Hiber radio: በረሃብ ለተጎዳው ወገን ሁሉም በቅድሚያ የራሱን አስተዋጽዎ እያደረገ ለዚህ ችግር ምክንያቱ ምንድነው የሚለው ላይ የራሱን የፖለቲካ አቋም ማራመድ ይችላል -ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ

በኢትዮጵያ የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ የረሃብ አደጋ ቀስ በቀስ ሕዝቡን ከቀዬ እያሰደደ፣የህጻናትን ህይወት እየቀጠፈ፣ረሃቡን ተከትሎ የተለያዩ በሽታዎች እየታዩ ወገን የወገኑን እርዳታ የሚአልግበት ወቅት ላይ ነን።በስልጣን ላይ ላሉት ሰዎች ከ15 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ይፈልጋል መባል የቁጥር ስሌት ተደርጎ ቢቆተር አይገርምም።ታሪካቸው የሚናገረው በረሃብ ስም መታ ዕርዳታ ወስደው ረሃብተኛው እአለቀ ለስልታን ሲሉ ካድሬ ማሰልጠኛና ለፓርቲ ድግስ አውለዋል።ያ የሆነው በ1977 ዓ.ም ተከስቶ በነበረው ረሃብ ነው።ዛሬም ረሃቡ ዜጎችን በጠኔ እአስቸነቀና ሕይወት እየቀተፈ ፓርቲ ድግስ ጋጋታ አልቆመም።የወገን ጉዳይ የሚያስጨንቃቸው ወጣቶች ራሳቸውን አሰባስበው ኮሚቴ መስርተው <ቤዛ ለወገን> ብለዋል።ከተቋቋሙ ወር ያልሞላቸው ወጣቶች ብዙ ርቀት እሄዱ ነው። አብሯቸው እኔም ለወገኔ ሚል ይፈልጋሉ። የቤዛ እንሁን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ ጋር ተወያይተናል።

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 እና በአውስትራሊያ 0280725172 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *