ከመቀሌ የምታንሱ ከተሞች እነማን ናችሁ›! በሱስ እንዲጠፋ የተፈረደበት ትውልድ!

ethiopia_shisha_kachat_02

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን የሚያስተዳድረው ማነው? የሚል የጅል ጥአቄ የሚአነሳ ያለ አይመስልም። የአገሪቱን ዋና ዋና ስልጣን የተቆታጠረው ሕወሃት ዋናው መሪ እሱ ነው። ኢህአዴግ የሚለው የሕሠሃት ጃንጥላ እንደ አየሩ ጸባይ ሲፈልገው የሚጠቀምበት፣ጃንጥላ ያዦችም በተፈለጉ ጊዜ የሚለወጡበት ነው። ዓት ትውልዱን አጠፋ፣መጠጥ ቤት ተስፋፋ፣ሀሺሽ በጠራራ ጸሐይ ይጨሳል <<ወዮ ለዚህ ትውልድ>> የሚል ጩኸት ከዛሬ ሃያ ኣመት በፊት ጀምሮ ነበር። ዋና መቀመጫውን መቀሌ ያደረገው የአገሪቱ የበላይ ባለስልጣን ሕወሓት ከዛሬ ሃአ ዓመት በፊት ጀምሮ <<ትግራይን>> ይሄ አስፈሪና ትውልድን በቁሙ እያነተበ ያለ የሱስ ወረርሽኝ ላይ ጠበቅ ያለ እርምጃ ሲወሰድ ቆይቷል። የአገሪቱን ዋና ከተማ ጨምሮ ሌሎች በሕወሓት መዳፍ ስር ከማጀት እስከ አደባባይ የሚዳመጡ፣በሱ ጭቃ ሹሞች የሚራወጡት ግን ኢሄ ለመቀሌ የደረሰው ትውልድን አድን ስትራቴጂ ተግባራዊ አልተደረገባቸውም።አያውቁም እንዳይባል ገና ከአፍላው ጀምሮ በነጻ ፕሬስ ጋዜጦች ይሄው ጉዳይ አንድ ሰሞን ሲጻፍ ነበር። ሰሚ ግን የለም። ዛሬ መቀሌ የት ላይ ነች? ሌሎችስ ተከታዩን ምልከታ አንብቡት።

ከመቀሌ የምታንሱ ከተሞች እነማን ናችሁ›!

(የትነበርክ ታደለ)

የሰሜኗ ፈርጥ የትግራይ ዋና ከተማ ሰሞኑን በአንዳንድ አለማቀፍ ሚዲያዎች ላይ ስሟ ሲነሳ አይቼ የተሰማኝን ደስታ ልገልጽላችሁ አልችልም። ምሳሌ የሚሆን ነገር ተገኝቶብን መነጋገርያ ስንሆን ከማየት በላይ ምን ያስደስታል።

እርግጥ ዜናውን ከዚህ ቀደም የሰማሁት ቢሆንም ይህን ያህል እውነት ሆኖ የሌሎችን ቀልብ እስከመሳብ ይደርሳል ብዬ በፍጹም አላሰብኩም። ብዙ ነገሮች በወሬ ሲቀሩ እያየሁ እንዲህ ብጠረጥር አይፈረድብኝም!

ለማንኛውም መቀሌ ለብዙ አፍሪካ ከተሞች ምሳሌ እስከ መሆን ደርሳለች ነው የተባለው። ዘገባው እንዳለው ባሁን ሰአት ብዙ የአፍሪካ ከተሞች ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች በተለይ ወጣቶች በአልባሌ ሱሶች እየተጠመዱ ነው። ይህንንም ችግር ለመቅረፍ ከተሞቹ በርካታ ህጎች ቢያወጡም ምንም ለውጥ ማምጣት አልቻሉም እና መቀሌ በዚህ ረገድ ተሳክቶላታል።

መቀሌ ውስጥ ጫት መቃም አይቻልም። መቀሌ ውስጥ ህዝብ በሚበዛባቸው ስፍራዎች ትምባሆ ማጨስ ፈጽሞ የተከለከለ ነው። ይህንንም የከተማው አስተዳደር ቀንና ማታ እየተከታተለ እርምጃ የሚወስድበት ወንጀል መሆኑ ተነግሯል!

እንዴት ደስ ይላል! ይህን ያሰበ፣ ያሳሰብ፣ የፈጸመና ያስፈጸመ ሁሉ ምስጋና ይገባዋል! በማህበራዊ ህይወታችን ከፍተኛ ቀውስ እያደረሰብን ያለ ትልቅ በሽታችን ነውና ይህን በማደረግ ላይ የሚገኙ ሁሉ ሽልማት ይገባቸዋል!

ነገር ግን! ሌሎች ከተሞችስ ወጣቶቻችንን እንደዚህ ባለ አጉል ልማድ ሰጠፉ እያዩ ዝም ለማለት እንዴት ፈቀዱ? አዲስ አበባ ላይ ወጣ የተባለው ህግ የት ደረሰ? ለምንድነው የአዲስ አበባ መስተዳድር በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያወጣቸውን ህጎች ችላ የሚላቸው? ህጻናት ሳይቀሩኮ በየትምህርት ቤቱ ሽንት ቤት ውስጥ ከሲጋራም አልፈው ሀሺሽ እያጨሱ ነው! አዲስ አበባ ቀንና ማታውን ለመለየት አስቸጋሪ ሆኗል እኮ!

እነ ወልቂጤ ጂማ አዋሳስ? ኧረ ሁሉም ከተሞቻችን! ጫት የተባለ አረም ከትልቁ የመንግስት ባለስልጣን አንስቶ በየመንገዱ የሚንገላወደውን ሁላ እግር ከወርች አሳስሮት መንቀሳቀስ ሲሳነው ምነው ዝም አላችሁ? ነው ወይስ ሱስ የሚለው ነገር በመቀሌ ትርጉሙ የተለየ ነው?

እውነቴን ነው የምልካችሁ ወደ ጂማ አካባቢ ብትሄዱ ደሙ ሞላ ያለው ወጣት ለማየት ይናፍቃችኋል። ጫት ምጥጥ አድርጎት! በዚህ ላይ ሲጋራና መጠጥ ተጨምሮበት! ከዚህ ትውልድ ሀገር ምን ትጠብቃለች?

መንግስት ወጣቱ ተሰደደ በሚለው ጩሀት ላይ ብቻ ምላሽ ለመስጠት ይሞክራል። ግን ሀገር ውስጥ የቀረው ወጣት ራሱ ምን እየሰራ እንደሆነ በደምብ ያጤነው አይመስልም!

አድናቆቴን ላጠቃለው! መቀሌንና ነዋሪዎቿን እንዲሁም ከሱስ ነጻ ህብረተሰብ ለመፍጠር እየጣረ ለሚገኘው የከተማው አስተዳደር ምስጋና አቅርቡልኝ! ሌሎች የራሳችሁን የከተማ አስተዳደሮች ግን “ከዚህ ተማሩ ለወጣት የማያስብ አስተዳደር ምን ያስተዳድራል?” ብላችሁ ጠይቁልኝ!

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *