በእስር ቤት የሚገኘው ታዋቂው ፖለቲከኛ ሃብታሙ አያሌው ዛሬ በድንገተኛ ህመም ዘውዲቱ ሆስፒታል ተወስዶ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። በዛሬው ዕለት ሃብታሙ ከ እስር ቤት ወደ ዘወዲቱ ሆስፒታል የተወሰደበት ምክንያት በሁለቱም ጎኖቹ ላይ የህመም ስሜት ስለተሰማው መሆኑን ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ዘግቧል:: የዘውዲቱ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች ምርመራ ካደረጉለት በኋላ ህመሙ የኩላሊት ጠጠር መሆኑን ለባለቤቱ ወ/ሮ ቤተልሄም መናገራቸውን በዚሁ ዘገባ ምንጮች አብራርተዋል:: ሃብታሙ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የተመለሰ ሲሆን በነገው ዕለትም ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ተገልጿል:: ከሃብታሙ አያሌው ጋር አብረው የተከሰሱትና በቅርቡ በከፍተኛው ፍርድ ቤት በነፃ የተለቀቁት አብርሃ ደስታ; ዳንኤል ሺበሺና የሺዋስ አሰፋም በነገው ዕለት አቃቤ ሕግ ይግባኝ በጠየቀባቸው ክስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርበው የቃል ክርክር ያደርጋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ከዚህ ቀደም የከፍተናው ፍርድ ቤት በነጻ ይለቀቁ ብሎ ይግባኝ እስኪጠየቅ በእስር ላይ እንዳሉ ይግባኝ ተጠይቆባቸው እየተንገላቱ ቆይተዋል።
ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ክርክሮች መሰረት የእስር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ላይ የሕግ ስህተት አለ ተብሎ ሲታመን ነው። እስረኞቹን ለማጉላላት ካልሆነ በቀር የአገዛዙ መዳፍ ስር ያለ የእስር ፍርድ ቤት ነጻ ሲላቸው ሳይፈቱ ማቆቱ የስርዓቱን ለሕግ አለውን ንቀት ያሳያል የሚሉ ቅሬታዎች ሲደመጡ ቆይተዋል።
የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።