Hiber Radio :የቀድሞው የአየር ሀይል አዛዥ ሜ/ጄ/ል አበበ ተክለሀይማኖት(ጆቤ) የይስሙላው ፓርላማ የአገሪቱን ሐብት ከሚያባክን ይፍረስ ሲሉ ጠየቁ፣ አቶ ሀይለማሪያም ቁጥራቸው 15 ሺህ የሚደርሱ የሱማሌ ክልል ልዩ ሀይሎችን ትጥቅ ፍቱ ማለታቸው ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱ ተዘገበ፣የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ቢራቡም ተቃውሞ እንዳያነሱ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው ፣ አልሸባብ በኢትዮጵያው አገዛዝ ወታደሮች ላይ ጥቃት ሰነዘርኩ አለ፣ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን አንደኛ ዓመት የግፍ እስርን በመቃወም በማህበራዊ ሚዲያው ተቃውሞ ተጠራ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቻይናውያን የበረራ አስተናጋጆችን መቅጠሩ ያስከተለበት ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው እና ሌሎችም አሉን

Hiberradio_progeram_cover10115_01

የህብር ሬዲዮ  መስከረም 30 ቀን 2008 ፕሮግራም

<… ህገ መንግስቱ መሻሻል ሁሉም ባይሆን አብዛኛው ሕዝብ የሚቀበለው መሆን አለበት። እነ ኦነግን መኢሶንና ኢህአፓን ጨምሮ የሕዝቡ ሀሳብ ተካቶ ውይይት ተደርጎበት መሻሻል አለበት…ሕገ መንግስት ማሻሻል አለበት የሚለውን በአንዳንድ አፍሪካ አገሮች እንደታየው ለዕድሜ ማራዘሚያ ሊጠቀሙበት ይችላሉ ወይ የሚለው ሊሆን ይችላል ነገር ግን… >   ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ተከብሮ የማያውቀውን ሕገ መንግስ ይሻሻል ማለቱ ምን ጥርጉም አለው በሚሉና በሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች ካደረግነው ውይይት   (ሙሉውን ያዳምጡ)

ዕውቁ የኢትዮጵያ ፈርጥ ጋዜጠኛ፣ዲፕሎማት፣የታሪክ ጸሐፊ  አምባሳደር ዘውዴ ረታ ማን ናቸው (ልዩ ጥንቅር)

<…የኩላሊት በሽታ አሳሳቢ ነው። በተለይ አመጋገባችንን ማስተዋል አለብን ስጋ የምናበዛ ከሆነ ብዙ ውሃ ካልጠጣን ወይ በቤተሰብ የኩላሊት በሽታ ካለ በየጊዜው ሕክምና ማድረግ እና ማረጋገጥ ይጠበቅብናል ….ለገንዘብ ሲሉ ቀዶ ጥገና ያደርጋሉ በሚል የሕክምና ባለሙያዎች የሚሰጡትን ምክር ማናናቅ ተገቢ አይደለም አስቀድሞ መከላከሉ ላይ ማተኮርም ይገባል። ይህ ሳይሆን ግን…>

ዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን  የኩላሊት ጠጠር እና አብሮት የሚመጣውን ተያያዥ ችግሮች ከነ መፍትሄያቸው አብራርተዋል(ሙሉውን ያዳምጡት)

ሁበር እና የሁበርን በቬጋስ ስራ መጀመር ተከትሎ በኩባንያዎች በኩል የሚወጡ የውስጥ መመሪያዎች ምን ያህል ይገድባሉ? በአሽከርካሪው በኩል ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎችና  የተፈጠሩ ችግሮች (ውይይት ከአድማጮች የቀረቡ ጥያቄዎች ላይ)

የአሜሪካና አጋሮቿ የምዕራቡ ዓለም   ከሩሲያ ጋር በሶሪያ  ጉዳይ አይ.ሲ.ስን በመዋጋት ሰበብ የጀመሩት ወታደራዊ ፍጥጫ ሳምንታዊ ሁኔታ ሲቃኝ (ልዩ ጥንቅር)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የቀድሞው የአየር ሀይል አዛዥ ሜ/ጄ/ል አበበ ተክለሀይማኖት(ጆቤ) የይስሙላው ፓርላማ የአገሪቱን ሐብት ከሚያባክን ይፍረስ ሲሉ ጠየቁ

የመቶ በመቶ ምርጫ አሸነፍኩ ማለት የሚያስፎክር ሳይሆን የአደገኛ ሁኔታ ምልክት ነው ብለዋል

አቶ ሀይለማሪያም ቁጥራቸው 15 ሺህ የሚደርሱ የሱማሌ ክልል ልዩ ሀይሎችን ትጥቅ ፍቱ ማለታቸው ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱ ተዘገበ

አልሸባብ በኢትዮጵያው አገዛዝ ወታደሮች ላይ ጥቃት ሰነዘርኩ አለ

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ቢራቡም ተቃውሞ እንዳያነሱ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን አንደኛ ዓመት የግፍ እስርን በመቃወም በማህበራዊ ሚዲያው ተቃውሞ ተጠራ

የዕውቁ የነጻነት ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ ልጄ የሰብዓዊ መብት ሽልማት አሸናፊ ሆነች

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቻይናውያን የበረራ አስተናጋጆችን መቅጠሩ ያስከተለበት ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber_radio_101115-102215

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *