በታምሩ ገዳ
ከወሊድ ጋር በተያያዘ የሚሞቱ የኢትዮጵያ እናቶች እና ጨቅላ ህጻንታን ቁጥር ለመቀነሰ ይረዳ ዘንድ አንድ የሰካንዲቪያን አገር ኩባንያ ኢትዮጵያ ውስጥ የሙከራ ሰራ እያካሔደ መሆኑ ታውቀ። የፈርንሳዩ የዜና አገልግሎት አጃንስ ፍራንስ ፕሪስ )በትላንትናው እለት (እሮብ ) እንደዘገበው ከሆነ የወላዶች ድርጅት (Maternitity Foundation ) የተሰኘ የዴንማርክ የልማት ትራድኦ ግብረሰናይ ድርጅት ኢትዮጵያዊያን አዋላጆች ነፈሰጡሮችን ለማዋላድ ሲሉ የሚደረሰባቸውን ከአቅም በላይ የሆነ አሰራርን የሚያቀል በተንቀሳቃሽ ሰልክ አማካኝነት የሚያሰረዳ ጤናማ የማዋልጃ ዘይቤ ወይም (Safe Delivery App) የተሰኘ አዲስ የፈጠራ ሰራ በመተግባር ላይ መሆኑን አሰታውቋል። አዲሱ የምሰል አገልገሎት በወሊድ ጊዜ ብዙ ደም የሚፈሳቸው እናቶችን ፣የመተንፈስ ችግሮች የሚገጥማቸው አዲስ ህጻናት እና በኢንፌክሽን የመሳሰሉት አደጋዎች ላለመጠቃት አዋላጆች ምን አይነት ቀደም ተከተል መከተል እንዳለባቸው በማሰተማር ረገድ ጉልህ ሜና የጫወታል ተብሏል። ከአንድ አመት በፊት በምእራብ ኢትዮጵያ፣ ወለጋ(ጊምቢ) ውስጥ ለሙከራ ለነፈሰጡር ሴቶች እዋላጆች የታደለው 78 የ ተንቀሳቃሽ ሰልክ የተጠቃሚው ቁጥር የጨመረ ሲሆን በወሊድ ጊዜ የደም ፍሰትን መጥን መቆጣጠርን በተመለከተ ከ 20 ከመቶ ወደ 60 ከመቶ ከፍ ሊል ችሏል በማለት አቶ መሰፍን ወንዳፍራሽ የተባሉ የገብረሰናይ ድርጅቱ የአፍሪካ ቀንድ ተጠሪ ለ ዜና ወኪሉ ገለጸውለታል።
የቅርብ ጊዜያትጥናቶች ኣንደሚገልጹት ከሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ ከ 10 ነፍሰጡሮች ውስጥ 9ኙ በቤ ታቸው ውስጥ በልምድ አዋላጆች ሕጻናትን የሚገላገሉ ሲሆን አብዛኞቹ እናቶች ተግቢውን የሕክምና አገልግሎትን አያገኙም።አዲሱ የተንቀሳቃሽስ ስልክ የማዋለጃ መረጃ ከከተማ አልፎ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ከወሊደ ጋር በተያያዘ ህየወታቸውን በቀላሉ ለሚያጡት ነፍሰ ጡር እናቶች መልካም ዜና ሲሆን በተለይ ደግሞ የመርጃ ፍልሰቱ በእንግሊዘኛ እና በአካባቢያዊ ቋንቋዎች መሆኑ ብዙ ወጣውረዶችን ይቀነሳል ተብሎ ይገመታል። ከወሊድ ጋር በተያያዘ በአንዳንድ የኢትዮጵያ ክፍሎች ብዛት ያላቸው አናቶች ልጆቻቸውን ሳያዩ ይሞታሉ ተብሏል። ሌላ ከወሊድ ጋር በተያያዘ ዜና ኢትዮጵያ ውስጥ ለወትሮው በአማካኝ እሰከ ሰባት ሕጻናት የሚወልዱ እናቶች በአሁኑ ወቀት ቁጥራቸው ወደ 4.6 ዝቅ ማለቱን የተባበሩት መንግስታት የሕዝቦች ተቋም በቅርቡ ይፋ አድርጓል። ለዚህ ምክንያቶቹ ከተባሉት ውስጥ ብዙ ሴቶች የእርግዝና መቆጣጠሪያ መደሃኔት ተጠቃሚዎች በመሆናቸው ፣ ሴቶች ከማጀት የመውጣታቸው ጉዳይ ተጠቃሽ ሲሆን የኑሮ ውድነቱ በተለይ ደግሞ በከተሞች አካባቢ ልጅ የወለድ እንጂ በእድሉ ያድጋል የሚለው ብሄል “የምበላው ሳጣ ልጄ ጥርስ አወጣ” ወደ ሚለው ዘመናዊ አባባል ሰለተቀየረባቸው ነው ተብሏል ።
የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 እና በአውስትራሊያ 0280725172 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።