አቶ ምትኩ ተሾመ ምርጫ 97ን ተከትሎ ዛሬም ድረስ ስልጣን ላይ ባለው አገዛዝ የሀይል እርምጃ የተገደሉትን ፣የቆሰሉትን፣የታሰሩትን እና የደረሰውን ጉዳት ለማታራት የተቋቋመው ሕጋዊው አጣሪ ኮሚሽን አባል ናቸው። የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ዳኛ ፍሩህይወት ሳሙኤል፣ም/ሰብሳቢ ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻና የዛሬ እንግዳችን የኮሚሽኑ የመጨረሻ ውሳኔ አገዛዙን ባለማስደሰቱ ለመቀልበስ እጅ ጥምዘዛ ውስጥ ሲገቡ ታላቅ መስዋዕትነት ከፍለው የተፈጸመውን ግፍ አጋልጠዋል።ዛሬም ድረስ በዚህ ታላቅ የግፍ ድርጊት የተጠየቀ የለም።የሰማዕታቱን 10ኛ ዓመት መታሰቢያ አስመልክተን ከአቶ ምትኩ ተሾመ ጋር ቆይታ አድርገናል። ወደ ሁዋላ ከአስር ዓመት በፊት ቤተሰቦቻቸው፣ወገኖቻቸው በግፍ የተገደሉትን በጊዜው ለመገናኛ ብዙሃን ያቀረቡትን የዋይታ ጥሪ ሁኔታውን የበለጠ ያስታውሳልና በቃለ መጠይቁ መግቢያና በስተመጨረሻ አካተናል።