ንቧ ድፍት ኣለች!

tplf_nib_01

 Amdom Gebreslasie

እንደው ባለፈው ኣመት ህወሓት 40 ዋ ስታወጣ 2 ቢልዮን ብር ወጪ እንዳደረገች የምታስታውሱት ነው።

የዲያስፖራ ቀን በትግራይ ሲከበር 200 ሚልዮን ብር ወጪ፣ የኣርቲስቶች ጉብኝት፣ የከተሞች ቀለሞች መቀባት፣ የዜሮ ኣምፑል መብራቶች( ህዝቡ ዜሮ ኣምፑል መንግስት ያለው)፣ የካኪ ልብሶች፣ ድግሶችና ግዢዎች ወጪ ከ2 ቢልዮን እንዳወጣች በወቅቱ የተገለፀ ነው።

በወቅቱ የ38 ሚልዮን ኩንታል ከክረምት፣ 75 ሚልዮን ኩንታል ደግሞ ከመስኖ እርሻ እህል ተመረተ ብለው የተተረተሩበት ዓመት ተበር።

እያንዳንዷ ካድሬ፣ ልማታዊ ጋዜጠኛ፣ የሊግ፣ የማህበራትና የኣንድ ለ ኣምስት ኔትወርክ መሪ ሁላ ኣካኪ ዘራፍ እያለች የመለስ ራኢ ተሳካ እያለች ስታሽካካ ነበር።

እውነት እንኳን ድሃ ድህነት የሚል ቃልም ድራሹ የጠፋ ኣስመስለውት ነበር። ዳሩ ግን ያሁሉ ፕሮፖጋንዳ 4 ወር ሳይቆይ ለኣለም ማህበረሰብ በድርቅ ለተጠቃ ህዝብ እርዳታ በመለመን ኣስደነገጡን።

የለካቲት 11 በዓልና ያጋጠመው ድርቅ ኢህኣዴግ ልክ እንደ ሃይለስላሴና ደርግ ስርዓቶች የህዝብ ስቃይ፣ ርሃብ፣ ሞት የማይሰማው ግኡዝ መንግስት መሆኑ ያጋለጡበት ኣጋጣሚ ፈጥሮ ኣልፏል።

1) የጃንሆይ ልደትና የ67 ድርቅ

2) የደርግ ኢሠፖኣኮ ልደትና የ77 ድርቅ

3) ህወሓት ልደት የለካቲት 11ና ድርቅ 2007/8 በተመሳሳይ ምድብ ያጋልጣቸዋል።

ህወሓት ከ30 ዓመት በፊት ያና የሽምቅ ተዋጊ በነበረችበት ግዜ ራስዋ ወደ ማሌሊት ስታሸጋግር ለትግራይ ህዝብ እንድታከፋፍል የተሰጣት እርዳታ 95% ለመመስረቻ በኣል ድግስና ለጦር መሳርያ መግዣ እንዳዋለችው BBC እንደዘገበው የኣሁኑ የእርዳታ እህል ” ለኣባይ ግድብ፣ መጋዘን ሞላ” እየተባለ እየተሸጠ እንዳለ እየተነገረ ነው። ህወሓት በበረኻም በቤተ መንግስትም ሁና የህዝብ እርዳታ የመቀማት ልማዷ እንዳልተወች ነው።

ህወሓት ለኣርባዋ ብዙ ሽርጉድ ብላለች። ዝግጅቱ ኣንዱ ትልቅ ንብ ቀርፀው ተሽከርካሪ ነገር ሰርተው በቲዮታ መኪና እየጎተቱ በማዞር የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ ኣንዱ ተበር።

ታድያ ንቧ የጉዘዋ ግማሹ ከሄደች በኋላ ንግድ ባንክ ኣለፍ ብላ ሑመራ ሆቴል ኣጠገብ እኔ ወደ ነበርኩበት ስትደርስ ንቧ በኣፍ ጢሟ ድፍት ኣለች።

ንቧ ፊትለፊቴ ድፍት ስትል እኔን የሚል ኣንድም ሰው ኣልነበረም። ኣንዷ ተለቅ ያሉ ሴትዮ ” እንዴ ምን ነክቷት ነው ኣሁን በኣፍጢሟ የተደፋቹ…?” ይላሉ። ሌላኛዋ ደግሞ “ኣታዮ ክንደየን ዳ ኖኣኻ ትኾኖ”( እናንተዮ እንዴት ኣባትዋ ታክላለች) ሲሉ ነበር።

ጨዋታው ስያዳምጥ የነበረው ወጣት ” እቺስ ኣውራዋ ሙሰኛዋ ናት። እንዲህ የወፈረችው ሙስና በልታ በልታ መሆን ኣለባት” ሲል ቀለደባት።

ንቧ ፊትለፊቴ መጥታ ድፍት ኣለችና ተጎትታ ወደጎን ተወሰደች።

በመኪና የመጣቹ ንቢቱ ሰው ድሃ ይሁን ሃብታም ሲሞት በሶስት ሜትር ኣቦጀዲድ እንደሚገነዝ ጋሪ መጥታ ተገንዛ ተጭና ሄደች። እኔም ወደ ጋሪዋ ስጭንዋት ኣገዝኳቸው። ምክንያቱም በባህላችን ሬሳ ሲሸኝ የማታውቀው ቢሆን’ኳ ተሸክመህ መሸኘት ግዴታ ነው።

ቦታው ላይ የኣውራምባ ታይምስ ኣዘጋጅ ዳዊት ከበደ ነበረና ድፍት ያለችው ንብ ፎቶ ሲያነሳ ነበረ።

የንቧ ፊት ለፊቴ መጥታ በኣፍ ጢሟ ድፍት ማለት ግን ኣይገርምም……?

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *