Hiber Radio: የአረና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ በአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ በቤንሻንጉል የሚደረገው ጭፍጨፋ እንዲቆም ጠየቀ

Amehara_displaced_killed_in_beneshanegul_001

በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ በሚያራግበው ዘረኛ ብሄርን ከብሄር ሐይማኖትን ከሀይማኖኢ የሚያጋጭ ፖሊሲ ሳቢአ በአገር ቤት በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ በቤንሻንጉል ጉምዝ የሚደረገው ጭፍጨፋ አሳዛኝና ስርዓቱ ሀላፊነቱን በመውሰድ ጭፍጨፋውን ሊያስቆም እንደሚገባ የአረና የሕዝብ ግንኑነት ሀላፊ ጠየቀ።

አምዶም ገ/ስላሴ ሁኔታውን አስመልክቶ ዛሬ ማምሳውን በፌስ ቡክ ገጹ ባወጣው ጽሁፍ ይህን ዘግናኝ በመቃወም <<ጭፍጨፋው ይቁም ሲል ጠይቋል።

የአረና የህዝብ ግኑኙነት ሀላፊ አምዶም ገ/ስላሴ ጽሑፍ ከዚህ በታች እንድታነቡት አያይዘነዋል።

ጭፍጨፋው ይቁም……!!!

በአምዶም ገ/ስላሴ በኣማራ ብሄር ተወላጅ ወገኖቻችን በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል እየደረሰባቸው ያለው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ኣጥጥብቄ እኮንናለው።

ይህ ዜጎች ባገራቸው ይህ የመሰለ ጭፍጨፋ መካሄዱ እጅጉን የሚያሳዝንና የሚያሳፍር ሰብኣዊነት የጎደለው ተግባር ነው።

መንግስት ለዚህ ኣስደንጋጭና ዘግናኝ ተግባር ሃላፍነት በመውሰድ ወንጀሉ በኣስቸኳይ እንዲያስቆመውና ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ ኣለበት እላለው።

ዜጎቻችን በስደት ሳውዲ ዓረብያ፣ የመን፣ ደቡብ ኣፍሪካ፣ ሊብያ፣ ደቡብ ሱዳንና ቤሩት የመሳሰሉ ሃገራት፤ በቀይ ባህር፣ ሜድትራንያን ባህር፣ በሲናይና ሰሃራ በረሃዎች እየደረሰባቸው ያለው መቅዘፍት ሳይበቃ በገዛ ሃገራቸው ይህን የመሰለ ሰቅጣጭ ጭፍጨፋ ሊደርስባቸው ኣይገባም።

ሃገራችን 15 ማልዮን በኣስከፊ ረሃብ በተያዘበትና ሂወቱ እያጣበት ባለበት ግዜ ይህን መሰል ወንጀል መፈፀሙ የሚዘገንንብቻ ሳይሆን የሚያሳፍር ወንጀል ነው።

ብኣዴንም እወክለዋለውና ኣስተዳድረዋለው የሚለው ህዝብ ኣስከፊ ወንጀለ እየተፈፀመበት እያየ የሰው መሰውያ እንደለመደ ጣኦት ምንም ሳይል ደማቅ በዓል እያሳለፈ መሆኑ ያስገርማል።

የኢህኣዴግ መንግስትም እንደዚህ ዓይነቶች ወንጀሎች የሚፈፅሙ ወንጀለኞች ይዞ ለፍርድ የማያቀርብ ከሆነ ኣስፍኘዋለው የሚለው ሰላም ከመደፍረሱ በላይ የወንጀሉ ተባባሪና ቁጥር ኣንድ ተጠያቂ ያደርገዋል።

መንግስት ወንጀለኞች ባስቸኳይ ለህግ ያቅርብልን ! ‪#‎ETHIOPIA_FAMINE ‪#‎ክፉ_ቀን ‪#‎ዘበን_ኣካሒዳ

‪#‎ነፃነታችን_በእጃችን_ነው።

It Is So…!

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 እና በአውስትራሊያ 0280725172 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *