ፕ/ት ኦባማ በኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ተገኝተው ያደረጉት ንግግር በተሌኢ የአፍሪካ አምባገነኖች ረጅም ጊዜ ስልጣን ላይ መቆየት በተሌኢም ገንዘብ እአላቸው ማብቃት አለበት ሲሉ በይፋ ተችተዋል። በዚህ ወቅት ስልታን የሙጥኝ ያሉ የህወሃት መሪዎችና ጨምሮ የበርካታ የአፍሪካ አምባገነኖችን አስታውሰናል።ሙጋቤ ያው ግንባር ቀደሙ ናቸው። በአፍሪካ ያሉትን ችግሮች መዘርዘሩ ለቀባሪው ማርዳት ነው። ሕዝቡ ከችግሩ አልፎ ምን ያህል በፍርሃት ሳቢያ አምባገነኖች የት ድረስ ሊቀልዱበት እንደሚችሉ የሰሞኑ የሙጋቤ ነገር ማሳያ ነው። ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን ሁኔታውን ታዝቦ ጽፎታል።
91 ዓመታቸውን አክብረዋል፡፡ዚምቧቡዌ ነጻነቷን ከተቀዳጀች ጀምሮ እስካሁን ድረስ ሮበርት ሙጋቤ የዛኑ ፓርቲ ሊቀመንበርና የአገሪቱ ፕሬዘዳንት ናቸው፡፡ መቼ ነው ስልጣን የሚለቁት ተብለው ‹‹ህዝቡ የት ሊሄድ ?››በማለት መልሰዋል፡፡ሙጋቤ ለፕሬዘዳንትነት የተፈጠሩ መሆናቸውን ‹‹ስዮመ እግዚአብሄር››አድርገው የሚወስዷቸው መኖራቸው ሙጋቤን ራሳቸውን ‹‹ለዋናው ወንበር የተፈጠሩ አድርገው እንዲወስዱ ሳያደርጋቸው አልቀረም፡፡ ሙጋቤ ጥቁሮች በነጮች ተይዘው የነበሩ የእርሻ መሬቶችን እንዲወስዱ ማድረጋቸውና ለነጮች አለማጎብደዳቸው አፍቃሪ አፍርቶላቸዋል፡፡ከቅርብ አመታት ወዲህ ግን ከዕድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ የሚመጣው የጤንነት መቃወስ በአደባባይ መሬት ለመሬት ሲጎትታቸው ቢታይም ሙጋቤ የአረጀ አንበሳ ግሳታቸውን በግል ጠባቂዎቻቸው ላይ በማንቋረር ሲያባርሩና ሲያስሯቸው ቆይተዋል፡፡ አስቂኙ ነገር ደግሞ ሙጋቤ አንዷን ዚምቧቡዌን ለመምራት አቅም ከድቷቸው እየተመለከትን በአፍሪካ ህብረት የተሰገሰጉ ጓዶቻቸው ህብረቱን እንዲመሩ መርጠዋቸዋል፡፡የአህጉሪቱ ድርጅት የባለስልጣናቱ ከገላ ማከኪያነት ያለፈ ሚና ቢኖረው ሙጋቤ የአፍሪካዊያን ፕሬዘዳንት ይሆኑ ነበር ማለት ነው፡፡ ለማንኛውም ዛሬ ከወደ ሐራሬ የሙጋቤን እርጅና የሚያሳብቅ ተጨማሪ ዜና ተገኝቷል፡፡ከወር በፊት ለፓርላማ ንግግር ሲያደርጉ አቅርበውት የነበረን ወረቀት በዛሬው የፓርላማ ውሎም በድጋሚ አንብበውታል፡፡ሙጋቤ ወረቀቱን ሲያነቡት ለማስታወስ እንኳን አለመቻላቸውም አነጋጋሪ ሆኗል፡፡የፕሬዘዳንቱ ጽ/ቤት በኋላ ላይ ባወጣው ማስተባበያ ‹‹ስህተቱ የተፈጸመው ሙጋቤ ለዛሬው ፓርላማ ለማንበብ ያዘጋጁት ወረቀት ከባለፈው ወር ጋር በመደበላለቁ ነው፡፡ስህተቱ በዋናነትም የሚመለከተው ጸሐፊያቸውን ነው››ብሏል፡፡ አንድ አስቂኝ ነገር እንጨምር በፓርላማው የዛኑ ፓርቲ ተመራጭ የሆኑ አባላትም በፕሬዘዳንቱ ንግግር ዙሪያ ሞሽን ለማድረግም ተዘጋጅተው ነበር፡፡ተቃዋሚዎች በበኩላቸው ‹‹ሰውዬው ወንበሩ ላይ እስኪሞት መጠበቅ አይገባንም እናም በቃኝ ይበሉ››ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ በዜናው ልስቅ አሰብኩና መቶ አለቃ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ትዝ አሉኝ፡፡
የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።