Hiber radio: ኦነግ የሕዝቡን የለውጥ ጥያቄ የማይመልስ ከወያኔ ጋር የሚደረግ የጓዳ ድርድር ጥያቄ እንደማይቀበል ገለጸ ፣ሕዝቡ በወያኔ ሴራ ሳይከፋፈል ለነጻነቱ በጋራ መቆሙምን እንዲቀጥል ጠየቀ፣አና ጎሜዝ የወያኔ ባለስልጣናት ከፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋርና ከግንቦት ሰባት መሪዎች ጋር እንዳስታርቃቸው ጠይቀውኝ ነበር ሲሉ ገለጹ ፣በኦሮሚያ ክልል በርካታ ንጹሃን የተገደሉበትን ጭፍጨፋ የአገዛዙ ሸሪኮችን ጭምር አስቆጣ፣ሐርማን ኮህን አገዛዙ በሰላማዊ በዜጎች ላይ እየወሰደ ያለውን የጭካኔ እርምጃ ተቃወሙ፣ሰሞኑን በጎንደር የመከላከያ ሰራዊቱ በተቃዋሚው ሕዝብ ላይ ጦርነት የገጠመው ከግብጽ ሰራዊት ጋር ተዋጉ በሚል ማታለያ መሆኑን ቁስለኛ ወታደር ገለጸ፣በመላው አገሪቱ ሕዝቡ ተቃውሞውን በተመሳሳይ ሰዓት በመጮህ እንዲገልጽ ተጠየቀ፣ የሰራዊቱ አባላት ድንበር ጠብቁ ብላችሁ ቤተሰቦቻችንን ትገላላችሁ ሉ መጠየቃቸው ተነገረ፣ ታፍነው የተወሰዱ አሉ ተባለ እና ቃለ መጠይቅ ከኦነግ ቃል አቀባይ ቃሲም አባነሻ ጋር እንዲሁም በታክሲ ሊዝ ጉዳይ ከቺጋጎ ኢትዮጵያዊው የታክሲ ኩባንያ ባለቤት ጋር እነ ሌሎችም አሉን

hiber_cover_122015

የህብር ሬዲዮ ታህሳስ 10 ቀን 2008 ፕሮግራም

<…የሕዝቡ የጋራ ጠላት እርስ በእርሱ በጎሳ በሀይማኖት ከፋፍሎ ሊአጋድለው የሚሰራው ወያኔ እንጂ ይሄ ህዝብ ትላንትም በሰላም አብሮ ኖሯል ነገም በሰላም አብሮ ይኖራል።ወያኔ እንደፈለገው ሳንለያይ ለነጻነታችን በጋር አብረን በመቆም ትግሉን ዳር ማድረስ አለብን ወደሁዋላ ሄደን በወያኔ ሴራ ውስጥ መግባትና ተከፋፍለን የነሱን እድሜ ማራዘም የለብንም…ወያኔ ተሸንፎ በሕዝቡ አመጽ ተንበርክኮ በይፋ የሚገባበት ሁሉንም ወገኖች ያካተተ የሽግግር መንግስት የሚቃቋምበትን እንጂ ከዚህ በፊት እንዳደረጉት በአደባባይ አሸባሪ እአሉ ከመጋረጃ ጀርባ እንደራደር የሚሉትን ዛሬ ቢሞክሩት ኦነግ ይሄን አይቀበልም።ሌላውም የሚቀበል አይመስለኝም።የሕዝቡ መስዋዕትነት ለለውጥ ነው በጋራ ሁሉም ታግሎ ለውጡን ተግባራዊ ማድረግ አለበት ።ወያኔ እኔ ከሌለሁ አገሪቱ ሶሪአ ትሆናለች የሚለው እነሱ ሳይኖሩም ከነሱ በሁዋላም ህዝቡ አንድ ላይ ነው።…> የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቃሲም አባነሻ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…የኦሮሞ ተማሪዎች የጀመሩት ትግል የማስተር ፕላን ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የዴሞክራሲ የነጻነት ጥያቄ የሁሉም ሕዝብ የጋራ ጉዳይ ጭምር ነው። በወያኔ ሴራ ሕዝቡ አንተ አማራ አንተ ኦሮሞ አንተ ጉራጌ እየተባባለ ሳይከፋፈል በጸረ ወያኔነት አንድ ላይ መሰለፍ አለበት…በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ እንዲመጣ እንታገላለን የሚል ማንኛውም ድርጅት ለጸረ ዌአኔ ትግል በጋራ መቆም ያለበት ነንጹሃን ላይ የተደረገውን ግድያ ማውገዝ አለበት። ይሄን ሕዝባዊ እምቢተኝነት በጋራ ለውጤት ካላበቃነው ግን…> ዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን የቀድሞው የኢትዮጵያ ራዕይ ማህበር ሊቀመንበር በወቅቱ የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

<…በቺካጎ የታክሲ ኩባንያ የከፈትኩት በ2004 ነው ድሮ ተማሪቤት እየሄድኩ ታክሲ እነዳ ስለነበር በአርትቴክት ከተመረቅሁም በሁዋላ የታክሲውን ስራ ስለማውቀው ከሰባት ወራት በሁዋላ ፈቃዱ አልቆ ታክሲ ኩባንያ አቃቋምኩ። ቺካጎ ታክሲ ሊዝ የሆነው ሁበርና ሊፍት ከመምጣታቸው አስቀድሞ ነው። የሊዝ አሰራር ከአንዱ ቦታ ሌላው ጋር ይለያል።… በቬጋስ ታክሲ ሊዝ በቅርብ ይጀመራል መባሉን አይቻለሁ ግን አስቀድሞ በማህበር መደራጀት ይገባል። የግድ የማህበሩ ባይሳካም ሁለትም ሶስትም ሆኖ ምናልባት የሊዝ አሰራሩ መምጣት ጥሩ አጋታሚ ከፈተረ የራስን ኩባንያ ለማቃቋም መሞከር አስፈልጋል።ይሄን ለማድረግ ነገሮች ቀላል ላይሆኑ ይችላሉ ግን አንዱ መንገድ ሲዘጋ ሌላውን በመጠቀም ካሰቡት መድረስ ይቻላል…> አቶ ንጉስ ሰለሞን በቺካጎ የ24/7 የታክሲ ኩባንያ ባለቤትና ዋና ስራ አስፈጻሚ ስለታክሲ ሊዝ አሰራር ተጠይቀው ከሰጡት ምላሽ (ሙሉውን ያድምጡት)

በብሩንዲ ውስጥ ያንጃበበው የእርሰበርሰ ግጭት ስጋት መንሴዎቹ እና የዓለማቀፉ ማህበረሰብ ሰሞነኛ ምላሽ ሲቃኝ (ልዩ ጥንቅር)

 ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ኦነግ የሕዝቡን የለውጥ ጥያቄ የማይመልስ ከወያኔ ጋር የሚደረግ የጓዳ ድርድር ጥያቄ እንደማይቀበል ገለጸ

ሕዝቡ በወያኔ ሴራ ሳይከፋፈል ለነጻነቱ በጋራ መቆሙም እንዲቀጥል ጠየቀ

አና ጎሜዝ የወያኔ ባለስልጣናት ከፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋርና ከግንቦት ሰባት መሪዎች ጋር እንዳስታርቃቸው ጠይቀውኝ ነበር ሲሉ ገለጹ

በኦሮሚያ ክልል በርካታ ንጹሃን የተገደሉበትን ጭፍጨፋ የአገዛዙ ሸሪኮችን ጭምር አስቆጣ

ሐርማን ኮህን አገዛዙ በሰላማዊ በዜጎች ላይ እየወሰደ ያለውን የጭካኔ እርምጃ ተቃወሙ

ሰሞኑን በጎንደር የመከላከያ ሰራዊቱ በተቃዋሚው ሕዝብ ላይ ጦርነት የገጠመው ከግብጽ ሰራዊት ጋር ተዋጉ በሚል ማታለያ መሆኑን ቁስለኛ ወታደር ገለጸ

በመላው አገሪቱ ሕዝቡ ተቃውሞውን በተመሳሳይ ሰዓት በመጮህ እንዲገልጽ ተጠየቀ

የሰራዊቱ አባላት ድንበር ጠብቁ ብላችሁ ቤተሰቦቻችንን ትገላላችሁ ሉ መጠየቃቸው ተነገረ

ጥያቄ በመጠየቃቸውታፍነው የተወሰዱ አሉ ተባለ

በግብጽ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በጋራ አገዛዙ በኦሮሚያ በወገኖቻቸው ላይ የፈጸመውን ግድያ በተቃውሞ ሰልፍ አወገዙ

ኤርትራዊው ጥገኝነት ጠያቂ ወጣት ጣሊያን ውስጥ ከሆስፒታል ፎቅ ተንጠልጥሎ ለመውረድ ሲሞክር ሕይወቱ አለፈች

በባህር ዳር እስር ቤት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች በእግር ብረት ታስረው እንደሚገኙ ታወቀ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-122015-122715

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *