Hiber radio: በኢትዮጵያ ተቃውሞው በከፍተኛ ደረጃ እያደገ ሄዷል፣በአገዛዙ ባለስልጣናትና መገናኛ ብዙሃን የሚሰጡ መግለጫዎች ድንጋጤያቸውን እያጋለጠ ቀጥሏል

oromo_protest_cloused_road_003

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎችና በሰሜን ጎንደር የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ ተቃውሞ አገዛዙ አንዱን ሽብር ሌላውን አለመረጋጋት ማለቱን የቀጠለ ሲሆን በኦሮሞአ የሚካሄደው ተቃውሞ ሙሉ ለሙሉ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ተሸጋግሮ ሕዝቡ ከስርኣት ለውጥ ሌላ ጥአቄ እንደሌለው ማሳቱን የቀጠለ ሲሆን በተቃራኒው የአገዛዙ ባለስልታናት በተከታታይ የሚሰጧቸው መግለጫዎች የተምታቱ፣በሕዝቡ ተቀባይነት ያላገኙና ይልቁንም የስርዓቱን ድንጋጤ የሚአጋልጡ ሆነው ቀጥለዋል።

በሕዝባዊ ተቃዎሞው በኩል የአገዛዙ ተከታታይ መግለቻዎች ሕዝቡን ከማስፈራራት ይልቅ በልበ ሙሉነት ወደፊት እየገፋ ነው።የፌደራል የሚባሉ የሕወሃት መጫዎቻ የፌዴራል ስርዓትም ሆነ የክልሉ ባለስልታናት ባልተረጋጋ ሁኔታ አደባባይ እየወጡ የሚሰጡት መግለቻ ፍርሃታቸውን በግልጽ የሚያሳይ ግራ የተጋቡ መምሰላቸውን በሕዝቡ ውስጥ ጭምር መነጋገሪአ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ዛሬ በሱልልታ የታየውን አዲስ አበባ ከተማ አፍንጫ ስር የተደረገው ጠንካራ ተቃውሞ ለኣለም አቀፉ ማህበረሰብ ከዚህ ስርዓት ለውጥ ውጭ የሚመጣ ማንናውም አፈና እርምጃ ተቃውሞውን የበለጠ የሚያጠነክር እንጂ አገዛዙ በየመገናና ብዙሃኑ እንደሚፎክረው አሸባሪ ብሎ በመወንጀልና በመግደል የሚቆጣጠረው እንዳልሆነ እየታየ ነው።

አገዛዙ ከፍተና ባለስልጣናት በስብሳባ በቀላሉ እናረጋጋዋለን ብለው አቀዱት የሰሜን ጎንደር ሕዝባዊ ተቃውሞና የታጠቀው ገበሬ ሕይወቱን ለመስጠት በአደባባይ መማማሉ ሁኔታውን እአጋለው ሄዷል። ስርዓቱ አንዱን በአንዱ ላማስነሳት እያደረገ ያለው ሙከራ በስፋት በሕዝቡ በአገር ውስትና በውጭ በሚገኙ የትግሉ ደጋፊዎች ተደጋጋሚ የማስገንዘቢያ መግለጫ እየተሰጠበት ነው። ሕዝብ በቃ ካለ የወታደር ጋጋታና ጥይት ናዳ፣ እስራትና ግድያ በቀላሉ እንደማያቆመው እየጋመ የሄደው ሕዝባዊ ተቃውሞ ማሳአ ቢሆንም ነገሩን የበለጠ ለመግፋትና ስር ነቀል ለውጥ ለማምታት ራሱን ግንባር ላይ አውጥቶ ትግሉን በተከታታይ ሕዝባዊ ጥሪ የሚመራ ሀይል የትግሉን ፍጥነት ያህል በይፋ አለመውጣቱ የተቃውሞውን ያህል በስርኣቱ ላይ ተጨማሪ የማዳከም ጫና መፍጠር ይቻል ነበር ብለው የሚያምኑ ወገኖች አሉ።

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *