ትላንት በጎንደር ከተማ ቀበሌ 09 ውስጥ በሚገኘው ባዕታ እስር ቤት ውስጥ በእሳት ቃጠሎ ጉዳት የደረሰባቸው፣ቃጠሎ ሽሽት ሲሮጡ በእስር ቤቱ ጠባቂዎች፣በአካባቢውና በፌደራል ፖሊሶችና በታጣቂዎች ከተተኮሰ ጥይት የተገደሉት ቁጥር የአማራ ክልል ፖሊስ እንደገለጸው 17 ብቻ አለመሆኑን ህብር ምንጮች ከስፍራው ገልጸዋል።
በየአቅጣጫው ከሳት ለማምለጥ በሮቱት ላይ በሩምታ ተኩስ በእስር ቤቱ አካባቢ ብቻ የገደሏቸው ቁጥራቸው ቢያንስ ከአርባ በላይ እንደሚሆን በቃጠሎ ጉዳት የደረሰባቸውና የህክምና እርዳታ ያገኙም ሆነ ሳያገኙ የቀሩት ቁጥራቸው በግልጽ ሳይለይ የክልሉ ፖሊስ ከእስር ቤት ሲጋፉ ሊያመልቱ ሲሉ 16 ሞቱ አንድ ገደልኩ ማለቱ ፍጹም የተሳሳተ መረጃና በጠራራ ጸሐይ በጥይት በገደሏቸው ላለመጠየቅ መሆኑን እነዚሁ ምንጮች ገልጸው የከተማው ሰው ተቃውሞና ወታቶች ከፖሊሶች ጋር ግጭት ውስጥ የገቡት ከእስር ቤት ቃተሎ ሸሽተው ያመለጡት ላይ ተኩስ ተከፍቶ አደባባይ ላይ ተመቶ ጭምር ሲወድቅ በማየታቸው ነው ሲሉ እነዚሁ ምንጮች ገልጸዋል።
የጸጥታ ጥበቃውና ከእስር ቤት አለመጡ የተባሉትን ብቻ ሳይሆን ትላንት ተቃውሞ አሰሙ በሚል በጥይት የተመቱ ጭምር ወጣቶች መኖራቸውን የገለጹት እነዚህ ምንጮች አሁንም በተሌኤዩ ታቢያዎች ሰዎች እየታሰሩ እና እየተደበደቡ ከመንገድ እንደሚወሰዱ ገልጸዋል። በጎንደር ሆስፒታል በቃተሎውና በጥይት የቆሰሉ ሰዎች አንደሚገኙ የገለጹት እነዚህ ምንቾች ከሟቾቹ መካከል የተሰወኑት በጎንደርና ዙሪአው ማንነታቸው የታወቀ አስከሬናቸው ተወስዶ ስርኣተ ቀብራቸው መፈጸም መጀመሩን ጠቅሰው በግልጽ በጥይት ተገለው ፖሊስ ሲጋፉ የሞቱማለቱ ብቻ ሳይሆን ቁጥሩን ሆን ብሎ ማሳነሱን ተቁመዋል።
የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 እና በአውስትራሊያ 0280725172 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።