በኦነግ ስም ተከሳ ዕድሜ ልክ የተፈረደባት ትምህርት እንዳትማር ተከለከለች

Poltical_prisoner_in_ethiopia

በ2004 ዓ.ም በኦሮሞ ነፃአውጭ ግንባር (ኦነግ) አባልነት ተጠርጥራ ከታሰረች በኋላ የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደባት አሊማ አብዲ መሃመድ እንዳትማር መከልከሏን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትገኘው አሊማ (ቢፍቱ) አብዲ ባለፉት አራት አመታት በማረሚያ ቤት እየተማረች እንደነበርና አምስተኛ ክፍልም መድረሷ የተገለጸ ሲሆን በመከልከሏ ትምህርቷን ማቋረጧን ነገረ ኢትዮጵያ ዘገበ።

ይሁንና በዚህ አመት እንዳትማር የተከለከለች ሲሆን የተከለከለችበትን ምክንያት ስትጠይቅም ‹‹አንቺ መማር አይገባሽም!›› እንደተባለች ነገረ ኢትዮጵያ ታማኝ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግባል። አሊማ አብዲ መሃመድ የ23 አመት ወጣት ስትሆን በመደበኛ ጊዜ እንዳትጠየቅ በመከልከሏ ክፍለ ሀገር በሚኖሩት የተወሰኑ የቤተሰብ አባላት ብቻ ከ6፡00 እስከ 6፡30 ለሰላሳ ደቂቃ ብቻ እንደምትጠየቅ ለማወቅ ተችሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዝዋይ እስር ቤት በከባድ የጀርባና የጆሮ ሕመም እየተሰቃየ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሕክምና የተከለከለ ሲሆን ከጥቂት የቤተሰቡ አባላት በስተቀር ጠያቂም መከልከሉ አይዘነጋም።ጋዜጠኛ ተመስገን ዛሬ ከታሰረ አንድ ዓመት የሞላው ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያው የተመስገንን የግፍ እስር በመቃወም ላለፉት ሶስት ቀናት የተካሄደው ዘመቻ ዛሬ ያበቃል።

በኢትዮጵያ በልዩ ልዩ እስር ቤቶች በሚገኙ ፖለቲካ እስረኞች በፈጠራ ክስ ፣ማሰቃት ከታከለበት ምርመራና የግዳጅ ቃል መቀበል በሁዋላም የስርኣቱ የበቀል እርምጃ በጋዜጠኞች፣በሙስሉም መፍትሄ አፈላላጊዎች፣በተቃዋሚ ድርጅት ዋና ዋና አባላትና አመራሮች እና ከተሌኤዩ አካባቢ እታፈኑ በኦነግ፣በአርበኞች ግንቦት ሰባት፣በኦጋዴን ነጻውጭና በተለያዩ ስሞች ታስረውም መቀጠሉ ከዚህ ቀደም ተደጋግሞ መገለጹ ይታወሳል።

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *