የህብር ሬዲዮ መስከረም 16 ቀን 2008 ፕሮግራም
<… በሳውዲ በሚና በደረሰው አደጋ የሞቱና የቆሰሉ ኢትዮጵያውያን ሓጃጆች ቁጥር ለማወቅ የጋራ ጥረት የተቀናጀ ስራ መስራት ግድ ይላል ብዙ አገሮች ተቀናጅተው ሰርተው የሞቱ ዜጎቻቸውን ማንነት በቀላሉ ለይተዋል። እኔ እንኳን እዚሁ ሳውዲ ውስጥ የአምስት ሟች ወገኖቻችንን ለቅሶ ደርሻለሁ። ሁለት ሰዎች ብቻ የሚለው …> ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ከሳውዲ አረቢያ በሐሙሱ አደጋ ሳቢያ የሞቱና የቆሰሉ ኢትዮጵያውያን አለመታወቁን በተመለከተ ከህብር ሬዲዮ ተጠይቆ ከሰጠው ማብራሪያ (ሙሉውን ያዳምጡ
በቬጋስ የመስቀል በዓል አከባበር (ልዩ ቃለ መጠይቅ)
<…ካሳለፍነው ጊዜ በመነሳት ይሄ ገዢ ፓርቲ ሁሉን ነገር ለፖለቲካ ፍጆታ ለማስመሰል የሌለውን አለ በማለት ነው እዚህ ድረስ የዘለቀው። ከዚህ በፊትም ፓርላማ ውስጥ እያለን የተራበውን ሰው ቁጥር ቀንሰው ይከራከሩ ነበር። በሰው ሕይወት ላይ መጫወት ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት አቅመ ቢስ መሆናቸውን ነው… የድርቅ ጉዳይ በአንድ ሌሊት የተከሰተ ጉዳይ አይደለም ደግሞ ደጋግሞ የተከሰተ ነው…> አቶ ተመስገን ዘውዴ ቀድሞው የፓርላማ አባልና በጉልበት የፈረሰው አንድነት ፓርቲ የብሄራዊ ም/ቤት ሰብሳቢ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለህብር ከሰጡት ምላሽ የተወሰደ ክፍል አንድና ሁለት (ሙሉውን ያዳምጡ)
በአገር ቤት ባለው የሰብአዊ መብት ረገጣ ሳቢያ ዓለማቀፋዊ እውቅና ያላቸው በርካታ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሜሪካ ውስጥ ለጉሰቁለና ኑሮ መዳረጋቸው ተገለጸ(ልዩ ጥንቅር)
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በአፍሪካ ቀንድ ፈጥኖ ደራሽ ጦር እንዳይቋቋም እንቅፋት ሆነዋል ተባሉ
ኢትዮጵያ የሶማሊያ ወጣቶችን ለጦርነት እያሰለጠነች መሆኑ ታወቀ
በሳውዲ ለሐጂ ሀይማኖታዊ ስርዓት ሔደው በአደጋ የሞቱት ኢትዮጵያውያን ቁጥር ዛሬም ተለይቶ አልታወቀም
የሟቾች ቁጥር መጨመሩን የአገሪቱ ባለስልጣናት ገለጹ
በዲሲ በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በፖለቲካ ሳቢያ ተሰደው ብርቱ ፈተና ገጥሟቸዋል ተባለ
ከኢትዮጵያ በሕገወጥ መንገድ ወደ አየርላንድ እና ወደ ስሎቫኪያ የገባ በርካታ ደረቅ ጫት በቁጥጥር ሰር ዋለ
አንድ ኢትዮጵያዊ ተጠረጣሪም ከፖሊስ እጅ ወደቋል ተባለ
አገዛዙ ዕድሜ በጨመረ ቁጥር የአገሪቱ ችግሮች እየተባባሱ ስለሚሄዱ ለውጥ በአገሪቱ መምጣት አለበት ሲሉ የቀድሞ የፓርላማ አባልና የተቃዋሚ መሪ ገለጹ
የሙዚቃው ንጉስ ጥላሁን ገሰሰ በማህበራዊ ሚዲያው ልደቱ እንዲዘከር ጥሪ ቀረበ
ኦብነግ በአልሸባብ ለተቀሉ ሁለት አመራሮቹ ሞት የኢህአዴግ ደህነቶች እጅ ከጀርባ ሊኖርበት እንደሚችል ገለጸ
ኢትዮጵያ ለከፋ የረሀብ አደጋ መጋለጧን የኢሕአዲግ ባለሰለጣናት አመኑ
ዓለማቀፍ ግብረሰናይ ድርጅቶች ፊታቸውን ወደ ጎረቤት ኬኒያ አዙረዋል
ሌሎችም ዜናዎች አሉ
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።
https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-092715-100415