Hiber radio: የበጎች መንጋ ግዙፉ የመጓጓዣ አውሮፕላንን በድንገት እንዲያርፍ አሰገደዱት

air_plan_02

በታምሩ ገዳ

ንብረትነቱ የሲንጋፖር አየር መንገድ የሆነ አንድ የእቃ ማጓጓዣ አውሮፕላን በውስጡ ጭኖ የነበረውን በረካታ በጎች ይዞ በረራውን አቁርጦ ለሰዓታት እንዲያርፍ ተገዷል። አቪዮሽን ሀራልድ የተሰኘው ድህረ ገጽ እንደዘገበው ከሆነ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሰማኒያ ስደሰት (2186) በጎችን ጭኖ መነሻውን ከ ሲዲኔ( አውስትራሊያ )አደርጎ ወደ ኳላላምፑር (ማሊዢያ) ይበር የ ነበረው የማጓጓዣ አውሮፕላን በበረራ ላይ እንዳለ ከጭስ አነፈናፊው (ስሞክ ዲክተክቶር ) መሳሪያ ላይ ያለተለመደ የጭስ ምልክት የታያል ።ፓይለቶቹም አውሮፕላኑን ወዲያውኑ በድንገተኛ እንዲያርፍ አድርገው መንሰኤው ሲጣራ በውስጡ ምንም አይነት እወነተኛ የእሳት ዘር (ጭስ) አለተገኝም። ለዘመናዊ ቴክኖሎጂ ምስጋና የገባውና በሁዋላ ሰለ ጭሱ መንሰኤ ሲጣራ እንዚያ ለመታረድ ይሁን ለመራባት ወደ ሲንጋፖር ሲጓጓዙ የነበርቱት በጎች “ከረጅም ጉዞ ሳቢያ ፣ ሲያመነዥጉት ከነበረው ግሳት ፣ ከተጸዳዱት (በጠጣቸው) አና በመጸዳጃቸው ካሰወገዱት ከተቃጠለው አየር (ፈስ) የወጣ ጋዝ ለካ ወደ ጭስ መመረመሪያዋ ማሽን ዘልቆ የእሳት አደጋ መመረመሪያውን አስጨንቆ እና አሰጠንቅቆ አውሮፕላኑም በአደጋ ጊዜ እንዲያርፍ ተገዷል “ ሲሉ የአየርመንገዱ ባለሰልጣናት ግምታቸወን የሰነዘሩ ሲሆን በተለይ ደግሞ የእንሰሳ ባለሙያዎች በጎች ሲደክማቸው የተቃጠለ አየር(ጋዝ) በብዛት ያሰወጣሉ ብለዋል። አሮፕላኑም ከሁለት ሰእት ተኩል የድንገተኛ ማረፍ በሁዋላ መንገዱን በማቅናት ከመዳረሻው(ኳላላምፑር) በሰላም ደርሷል ተብሏል። ከዚህ ቀደም ሌላ የሲንጋፖር አየርመንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን ባለፈው ነሃሴ ወር ወስጥ ከግሪሳ ወፎች ጋር ተጋጭቶ በድንገት ለማረፍ ተገዷል። መቸም ጥንቃቄ ማድረግ ባይከፋም በሰንካላ ምክንያት አውሮፕላኖች እንዲያርፉ ሲገደዱ ማየት እየተለመደ የመጣ ጉዳይ ሲሆን በተለይ ከሽብር ጋር በተያያዘ ብዙ ሰዎች በምርመራ ሰም ይያዛሉ አሊያም ከመንገዳቸው ይደናቀፋሉ። ይሁን እና ሰሞኑን ግዙፉ አወሮፕላንን በማሰደንገጥ በደንገት እንዲያርፍ ያደረጉት የበጎቹ እጣፈንታ (በቀጥታ ወደቄራ ሰለመላካቸው ወይም ወደማጎሪያ ቤታቸው ሰለመላካቸው ) ለጊዜው አልታወቀም

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 እና በአውስትራሊያ 0280725172 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *