በታምሩ ገዳ
በአሜሪካን አገር በቴክሳስ ግዝት ዳላስ የ መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ የነበርው የ 14 አመቱ አህመድ መሃመድ ባለፈው መስከረም 14 2015ን ውስጥ ለትምህርት ቤቱ የምርመር ግባት ይሆን ዘንድ የሰራው የፍጠራ የግድግዳ ሰአት በመመህራኖቹ ዘንድ “ቦምብ ነው” የሚል ጥርጣሬ ነግሶ ለእስራት መዳርጉን ተከትሎ የ ታዳጊው አህመድ እስራት ጉዳይ ከ ምድረ አሜሪካ አልፎ በአለም ዙሪያ በሚገኙ የፈጠራ ስራ አደናቂዎች እና በተለይ ደግሞ በሙስሊሙ ማህበረስብ ዘንድ አህመድ የታሰርው የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ በመሆኑ ብቻ ነው የሚል ክርክር እና ከፍተኛ የመነጋገሪያ ርእስ ፈጥሮ መቆይቱ ይታወሳል።የአሜሪካ የሙስሊም ጉባኤ አሕመድን የአመቱ ታላቅ ሙስሊም ሲል መርጦታል።
ታዲያ ይህ በርካታ የአለማችን የዜና እውታሮች ሳይቀሩ የወሬ ማጣፈጫቸው የሆነው ፡የአለም ታላላቅ መሪዎች ፕ/ት ባራክ ኦባማ፣ የሱዳኑ ፕ/ት ኡማር አልባሽህር ፣ ጉግል ደሀረገጽ እና የተባበሩት መንግስታት በክብር እንግድነት ያስተናደዱት ፣ የ ፊስ ቡክ መሰራች ማርክ ዙካርበረገር እና የተለያዩ የፖሊቲካ መሪዎች ሳይቀሩ አደናቆታቸውን የቸሩት አህመድ ቤተሰቦች ባለፈው ሰኞ አሳሪዎቹ የሆኑት የቴክሳስ ከተማ ፖሊስን በ10 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ እና ይማርበት የነበረው እና የተሳሳተ መርጃውን ለፖሊስ ያቀበለው የኢርቪንግ መለሰተኛ ደርጃ ት/ቤትን በ5 ሚሊዮን ዶላር የሞራል ካሳ እና ኦፊሲላዊ የሆነ የቅርታ እንዲጠይቁት የቤተሰቦቹ ጉዳይን የያዘው ጠበቃ ሰኞ እለት በደብዳቤ አሳውቋል።
እንደ የክስ አቤቱታው መሰርት ከሆነ የ9ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው አህመድ በቤቱ ውስጥ ለምርምር ክፈለ ጊዜ ብሎ ከወዳደቁ ቁሶች የሰራውን የግድግዳ ላይ ሰአት ወደ ት/ቤት ይዞ በመሔድ ለእንድ መምህሩ ያለ አንዳች ችግር ያሳየ ሲሆን በመለጠቅ ለእንግሊዘኛ ቋንቋ መመህሩ ለማሳየት ሲሞክር ከመመህርቷ ሞገሳ እና ውደሴ የጠብቅ የነበረው ታዳጊው አህመድ በተቃራኔው መመህርቷ ሰአቱን ከ “ቦምብ ጋር በማመሳሰል “ በተሳሳተ ኣና በተንሸዋረረ መንፈስ ሰእቱን ከጠረጲዛ ላይ በማሰቀመጥ ለፖሊስ ሪፖርት በማደረጓ ታዳጊው እህመድም ያለ ሕግ አግባብነት በፖሊስ ታጅቦ ከክፍሉ እንዲወጣ ተደርጓል፣ ታስሯል፣ ያለወላጆቹ ፍቅድ/በአካል ሳይገኙ) በ 5 የፖሊስ ጓዶች ምርመራ ተደርጎበታል፣ በምርመራው ወቅትም ወላጆቹን እንዳያነጋግር እገዳ ተደርጎበታል፣ያለ እውቅናው ም“የውሸት ቦምብ አምጥቻለው” ብሎ እንዲፈረም(ኣንዲናዘዝ ) ካለሆነ ከት/ቤቱ እንደሚባረር በት/ቤቱ ዳይሬክተር ግፊት እና ጫና ተደርጎበታል፣ታዳጊው ህጻንም ከደረሰብት እንግልት እና ወከባ ሳቢያ ለሰነልቦና ችግሮች ተዳርጓል የሚሉ ሰሞታዎች የተካተቱበት ሲሆን አሳሪዎቹ ፖሊሶች ሆኑ መረጃውን ያቀብሉት የቀድሞው የ አህመድ ት/ቤት ባለሰልጣናት የተጠየቀውን 15 ሚሊኦን ዶላር በመጪው 60 ቀናት(ሶስት ወራት) ውስጥ ካልከፈሉ በአሜሪካ የግለሰቦች መብት(የሲቪል ራይት ) መሰርት የሕግ ግድፈት ያለበት በመሆኑ ክሱንለፍርድ ቤት ማቅርብ ተገቢ መሆኑን ገልጸዋል።የኢርቪንግ ክፈለ ከተማ ከነቲባ ቤትዝ ቫን ዳይኔ በወቅቱ ለዜና ሰዎች በሰጡት አሰተያየት “አህመድ ወደ ት/ቤት ይዞ የመጣው ሰኣት ሳይሆን የውሸት ቦምብ ነው፣ እኛ ለህጻናት ደህነነት ኣንቆማለን ፣ ለጋዜጠኞች የተናገርውን ያህል ለፖሊሶች ዘረዝሮ አልተናገርም”ወዘተ የሚሉ ወቀሳዎችን በታዳጊው ላይ ማሰማታቸው ሌላኛው የጉዳዩ ማቀጣጠያ ቤንዚን ሆኗል።የአህመድ ቤተሰቦችም ከንቲባውም ሆኑ የፖሊስ ሹሞቹ ይቅርታ እንዲጠይቁ ጥሪ አቅርበዋል። የክስ ፋይል የተከፈተበት የአህመድ የቀድሞ ት/ቤት ጉዳዩን በጠበቆቹ አማካኝነት በመመልከት ምላሹን በቅርቡ ለመሰጠት መዘጋጀቱን የገለጸ ሲሆን ክፈለ ከተማው ግን እስከአሁን ደረስ ዝምታን መርጧል ተብሏል። ከደረስበት እስራት እና ማዋከብ የተነሳ በቴክሳስ ግዛት ውስጥ እንደልቡ መዘዋውር የተሳነው ታዳጊው አህመድ ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ ከቤተሰቦቹ ጋር በኳታር(ዶሃ) ውስጥ ስፖንሰር አግኝቶ ትምህርቱን እዚያው ዶሃ ውስጥ እየተከታተለ እንደሚገኝ ታውቋል።የ አህመድ ቤተሰቦች በበኩላቸ በሰጡት አስተያየት “ልጃችን በፈጠራ ሰራው የተነሳ ሊመሰገን ሲገባው በደረሰበት እስራት ፣መጠነ ሰፊ የ ሚዲያ ሽፋን የተንሳ በአሜሪካ/ቴክሳስ/ግዛት እርሱም ሆነ እኛ ወላጆቹ በነጻነት ለመዘዋወር ባለመቻላችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ መሰደድን መርጠናል”ብለዋል።
ከጎረቤት ሱዳን የመጡት የአህመድ ቤተሰቦች ወደ ኳታርም ቢሰደዱ ሰለ እህመድ እና ሰለቤተሰቡ የሚወርው ወሬ ግን እሁን ድረስ አላቋረጠም ።ለምሳሌ ያህል ባለፈው ሳምንት ጠመንጃ የታጠቁ እና ጸረ እስልምና መፈክሮችን ያነገቡ ተቃዋሚዎች በአህመድ የትውልድ ከተማ ወስጥ ከአንድ መስጊድ አጠገብ ተቃውሟቸውን ሲስያስሙ ተሰተወለዋል ተብሏል። የተላያዩ ማህበራዊ ድህረገጾችም እንዲሁ የ ታዳጊው የአህመድን ምስል ከቢን ላዲን ጋር በማነጻጸር “በልምምድ ላይ ያለ አሸባሪ” እሰከ ማለት ደረሰዋል። የአህመድ ቤተሶቦች መኖሪያ ቤት አድርሻ ሳይቀር የለጠፉም ተስተውልዋል ሲል የ አህመድ ቤተሰቦች ጠበቃ የጉዳዩን ውስብሰብንትን ያስረዳል። ከዚህ ቀደም በሱዳን ውስጥ ለፕ/ታዊነት ተወዳድረው ያለተሳካላቸው የአህመድ ወላጅ አባት መሃመድ ኢልሻን ሁኔታውን ቀደም ብለው ያቀነባበሩት ነው ፣ አህመድ ስራው የተባለ የግድግዳ ሰአትም ቢሆን ከ ምደብር የተገዛ እንጂ የ አህመድ የፈጠራ ውጤቱ ኣይደልም ሲሉም የሚከራከሩ ወገኖች አልጠፉም። ከ አሜሪካ ርቆ በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖረው የ አህመድ ቤተስብ ግን የደረስባቸው ተጽኖ እንዲርቁ አስገደዳቸው እንጂ የልጆቻቸው የትወልድ ከተማቸው የሆነችው ቴክሳስን ሁሌም እንደሚናፍቁ “ኳታር በጣም ጥሩ አገር ናት፣ቴክሳስ ደግሞ ያው ሁሌም ቴክሳስ ነች”ሲሉ ከቴክሳስ ግዛት ጋር ያላቸውን ዘላለማዊ ቁርኝትን ተናግረዋል።
የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 እና በአውስትራሊያ 0280725172 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።