል የተጨማለቁ ዘፋኞች እንኳ ይህን ያህል ፈተና ሲደርስባቸው አላየንም። እንኳን ቴዎድሮስ ካሳሁን ግርማሞ…..ከልጅ እስከ አዋቂ የሚያሸረግድለት፣ የልብን ሚስጥር ነጋሪ፣ ችግርን ተጋሪ እንቁ የህዝብ ልጅ ቀርቶ…..

….እኔ ቴዲን ለማንቆለጳጰስ ምንም አቅም የለኝም። እሱም የሚፈልገው አይመስለኝም።

..እና…… ለማንኛውም ለእንቁጣጣሽ ዋዜማ ከምሽቱ ሁለት ሰአት ጀምሮ በዚሁ ፌስ ቡክ ገጻችን ላይ የቴዲ አፍሮን ሙዚቃዎች በተለያዩ ዝግጅቶች አስውበን ለማቅረብ ዝግጅት ላይ ነን እና …..ምንም ትኬት መቁረጥ አይጠበቅባችሁም።…. ሙሉ ወጪውን እኔ ራሴ ችላለሁ….ብቻ በሰአቱ ተገኝታችሁ የዝግጅቱ ታዳሚ ትሆኑ ዘንድ ተጋብዛችኋል።)))))) እግረ መንገዳችሁን ለቴዲም ንገሩት….ላይቭ ተከታተለን በሉልን! ~መልካም በአል!

የቴዲ አፍሮ የአዲስ ዓመት ዋዜማ ኮንሰርት

አርብ ምሽት ከ2 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *