በመንፈሳዊ አባትነታቸውና አጥማቂነታቸውየሚታወቁት መምህር ግርማ ታሰሩ

memehir_girma_04

መምህር ግርማ ወንድሙ ከአገር ቤት አልፈው በተለያዩ የውጭ አገራት እየተዘዋወሩ መንፈሳዊ ትምህርትና የማጥመቅ ተግባር በመፈጸም በርካቶች ከጽኑ ሕመም መዳናቸውን እየመሰከሩ ባሉበት በአሁኑ ወቅት ከውጭ ወደ አገር ከገቡ በሁዋላ በዛሬው ዕለት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል። ፖሊስ በምን ወንጀል እንደያዛቸው ያልተናገረ ሲሆን ከቤተ ክርስቲያን ፈቃድ የላቸውም መባሉን ለማወቅ ተችሏል።

መምህር ግርማ ወንድሙ በአገር ውስጥ ሆነ በውጭ መንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠት የቤተ ክህነት ፈቃድ አስቀድሞ የነበራቸው ሲሆን ከጥቂት ጊዜ በሁዋላ ፈቃዱን በሌሎበት አግደናል የሚሉ አስተያየቶች ሲሰጡ ቢቆይም ይህ የቤተ ክህነቱ ባለስልታናት ቅሬታ በየትናው የሕግ አግባብ መምህር ግርማን እንዳሳሰራቸው ፖሊስ አለመግለጹን ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

መምህር ግርማ ፈቃድ የላቸውም እአሉ ሲከሱ የቆዩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን በበላይነት የሚያስተዳድሩት የቤተ ክርስቲያኒቱ ባለስልጣናት በአገዛዙ ይሁንታ ወደ ስልታን የመጡና በአብዛኛው ከአንድ ብሄር ተውጣጡ ሲሆን እነዚህ ወገኖች ለቤተ ክርስቲያኒቱና ለመንፈሳዊ አገልግሎቱ በመቆርቆር ሳይሆን የእነሱ ታዛዥ ያልሆኑ መምህራንን ሲያግዱ፣የሀይማኖት አባቶችን ሲያባርሩ፣ሕዝብ በይፋ የሀይማኖት ህጸጽ አለባቸው ብሎ በማስረጃ የሚቃወማቸውን ሲሾሙ ፈቃድ ሲሰጡ መቆታቸው ተደጋግሞ መዘገቡ ይታወሳል።

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *