Hiber Radio ፡ በሊቢያ በግፍ ለተገደሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን እጁ ያለበት ያሸባሪዎች መሪ አሜሪካ በወሰደችው ጥቃት ሳይገደል እንዳልቀረ ተገለጸ፣ በኢትዮጵያ የተከሰተውን አስፈሪ የረሃብ አደጋን ስፋት አገዛዙ ለመደበቅ መሞከሩ ተዘገበ፣ የኢትዮ-ኬኒያ ድንበር ወታደራዊ ውጥረት አይሏል፣ኢትዮጵያ የድንበር ኬላዎቿን ዘጋች፣ 3 የኢትዮጵያ 4 የኬኒያ ወታደሮች መሞታቸውን የኬኒያ ጋዜጣ ዘገበ፣የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ህመም ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑና ዛሬም ሕክምና እንዳልተፈቀደለት ተገለጸ፣በቬጋስ የሁበርና ሊፍትን ተወዳዳሪነት ለማርገብ በርካታ አዲስ ታክሲ ለኩባንያዎች ተጨመረ እና ቃለ መጠይቅ ከዶ/ር ኑሩ ደደፎ የኦነግ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ ጋር እና ሁበር ሲያሽከረክር ጥቃት ከደረሰበት ኢትዮጵያዊ ጋር ውይይት እንዲሁም ሌሎችም አሉን

habtamu4

የህብር ሬዲዮ ህዳር 12 ቀን 2008 ፕሮግራም

<…ወያኔ በጉልበት ያለፈው ዓመት ተግባራዊ ለማድረግ የሞከረውንና ያልተሳካለትን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ዛሬ በህግ ስም የኦሮሚያ ከተሞች አስተዳደር ሕግ በሚል የኦሮሚያ /ቤት እንዲያወጣ አድርጎ ለወያኔና ለአባሎቹ የኦሮሞን መሬት ለመንጠቅ ነው። ይሄ ደግሞየኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከስርዓቱ ጋር እንጂ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ችግር የለበትም ።የወያኔ ስርዓት ለመኖር የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም ።ሕዝቦችን ከሕዝቦች ጋር ለማጋጨት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ይሞክራል ራሱ አጣልቶ ገላጋይ ልሁን ይሆናል።ለዚህ ሕዝቦች መጠንቀቅ አለባቸው…> / ኑሩ ደደፎ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የውጭ ጉዳይ ሀላፊ በቅርቡ የኦሮሞ ድርጅቶች አድርገውት የነበረውን ውይይት አስመልክቶ ካደረግንላቸው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

<…ሁበር ከሁለት ዓመት በላይ ሰርቻለሁ። እንዲህ አይነት አደጋ ያጋጥመኛል ብዬ አላሰብኩም። ሰውዬውን ጭኜ ወደመኖሪያው ነበር የወሰድኩት በመንገድ ላይም ስናወራ የነበረው ወሬ ያው የተለመደ አይነት ነበር ቦታው ሲደር ግን ያልጠበኩትን ንግግር መናገር ጀመረ።ሙስሊም መስዬው እንደሆነ ነገር ግን ሙስሊም ባልሆንም ሁሉም ሙስሊም ለዚአ ተጠያቂ እንዳልሆነ በጽሞና ለማስረዳት ለማረጋጋት ሞከርኩ። ሀይለ ቃል መናገር እንደውም ከመኪና እንድወርድ መጠየቅ ጀመረ .. በወቅቱ ሲያደርግ የነበረው እኔን ለማናደድና በግጭት ውስጥ ለማስገባት ነበር።እንዲህ ሲሆን መታገስና ሁኔታውን ለማረጋጋት ሞክሬያለሁ በሁዋላ ግን አልወርድም ብሎ ወደፊት ለመሄድ ስሞክር ደጋግሞ ጭንቅላቴ ላኢ መታኝ…> አቶ ዳንኤል /ሚካኤል ከቻርሎቴ ኖርዝ ካሮላይና ሁበር ሲያሽከረክር በጥላቻ ከተሞላ ተሳፋሪ ጋር የገጠመውን ጥቃት በተመለከተስለ ሁኔታው ከሰጠን ማብራሪአ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

የኢትዮጵያው አገዛዝን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ አምባገነኖች ከዓለም አቀፉ የወንጀለኛ ፍርድ ቤት ለማምለጥ የሚያደርጉት ሙከራ (ልዩ ጥንቅር)

በቬጋስ በሁበርና ሊፍት አሽከርካሪዎች ላይ ጫና ለመፍጠር የሚደረግ የከተማዋ አስተዳደሮች ሩጫ እና የቀድሞ የፍሪያስ አሽከርካሪዎች የስራ አጥ ኢንሹራንስ ክርክር ለግልግል ዳኝነት የተሰጠውን ቀጠሮ አስመልክቶ የተደረገ ውይይት(ሙሉውን ያዳምጡ)

የአርበኞች ግንቦት 7 በሳን ሆሴ የተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ ለነጻነት ትግሉ የኢትዮጵያውያን ምላሽ (ቃለ መጠይቅ ከዝግጅቱ አስተባባሪዎች ጋር)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በሊቢያ በግፍ ለተገደሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን እጁ ያለበት ያሸባሪዎች መሪ አሜሪካ በወሰደችው ጥቃት ሳይገደል እንዳልቀረ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የተከሰተውን አስፈሪ የረሃብ አደጋን ስፋት አገዛዙ ለመደበቅ መሞከሩ ተዘገበ

የኢትዮኬኒያ ድንበር ወታደራዊ ውጥረት አይሏል፣ኢትዮጵያ የድንበር ኬላዎቿን ዘጋች

3 የኢትዮጵያ 4 የኬኒያ ወታደሮች መሞታቸውን የኬኒያ ጋዜጣ ዘገበ

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ህመም ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑና ዛሬም ሕክምና እንዳልተፈቀደለት ተገለጸ

በረሃቡ ሳቢያ ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉና በጎዳና ለልመና የተጋለጡ አርሶ አደር ኢትዮጵያውያን አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ቁጥራቸው እያደገ ነው

የመኢአድ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አብርሃም ጌጡን ጨምሮ በተለያዩ እስር ቤቶች ቁጥራቸው በርካታ የድርጅቱ አባላት በእስር ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑ ተገለጸ

የሎስ አንጀለስ ፖሊስ አንድ የቀድሞ የኢትዮጵያን መኮንን አፋልጉኝ አለ

በቬጋስ የሁበርና ሊፍትን ተወዳዳሪነት ለማርገብ በርካታ አዲስ ታክሲ ለኩባንያዎች ተጨመረ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-112215-112915

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *