Hiber Radio: የዘንድሮው የዓመቱ የአስቀያሚዎች አሸናፊ አመራረጥ ታላቅ ተቃውሞ አሰነሳ

ugly_contest_005

በታምሩ ገዳ

አንዳንድ ጊዜ የዘመናችን የምርጫ እና የውድድር አይነቶች እና ይዘታቸውን ቀረብ ብሎ ለተመለከታቸው አጀይብ ያሰኛል።ሰሞኑን ከወደ ዙምባብዊ የተሰማው ዜና ከላይ የተጠቀሰው አባባልን ያጠናክረዋል። ነገሩ እንዲህ ነው።ሰሞኑን ዙምባብዊ ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ በተካሔደው የአመቱ የአሰቀያሚ ሰዎች ውድድር(Mr Ugly 2015) የ 42 አመቱ ሚሶን ሴሪ ቀደም ሲል የሶስት ጊዜ የአመቱ የአስቀያሚዎች ሻምፒዮና ተብሎ በዳኞች የተመረጠው ዊሊዮም ሙሳቪኒን በመርታት የአመቱ የአሰቀያሚዎች አክሊልን በማጥለቅ እና ለዚህም ውበቱ ሲባል የ አምስት መቶ ዶላር ጉርሻም ለማግኘት ችሏል። ይሁነና የቀደሞው የአስቀያሚዎች ሻምፒዮናው ዊሊም ሽንፈቱን ለመቀበል ያዳገተው ሲሆን “አዲሱ የአመቱ የአስቀያሚዎች ሻምፒዮናው ፣ሚሶን፣”ጥርሱን ሲከፍት ካልሆነ በቀር አስቀያሚ አይደልም እንዲያውም ከወላቃ ጥርሶቹ በስተቀር ቆንጆ ሲሆን ፣ እኔ ግን በተፈጥሮ ኮኮብ አስቀያሚው ነኝ፣ባለፈው አመት 4ኛ ደርጃ የወጣ ግለሰስብ (ሚሶን)ዘንድሮ ምን አዲስ ነገር ተገኝቶ ነው አንደኛ ሊወጣ ይቻለው? ” በማለት ያለፉት ሶስት ተከታታይ አመታት አሸናፊው የዘንድሮው ሁለተኛ የአመቱ አሰቀያሚው ዊሊየም ቅሬታውን በግላጭ አስምቷል። ደጋፊዎቹም እንዲሁ በዳኞቹ ላይ የሰድብ እና የተችት ናዳ አውርደዋል። ፓትሪክ ሙቡዳሬ የተባለ ሌላኛው የአመቱ የአስቀያሚዎች ተወዳዳሪ በበኩሉ”ውድደሩን ለማሸነፍ ሲባል ጥርሶቻችንን ማስወልቅ ነበረብን ?” በማለት በዘንድሮ የአስቀያሚዎች ውድድድር አሸናፊ የሆነው ብዙ ጥርሶች አልባው ሚሶንን አጣጥሎታል። እርሱም በውደድሩ ዳኞች ላይ ቅሬታውን አሰምቷል።ባለፉት ሶስት አመት የአሰቀያሚዎች ወድድድሮች 10 ተወዳዳሪዎች ብቻ ብቅ ያሉ ሲሆን በዘንድሮው አመት ግን ቁጥራቸው ወደ 25 ክፍ ማለቱ የውድድሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተወዳጅ እየሆነ መምጣቱን ያመላክታል ተብሏል።አዘጋጆቹም በበኩላቸው” የምንፈልገው ተፈጥሮአዊ አስቀያሚዎችን ብቻ ሲሆን በደል ደርሶብናል የሚሉ ወገኖች ሸንፈትን መቀበል የተሳናቸው ወገኖች ብቻ ናቸው ”ሲሉም ተደምጠዋል።

ይሁን እንጂ የዘንድሮው የዙምባቢው የአሰቀያሚዎች አሰቀያሚው ( ሻምፒዮናው) ሚሶን ተቀናቃኞቹን”መሪር ሽንፈትን መጎንጨት ያልቻሉ ፣ እኔ ከእነርሱ የበለጥኩ አሰቀያሚ መሆኔን ያልተዋጠላቸው ደካማ ፍጡሮች ናቸው“ሲል ሃሜታቸውን አጣጥሎታል። በአሁኑ ወቅት በትምህርት ቤቶች አካባቢ አየተዘዋወረ በአስቀያሚነቱ እንዴት እንደሚኮራ ትምህርት በመሰጠት ላይ የሚገኘው ይሄው የአመቱ የአሰቀያሚዎች ሻምፒዮናው ሚሶን ወደፊት የቴሊቪዥን ውሎችን ለመፈራረም እቅድ አንዳለው ሳይገልጽ አላለፈም።

አንዳንድ ጊዜ መልኬ ፣ ቁመቴ፣ ጸጉሬ አረማመዴ፣ አነጋገሬ ወዘተ ለምን እንዲህ አልሆነም? በማለት ፈጣሪን የሚያማርሩ አሊያም ያልሆኑትን ለመሆን የሚጥሩ ወገኖች ከዘንድሮው የዙምባቡኤው የአሰቀያሚዎች ሻምፒዮናው ሚሶን ብዙ የሚቀስሙ የመሰለኛል።የእኛ አገር ስፖንሰሮችም ተብዮዎችም ቢሆኑ ቆንጃጃት፣ ድምጸ መረዋዎችን ፣አይምሮ ብርሆችን ፣ፈጣን ሯጮችን ፣ኮኮብ ግብ አግቢዎችን ወዘተ ብቻ በማሳደድ እና በሃብት ላይ ሃብት ከማጋበስ ተፈጥሮ በሰጠቻቸው ጸጋ የሚኮሩ ነገር ግን በእንዳንድ የማሕበረሰቡ ክፍል የተናቁ ወገኖችን በየምክንያቱ ቢያነሷቸው ሰማቸንም ቢያሰጠሩ ለሞራልም ለክብራቸውም ቢሆን ሳይጠቅምም አይቀርም። በዚህ አጋጣሚ ብርቮ ዙምባቢዎች፣ በራሰ መተማመን ምን ማለት እንደሆነ በተግባር አሳያችሁን ማለቱ ሳይቀል አልቀርም።

 

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 እና በአውስትራሊያ 0280725172 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *