Hiber Radio ፡በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ ከተፈጥሮ ችግር ባሻገር የመልካም አስተዳደር እጦት ውጤት ጭምር መሆኑን ምሁራኖች ገለጹ፣ የኢትዮጵያው አገዛዝ ስኳር ለውጭ ገበያ ላቀርብ ነው ማለቱ አነጋጋሪ ሆነ፣ የግብጽ የጸጥታ ሀይሎች የበርካታ ስደተኞችን አስከሬን ከበረሃ ውስጥ ወድቆ ማግኘታቸውን ገለጹ ፣ በረዳት አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ላይ በኢትዮጵያ የተከፈተበት ክስ እንዲቋረጥ ወንድሙ ጠየቀ ፣ እና ቃለ መጠይቅ ከዶ/ር አክሎግ ቢራራ ጋር እና ሌሎችም አሉን

ጋዜጠኛ ሐብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሐብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ህዳር 5 ቀን 2008 ፕሮግራም

<…ኢህአዴግ ስልጣን ላይ ከወጣ ቢያንስ አምስት ረሃብ ተከስቷል ።የተስተካከለ አስተዳደር ለአገርና ለሕዝብ የሚያስብ ስላልሆነ የስርዓት ለውጥ እስካልመጣ የዛሬ አምስት ዓመትም ረሃብ አይቀርም ። ለህሊናዬ ስል ለወገኖቼ ለረሃቡ ለመድረስ አዋጣለሁ እንጂ መፍትሄው የስርዓት ለውጥ እንጂ ብልሹ አስተዳደር የፈጠረው ረሃብ በየጊዜው አይቀርም… የትኛው ሀገር ነው ለም መሬቱን ለባዕዳን በርካሽ ሸጦ ምርቱ እየተጫነ እየወጣ ለራሱ ከውጭ እህል እገዛለሁ የሚል? የትም የለም…>   ዶ/ር አክሎግ ቢራራ የወቅቱን ረሃብና የስርዓቱን ሁኔታ በማስመልከት ካደረግንላቸው ሰፋ ያለ ቃለ ምልልስ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

<<…ለወገኖቻችን ለመድረስ በራሳችን ተነስተን <ቤዛ እንሁን > ብለን የዕርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ አቐቁመናል። ይህን ለማድረግ የመንግስት ፈቃድ አያስፈልገንም ። መንግስት ከአገርና ከወገን በላይ ሊሆን አይገባም ።ማንም ሰው በረሃብ እየሞተ ላለ ወገኑ መድረስ አለበት።ኢህ ካልሆነ ግን…>>

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ የ<ቤዛ እንሁን> ለድርቁ ተጎጂዎች ለመድረስ የተቋቋመው ኮሚቴ ሊቀመንበር ጋር የተደረገ ቆይታ(ሙሉውን ያዳምጡት)

የኔቫዳ ትርንስፖርት ባለስልጣን ለህብር ሬዲዮ ጥያቄዎች ሰጠው ምላሽ (ልዩ ጥንቅር )

የፈረንሳዩ የአሸባሪዎች መጠነ ሰፊና የተቀናጀ ጥቃት ከ130 በላይ ሰላማዊ ሰዎች ህይወት ቀጥፏል።ከሁለት መቶ በላይ ቆስለዋል።ፓሪስ እምዴት ሰነበተች? የዐይን እማኞች፣የጥቃቱ አራማጆች እና የዓለም መሪዎች ምን ይላሉ(ልዩ ጥንቅር)

በቻርሎቴ የተደረገው የአርበኞች ግንቦት ሰባት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት (ቃለ መጠይቅ)

 

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ ከተፈጥሮ ችግር ባሻገር የመልካም አስተዳደር እጦት ውጤት ጭምር መሆኑን ምሁራኖች ገለጹ

የኢትዮጵያው አገዛዝ ስኳር ለውጭ ገበያ ላቀርብ ነው ማለቱ አነጋጋሪ ሆነ

የግብጽ የጸጥታ ሀይሎች የበርካታ ስደተኞችን አስከሬን ከበረሃ ውስጥ ወድቆ ማግኘታቸውን ገለጹ

በረዳት አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ላይ በኢትዮጵያ የተከፈተበት ክስ እንዲቋረጥ ወንድሙ ጠየቀ

በአገር ቤት ዜጎች በድርቅ ሳቢያ በርሃብ የሚሞቱ ወገኖቻቸውን ለመርዳት በግላቸው ቤዛ እንሁን ሲሉ ኮሚቴ አቋቁመው እንቅስቃሴ ጀመሩ

ለርሀቡ ትኩረት አልተሰጠም በመቀሌ ለብአዴን 35ኛ ዓመት ታላቅ የሙዚቃ ድግስ ተደረገ

በኢትዮጵያ የሚገኙ ራስ ተፈሪያውያን አገሪቷ የጠበቋት የተስፋይቷ ምድር አልሆነችልንም ሲሊ አገዛዙን አማረሩ

የታክሲና ሊሞ አሽከርካሪዎች ሁበርን ጨምሮ ለሌላ ኩባንያ እንዳያሽከረክሩ የሚከለክል ሕግ የለም

የታክሲ ኩባንያዎች ሊዝ ለመስጠት ለመስተት የሚያስችላቸው የሕግ ረቂቅ ላይ ውይይት ሊደረግ ነው

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8  ሰዓት ህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-111515-112215

One Comment on “Hiber Radio ፡በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ ከተፈጥሮ ችግር ባሻገር የመልካም አስተዳደር እጦት ውጤት ጭምር መሆኑን ምሁራኖች ገለጹ፣ የኢትዮጵያው አገዛዝ ስኳር ለውጭ ገበያ ላቀርብ ነው ማለቱ አነጋጋሪ ሆነ፣ የግብጽ የጸጥታ ሀይሎች የበርካታ ስደተኞችን አስከሬን ከበረሃ ውስጥ ወድቆ ማግኘታቸውን ገለጹ ፣ በረዳት አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ላይ በኢትዮጵያ የተከፈተበት ክስ እንዲቋረጥ ወንድሙ ጠየቀ ፣ እና ቃለ መጠይቅ ከዶ/ር አክሎግ ቢራራ ጋር እና ሌሎችም አሉን”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *