(በታምሩ ገዳ) የሮማው ካቶሊክ ቤ/ክ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አቡነ ፍራንሲስ በአሜሪካ የሚያደረጉትን የ 6 ቀናት ጉብኝታቸውን ለማደረግ እሮብ እለት ከቀትር በሁዋላ ወደ ዋሽንገተን ዲሲ ጎራ ሲሉ ከተቀበሏቸው ታላላቅ መሪዎች (ፕ/ት ኦባማን እና ቤተሰቦቻቸው ጨምሮ) ይልቅ 11ሚለዮን ሰዎችን በመወከል ከካሊፎርኒያ /ሎሳንጀለስ ከተማ ድረስ ተጉዛ ፓፓውን በግንባር ያገኘችው የ 5 አመቷ ሶፊያ ክሩዝ ትልቅ አለም አቀፍዊ የዜና ሽፋን ለማግኘት እና ታሪካዊት ልጃገረድም ለመሆን ችላለች። ስፊያ አሜሪካ ውስጥ በመወለዷ ሙሉ የአሜሪካ ዜግነት ያላት ሲሆን ከጎረቤት ሜክሲኮ በህገወጥ መንገድ የመጡት ወላጆቿ ግን ህጋዊ ሰንድ የላቸውም። ታዲያ በአሜሪካ ህግ መሰረት በማነኛውም ጊዜ ሊባረሩ የሚችሉት ወላጆቿ እና መሰል 11 ሜሊዮን ሰደተኞች ጉዳይ እንቅልፍ የሚነሳት ሶፊያ አባቷን ጨምሮ ከጥቂት አክቲቪስቶች ጋር በመሆን ለአቡነ ፈራንሲስ ደህንነት ሲባል ልዩ እና እጅግ ጥብቅ የጸጥታ ቁጥጥር ወደ ነበረበት የ ዋሽንግተኑ ስለፍ ላይ ከተገኙት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የብጹነታቸው አፈቃሪዋች እና ምእመናን ጋር በመቀላቀል የፓፓውን መምጣት ይጠባበቁ ነበር።ታዲያ አቡኑ ወደ ሕዝቡ ሰቃረቡ ትንሿ ሶፊያ የደህነነት ጥበቃው አጥርን በማቋረጥ ወደ አቡነ ተንቀሳቃሽ መኪና መሮጧን የተመለከቱ የደህንነት ጥበቃዎች ሶፊያን ለማገድ/ለመከለከል ቢሞክሩም ሁኔታውን የተመለከቱት አቡነ ፈራንሲስ በምልክት ”ጨቅላ ህጻኑዋን ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ አትከልክሏት” በማለታቸው የተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በጽጥታ ሃይሎች የተዋከበችው እና የተገፈተረችው ሶፊያ ከጥቂት ደቂቃዎች በሁዋላ በነዚያ ባዋከቡዋት የጥበቃ ሰራተኞች በአንደኛው እቅፍ ተይዛ አቡነ ፍራንሲስ ከቆሙባት ግልጽ አውቶ ሞቢል በመቅረብ የበጹነታቸውን አባታዊ ቡራኬያቸውንም አግኝታለች። የትንሿ ሶፊያ እና የ ፓፓው ድንገተኛ ግንኙነት በዚህ ብቻ አላበቃም ። የወላጆቿ ከአሜሪካ ምድር የመባረር ሰጋት ከልቧ የገባዋ ሶፊያ በእጇ የጻፈችው ደበዳቤ ለብጹነታቸው በግንባር ተገኝታ በእጇ ሰጥታለች። መልእክቱም በከፊል “ብጹ አቡነ ፍራንሲስ ውሰጤ በእጅጉ ማዘኑን ለገልጽሎት እፈልጋለሁ።እንደማንኛውም ሰው ከወላጆቼ ጋር የመኖር መብት እንዳለኝ አምናለሁ፣ ደስተኛ የመሆን ተፈጥሮአዊ መብት አለኝ፣ የእኔን ቤተሰቦችን ጨምሮ ሁሉም ሕገ ወጥ ሰደተኞች ለአሜሪካ ህዝብ ካሮት ፣ብርቱካን ፣ሽንኩርት ፣ጎመን እና የመሳሰሉትን በማብቀል እና ለገበያ በማቅረብ ልዩ አስተዋጽኦ በማደረጋቸው ተገቢው ክብር እና ሰብእና ሊሰጣቸው ይገባል፤ብጹነቶ ወላጆቼ በማንኛውም ጊዜ ከአሜሪካ ምድር ሊባረሩብኝ ሰለሚችሉ እባክዎትን ፕ/ት ኦባማን ሆነ ኮንግረሱን አቋማቸውን እንዲቀይሩ ተማጸኑልኝ ”ይላል። ከጽሁፉም በተጨማሪ ፓፓው በግራ እና በቀኝ እጆቻቸው የተለያዩ ዝርያ ያላቸው ህጻናት “የቱንም ያህል ቀለማችን ቢለያይም እኔ እና ጓደኞቼ እንዋደዳለን” የሚል የግርጌ ማስታወሻ ተጽፎበት ይገኛል።የሶፊያ ወላጅ አባት የሆነው ራዎል ክሩዝም ከጉብኝቱ በሁዋላ “ አቡነ ፍራንሲስ የእግዜአብሔር መልክተኝእበመሆናቸው ልጄ ብጹነታቸውን በግንባር አግኝታ መባረኳ በራሱ ተአምር ነው።” ብሏል።
ትንሿ ሶፊያም የ11 ሚሊዮን ሰንድ አልባ ሰደተኞች ሰጋት እና ጭንቀት የሆነው በአሜሪካ ምድር በሰላም ሰርቶ የመኖር ሕጋዊ መብትን ለ76 አመቱ ፓፓ ከማደረሰ በተጨማሪ በዙዎች በቅርብ ርቀት ሊያዩዋቸው የሚመኙት አቡነ ፈራንሲሰን ጥምጥም ብላ ለመሳም እና በእጃቸውም ለመባረክ እድሉን አግኝታለች። የሶፊያ መልእክትን በጥሞና የተረዱት እና ሁሌም የሚያነሱት አባ ፍራንሲስ ሐሙስ እለት ከ አሜሪካ ኮንግረስ አባላት ፊት ቀረበው ባሰሙት ንግግር”እኔም የሰደተኞች ልጅ ነኝ፣ሰደተኞችን አንፍራቸው፣ አንግፋቸው። በአንድ ወቅት ሁላችንም እንግዶች/ሰደተኞች ነበረን።”በማለት መንፈሳዊ እና አባታዊ ምክራቸውን ሰጥተዋል። በመደረኩ ላይ የነበሩት በተለይ አፈጉባኤው(ካቶሊኩ) ጆን ቢይነር እንባቸው ልውረደ ፣አልውረድ እያለ ሲተናነቃቸው ተስተውለዋል።ከብዙ ሰደተኞች ቤተሰቦች እንደተገኙ የሚናገሩት አብዛኞቹ የአሜሪካ ኮንግረስ ኣባላትም “በአንድ ወቅት ሁላችንም እንግዶች ነበርን !”የሚለው የኣቡነ ፍራንሲስ አባባል ለጊዜውም ቢሆን ከልባቸው ዘልቆ የገባ የመሰላል።የሶፊያ ሆነ የብጹነታቸው ሰጋት እና መልእክትም ከምድረ አሜሪካ ውጪ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰደተኞች ወቅታዊ እና አስከፊው ሁኔታን ማመላከቱ አይቀረም።
የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።