Hiber radio: ዶ/ር አክሎግ ቢራራ በኢትዮጵያ ውስጥ መታተም ያልቻለውን አዲሱን <<ድርጅታዊ ምዝበራ >> መጽሐፋቸውን በአገር ቤት እንዲነበብ በኢንተርኔት በነጻ ለቀቁት

Dr_Akelog_book_cover_front_001

የቀድሞ የኣለም ባንክ የኢኮኖሚ አማካሪና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ጥናታዊ ጽሑፎችን በማቅረብ የሚታወቁት ዶ/ር አክሎግ ቢራራ በአሜሪካን አገር ታትሞ በአማዞን ላይ ዛሬም ድረስ በ22.44 ዶላር ሚሸጠውን <<ድርጅታዊ ምዝበራ የኢትዮጵያ<<እድገታዊ መንግስትና>> የስልጣን ባለጸጋዎች ኢኮኖሚ የተሰኘውን መጽሐፍ በአገር ቤት እንዲነበብ ለማድረግ ለማሳተት ያደረጉት ጥረት መቶ ሺህ ብር ጭምር አሳጥቷቸው ያልተሳካ ቢሆንም በኢንተርኔት አማካይነት በነጻ እንዲነበብ በዛሬው ዕለት መፍቀዳቸውን የመጽሐፉን ቅጂ በመላክ ለህብር ሬዲዮ ገለጹ።

ዶ/ር አክሎግ አስቀድሞም በኢትዮጵያ ለማሳተት የታሰበው በአነስተባ ዋጋ ተሽጦ ያሳተሙት ወገኖች ተጠቃሚ ሆነው ነገር ግን ወጣቱ ትውልድ በአገሩና በሕዝቡ ላይ የሚፈጸመውን ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ፣የተደራጀው የአገሪቱ ሀብት ዘረፋና በሙስና የማይጠየቀው ሀይል በስልጣን መዳድሉ ላይ መኖር፣ አገሪቱ እየገባችበት ያለው አጣብቂኝ፣ስር የሰደደ ድህነትና ከዚህ አስከፊ ሁኔታ ለመውጣት ሚቻልባቸው ዝርዝር በጥናት ላይ የተመሰረተና በመረጃዎች የበለጸገው ይሄ መጽሐፍ በአገር ቤት ተነባቢ ለማድረግ ያላሰለሰ ጥረት እንደሚአደርጉ ከዚህ ቀደም ለህብር ሬዲዮ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ መግለጻቸው ይታወሳል።

የዶ/ር አክሎግ ቢራራን ሙሉውን መጽሐፍ ለማንበብ የፒዲኢፍ ፋይሉን ይክፈቱ ወደ አገር ቤት በወዳጆችዎ አማካይነት ያሰራጩ።

DR Akelok_Birara_book_relased_ድርጂታዊ ምዝበራ

ድርጂታዊ ምዝበራ.doc

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *