የቴዲ አፍሮ በአገር ቤት በአዲስ አበባ ያቀደው የአዲስ ዓመት ዋዜማ ኮንሰርት መከልከሉን ተከትሎ ከአገር ውስጥ እና ከውጭ በአድናቂዎቹ በተጠራ የፌስ ቡክ ኮንሰርት በነገው ምሽት በቀጥታ የሚካሄድ ሲሆን ለዚህም ህብር ሬዲዮ የቀጥታ ስርጭቱን ለማካሄድ የሚከራ ስርችት በተሳካ ሁኔታ አካሂዲ ሰኣቱን እጠበቀ ነው። የዝግጅዩ ዋና አስተባባሪ ከአገር ቤት የትነበርክ ታደለ አጠቃላይ የእለቱን ኮንሰርት በተመለከተ የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል።በመላው ኣለም የሚገኙ የቴዲ አፍሮ አድናቂዎች በቀጥታ ከላስ ቬጋስ ከተማ በህብር ሬዲዮወደ አገር ቤትና ውጭ ለሚተላለፈው የዋዜማ የፌስ ቡክ ኮንሰርት ፕሮግራም የሙዚቃ ምርጫቸውን ለአዘጋጆቹ ከመልካም ምኞት ጋር መላክ ጀምረዋል።የአዘጋጆቹ መልክትን ያንብቡ።
የቴዲ አፍሮ የፌስ ቡክ ላይቭ ኮንሰርት እንዴት ይካሄዳል? ለዚሁ ታስቦ በተከፈተው ፔጅ ላይ አዝናኝ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ። የመረጣችኋቸው ሙዚቃዎች ከመረጡላቸው ሰዎች ስም ዝርዝር ጋር በዚሁ ፔጅ ይስተናገዳሉ። እነዚህንና ከዚህ በታች ሼር የምታደርጓቸውን በሙሉ (ከስማችሁ ጋር) እየተከታተልን በህብርና ዘ-ሀበሻ ሬዲዮ ጣብያዎች በቀጥታ እናስተላልፋለን። የራዲዮ ጣብያዎቹን ኦንላይን በኢንተርኔት ወይም ከጉግል ፕሌይ ዳዎንሎድ በማድረግ ማድመጥ ትችላላችሁ። ቴዲ አፍሮን በቀጥታ ለማሳተፍ እስከመጨረሻው ደቂቃ ጥረታችንን እንቀጥላለን።
1~ ከምሽቱ ሁለት ሰአት እስከ እኩለ ለሊት ስድስት ሰአት ድረስ የሚቆይ የፕሮፋይል ፒክቸሮቻችንን በድምጻዊው ፎቶ በመቀየር የኮንሰርቱን መጀመር እናበስራለን። በማስከተልም በላፍቶ ሞል ሊካሄድ ታቅዶ በተሰረዘው ኮንሰርት ምክንያታዊነት ላይ ውይይቶችን እናካሂዳለን።
2~ በመቀጠልም ለቴዲ አፍሮና ለስራዎቹ ያለንን አድናቆት የሚገልጹ አጫጭር ጽሁፎች በየገጻችን ላይ ወይም በቴዲ አፍሮ የፌስ ቡክ ኮንሰርት ገጽ ላይ እንለጥፋለን። (ከዚህ ቀደም በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ያደረጋቸውን ቃለ ምልልሶች ሊሆን ይችላል or quotable quotes )
3~ የቴዲ አፍሮን የተለያዩ ሙዚቃዎች ከዩትዩብና ከመሳሰሉት ምንጮች በየገጾቻችን ሼር እናደርጋለን፣ ወዳጅ ዘመዶቻችንን እንጋብዛለን። (እስካሁን ከመቶ በላይ ሰዎች ጃ ያስተሰርያል የሚለውን ታሪካዊ ሙዚቃ መርጠዋል። እርሶም ይህንኑ ፖስት ሊያደርጉ ይችላሉ።)
4~ በቴዲ ሙዚቃዎች በመጨፈር ወይም የተለያዩ የአዲስ አመት መልካም ምኞት በመግለጽ ወይም ምሽቱን እንዴት እያሳለፉ እንደሆነ የሚያሳዩ ወይም ሌላ ተመሳሳይ አዝናኝ የራስዎን የሁለት ደቂቃ ቪዲዮዎች በመቅረጽ ሼር ማድረግ።
5~ ከምሽቱ አምስት ሰአት ጀምሮ የአበባየሆሽ ሙዚቃን ሼር በማድረግ፣ አዲሱ አመት የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የብልጽግና እንዲሆንልን እየተመኘን ደስታችንን እንገልጻለን።
6 ~ ስድስት ሰአት ላይ የፕሮግራሙ ፍጻሜ ይሆናል። [ሰአት በሀገራችን አቆጣጠር ነው።] ወደ ፍቅር ጉዞ ቴዲን ይዞ! ዋዜማው ውብ ይሆናል!
የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።
JAH YASTESERIAL.lemlaw yeEthiopia hezeb
ቴዲዬ ምን ጊዜም ከጎንህ ነን ምርጡ የፍቅር ንጉስ
ነፃነትን ለተጠማው የኢትዮጵያ ህዝብ ” ጃ ያስተሰርያልን” ጋብዙልኝ
በመቀጠል በስደት ላይ ላለችው ጓደኛዬ “ደስ የሚል ስቃይ”
ቴድሻ ሁሉንም ስለምትወድ ታቸንፋለህ!!(ያለበቂ ምክንያት የሚጠሉህንም)
ጃ ያስተሰርያል እና ታም ታራራም አልሄድ አለ
አበባዬሽ የሚለውን መልካም አዲስ አመት ለመላ ኢትዬጲያዊያን