በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ዛሬም ረሃቡን ለመደበቅ ሬሳ እስከመግረፍ ይሄዳል። ረሃብ ቀን አይሰጥም ለወገናችን እንድረስ ያሉ በአገር ቤት የሚገኙ አስራ ሶስት ግለሰቦች ብዙዎቼ ጋዜጠኞች ናቸው ለወገን ደራሽ ወገን ነው በሚል ኮሚቴ አቋቁመው <<ቤዛ እንሁን!>>ብለው ተነስተዋል።የባንክ ሒሳብ ከፍተው ጥሪ አቅርበዋል።በረሃብ ለሚሞተውና በዚህ ሰቀቀንና ሰቆቃ ውስጥ ላለው ወገን ከመድረስ ይልቅ ስለ ረሃቡ መጋለጥ የሚአስጨንቀው ስርዓት አስፈሪውን አደጋ ለመከላከል የበኩላችንን እናድርግ ያሉትእ እነዚህን ወጣቶች ያሰራቸዋል? ከኮሚቴው ሊቀመንበር ጋዜጠኛ ኤልአስ ገብሩ ጋር አጭር ቆይታ አድርገናል። የኮሚቴው የባንክ ቁጥር እነሆ፤-Commercial Bank of Ethiopia Arada Ghiorgis Branch
Account No – 1000143645987
Swift Code – CBETETAA “ቤዛ እንሁን!”