Hiber Radio : በደቡብ ክልል በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ ለአባይ ቦንድ አንከፍልም ሲሉ ተቃውሞ ካሰሙ መምህራን መካከል አስራ አምስቱ ታሰሩ፣በተቃውሞው ሳቢያ ሁለት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል፣ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የኤርትራዊያን ስደት እንዲገታ ከተፈለገ የአስመራ መንግስት መወገድ አለበት ማለታቸው ቁጣ ቀሰቀሰ፣በተመድ የኤርትራ አመባሳደር ግርማ አሰመሮም <<የራሷ አሮባት>> ሲሉ የአቶ ሀይለማሪአምን ንግግር ማታታላቸው፣ በጎንደር ልዩ ልዩ አካባቢዎች ከአከላለል ጋር በተነሳ ግጭት የገበሬ ጦር ከአገዛዙ ሰራዊት ጋር ውጊያ መግጠሙ፣ሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ታጣቂ ተቃዋሚዎችን እየረዳች መሆኗ ተዘገበ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የታሰሩት የአለም ባንክ አሰተርጓሚ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ተጠየቀ ፣ስደተኛው ሲኖዶስ በአገር ቤት ያለው አገዛዝ ተቃዋሚዎችን <<አሸባሪ>> የሀይማኖት አባቶችንና ሰባኪያንን <<ተሃድሶ>> የሚል ስም እየለጠፈ የሚያደርገውን ውንጀላ አወገዘ፣ ዘጠኝ ተጨማሪ ጳጳሳት ሊሾም ነው ፣በመምህር ግርማ ዙሪያ ወቅታዊ ዘገባ፣የአርበኞች ግንቦት ሰባት የፊኒክስ- አሪዞና ስብሰባና ሌሎችም

hiber_cover_110815_1

የህብር ሬዲዮ  ጥቅምት 28 ቀን 2008 ፕሮግራም

<…የአቶ ሀይለማርያም ንግግር ከልብ ለውጥ ለማምጣት ነው ወይስ ዲስኩር ብቻ የሚለውን መመርመር ያሻል።ከልብ ለማድረግ የመፈለግ ምስል ሰጥቶ ለሰው፣ ሰው ያንን ይዞ ተስፋ እያደረገ ዕድል እንዲሰጣቸውና ያው የሚሳሱለት ስልጣን ላይ ለመቆየት ነው የሚለውን ጠጋ ብሎ መፈተሽ ያስፈልጋልነገሩ ግራ የሚያጋባው መቶ በመቶ ሕዝብ መርጦኛል ያለ ዛሬ ተመልሶ ሕዝብን አማረናል ሙስና ውሰጥ ተነክረናል ቢል የሕዝብ ድምጽ ለመዝረፍ ወደሁዋላ ያላለ ለቁሳዊ ነገር ይሳሳል ሌባው ሌባውን ያጋልጣል ተብሎ አይጠበቅም ። ምን አልባት እንደተባለው ንግግሩ የስርዓቱ ኑዛዜ ሊሆን ይችላል ወይም በፓርቲው ውስጥ ላለ የስልጣን ሽኩቻ ሙስናን እንደ ማጥቂያ…>

ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ የሰሞኑን የአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ንግግር ከእውነታው ጋር አገናዝቦ ተመልክቶታል (ሙሉውን ቃለ መጠይቅ አዳምጡት)

መምህር ግርማ ላይ ተጨማሪ የተጠረጠሩበት ክስ አስቀድሞ የነበረውን የዕምነቱን ተከታዮች ጥርጣሬ ያባብሳል? በእርግጥ መምህሩ የስርዓቱ ሰለባ ናቸው? የዕምነቱ ተከታዮች አወዛጋቢ የሁለት ጎራ አስተያየትና ወቅታዊውን ሁኔታ ቃኝተነዋል(ልዩ ዘገባ)

አርበኞች ግንቦት ሰባት በፊኒክስ ያደረገው ሕዝባዊ ስብሰባ እና የሕዝቡ ምላሽ (ልዩ ጥንቅር)

<…ኦህዴድ አመራር ሆነው ኦሮሞና የማይናገሩ አሉ። የዛሬው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የኦህዴድ አመራር ናቸው። በአንድ የኦህዴድ ጉባዔ ላይ አማርኛ ላለመናገር ከተናገሩ ስለሚሳቅባቸው ሁለት ሺህ ሰዎች ባሉበት ስብሰባ በእንግሊዝኛ ተናገሩ። የዘር ፖለቲካው የተዘራው በሕወሃት ሆን ተብሎ መጀመሪያ በዘር ቀጥሎ በጎሳ ዝቅ ሲል በሀይማኖት ሰው እንዲያስብ ሲገፋ ቆይቷል…ራሳቸው አቶ መለስ በ1979 ዓ.ም. በጻፉት የኤርትራ ሕዝብ ከየት ወዴት መጽሐፋቸው ወያኔና ሻዕቢያ እዛው በረሃ እያሉ የተጣሉት የሻዕቢያ መሪዎች እነ አቶ ኢሳያስ ወያኔዎችን ለኢትዮጵያ የዘር ፖለቲካ አይጠቅምም በዘር ፖለቲካ አትክፈሉ ስላሏቸው መሆኑን ራሳቸው መስክረዋል…> አቶ ኤርሚያስ ለገሰ በፊኒክስ -አሪዞና በአርበኞች ግንቦት ሰባት ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከተናገሩት (ቀሪውን ያዳምጡት)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በደቡብ ክልል በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ ለአባይ ቦንድ አንከፍልም ሲሉ ተቃውሞ ካሰሙ መምህራን መካከል አስራ አምስቱ ታሰሩ

በተቃውሞው ሳቢያ ሁለት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል

አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የኤርትራዊያን ስደት እንዲገታ ከተፈለገ የአስመራ መንግስት መወገድ አለበት ማለታቸው ቁጣ ቀሰቀሰ

“የአቶ ሃይለማሪያም ንግግር የራሷ አሮባት የሰው ታማሰላለች ነው የሆነብኝ ”ሲሉ በተመድ የኤርትራ አመባሳደር ግርማ አሰመሮም ተናገሩ

ሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ታጣቂ ተቃዋሚዎችን እየረዳች መሆኗ ተዘገበ

ኢትዮጵያ በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ አመሪቂ የጥናት ውጤት አለተገኘም ስትል አቁሟን ይፋ አደረገች

በጎንደር ልዩ ልዩ አካባቢዎች መብታችንን አናስነካም ያሉ የቅማንት ተወላጆች ከአገዛዙ ጦር ጋር ውጊአ ገጥመው ሙትና ቁስለና ማድረጋቸውን ገለጹ

በኢትዮጵያ ውስጥ የታሰሩት የአለም ባንክ አሰተርጓሚ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ተጠየቀ

“ግለሰቡ ባስቸኳይ ካለተፈቱ የሕይወታቸው መጨረሻ የኢትዮጵያ ወህኒ ቤት ይሆናል”ስጋት የገባው የሰባዊ መብት ተሟጋች ድርጅት

ስደተኛው ሲኖዶስ በአገር ቤት አለው አገዛዝ ተቃዋሚዎችን <<አሸባሪ>> የሀይማኖት አባቶችንና ሰባኪያንን <<ተሃድሶ>> የሚል ስም እየለጠፈ የሚያደርገውን ውንጀላ አወገዘ

ዘጠኝ ተጨማሪ ጳጳሳት ሊሾም ነው

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8፡30  ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በአውስትራሊያ 0280725172  በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-110815-111515

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *