Hiber radio: አሜሪካ የሰው አልባ የጦር አውሮፕላኑዋን ከኢትዮጵያ ስታስወጣ ቱርክ ወታደራዊ ጓዟን ጠቅልላ ከጎረቤት ገባች፣ የኢትዮጵያ ገዢዎች እንደሚሉት አሜሪካ ወታደራዊ ቤዟን በእነሱ ጥያቄ ዘጋች?

us_drone_ethiopia_04

በታምሩ ገዳ

እውን ኢትዮጵያ የአሜሪካ ገዳይ አውሮፕላኖችን ከግዛቷ ተጠራርገው እንዲወጡ አደረገች?

አሜሪካ ገዳይ ጥያራዎቿን ሰብሰባ ወጣች ፣ቱርክ ወታደራዊ ጓዟን ጠቅልላ ከጎረቤታችን ገባች

በ ወቅቱ የኢትዮጵያ ገዢ መንግስት ኢሕ አዲግ አና በ አሜሪካ መንግስት መካከል ያለው ስትራቴጂካዊ ቁርኝት የጠበቀ እንደሆነ በሚነገረበት በአሁኑ ወቅት አሜሪካ እስከ ዛሬ ድረስ ይፋ ያላደረገችው ፣ነገር ግን በበርካት የስለላ እና የመገናኛ ተቋማት ዘንድ ከ አ/አ 450 ኬ ሜ ርቀት በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ አርባ ምንጭ ውስጥ ከዛሬ አምስት አመት በፊት (2011) እንደቆረቆረችው የሚነገረው የ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ማእከሏን(ቢዝ) መዘጋቷን ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ይፋ አደርጋለች።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ለዜና ሰዎች ባቀበለው መልእክቱ” በአሜሪካ እና በኢትዮጵያ መንግስታት መካከል በተደረሰው የጋራ ሰምምንት በአርባ ምንጭ የሚገኘው የሰው አልባ አውሮፕላኖች(ድሮንስ) ማእከል ከዚህ በሁዋላ ስራውን አቁሟል” ይላል የመግለጫው መንፈስ። ታዲይ ይህ ባለፈው ሳምንት ለዜና ሰዎች ግባት የተገለጸው ነገር ግን እንደ ብዙዎች እምነት ካለፈው መሰከረም ወር ጀምሮ ሰራው አንደተቋረጠ የሚታመነው የአርባ ምንጩ የ አሜሪካኖቹ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጦር ካምፕ ጉዳይን እና መግለጫውን ተከተለው የሚወጡ ዘገባዎች የተለያዩ እንደምታዎችን እና ጥርጣሪዎችን ይዘው ብቅ እያሉ ናቸው። አንደ ዜና ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ የአርባ ምንጩ የሰው አልባ አውሮፕላኖች (ጥያራዎች) እንዲዘጉ “ከ ኢትዮጵያ መንግስት በኩል በቅድሚያ ጥያቄ በመቅረቡ ነው” ሲሉ የአገዛዙ አፈቀላጤ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል ብሏል። በአቶ ጌታቸው አምነት የአርባ ምንጩ የአሜሪካኖች የሰው አልባ አውሮፕላኖች ካምፕ ለናሙና የተቆረቆረ እንጂ ለ ዘለቄታ ተብሎ አይደለም የሚል አንድምታ አለው። አቶ ጌታቸው ሆኑ የአሜሪካ ባለ ስልጣናት ሰለ ጦር ካምፑ መዘጋት ይናገሩ አንጂ እንደ ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ዘገባ ከወራት በፊት የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የመከላከያ ባለሰልጣናት 6.7 ሚሊዮን ዶላር ግምት ያለው ፣ ለ 130 ጥያራ አበራሪዎች የ ሶስት አመት አዲስ የማሻሻያ ኮንትራት ተፈራርመውበት የነበረው እና የሰምመነቱ ቀለም ሳይደርቅ ባለተጠበቀ ሁኔታ እና በፍጥነት ሰለ ተቋረጠው ሰለፕሮጀክቱ አውንታዊ ይሁን አሉታዊ ውጤት ለጊዜው የገለጹት ነገር የለም። ይሁን እና ፒተር ፓሃም የተባሉ በአትላንቲክ ጉባኤ የአፍሪካ ጉዳይ ተመራማሪ “የአሜሪካ ሰው አልባዎቹ አውሮፕላኖቹ አልሽባብ ግስጋሴን በመግታት እና ቀንደኛ የተባሉ የቡድኑ መሪዋቹን በ መግደል በኩል ውጤታማ ነበሩ “ሲሉ ለዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ተናግረዋል።ከኢትዮጵያ ምድር እየተነሱ በሶማሊያ የአየር ግዛት ላይ የሚሳይል እና የቦምብ ናዳዏችን ሲያዘንቡ የቆዩት የአሜሪካ ድሮኖች ከዚህ ቀደም ስራውን ወደ አቁረጠው እና እድሳት ወደ ተደረገለት በጎረቤት ጅቡቲ ወደ ሚገኘው የአሜሪካ የጦር ካምፕ ይዛወራሉ ተብሎ የሚገመት ሲሆን ለሎች ምንጮች በበኩላቸው ሰው አልባዎቹ ጥያራዎች ወደ መካከለኛው ምስራቆቹ ሶሪያ እና ኢራቅ እና ወደ ማሊ እና ሊቢያ (እስላማዊ መንግስት ነኝ ባዩን ለመዋጋት) ፣ወደ ምእራብ አፍሪካ ዎቹ ናይጄሪያ እና ካሜሮን (ቦኮ ሃራምን ለመፋለም) ሳይዛወሩ አየቀርም የሚል ጭምጭምታም አልጠፋም።

በጆርጅ ማሶን ዩኒቨርስቲ ተባባሪ ፕሮፊሰር የሆኑት ተመራማሪው ትሪያንስ ለዮንስ የወጪ ፖሊሲ (ፎርያን ፖሊሲ) ለተባለው መጽሄት ሰሞኑን በሰጡት አስተያየት “የዋሽንግተን ባለሰልጣናት ከ አ/አ ገዢዎች ጋር የማይግባቡባቸው ጉዳዮች አሉ። ኢትዮጵያ ከመሬቷ እየተነሱ በጎረቤቶቿ በሚገኙ በሙስሊም ወገኖች ላይ የግድያ እርምጃ የሚወሰዱት ሰው አልባ አውሮፕላኖቹ ጉዳይ ጠጠር ያለ ችግር ሳይፈጥርባት አልቀረም።”ሲ ሉ ጥርጣሪያቸውን ሰንዝረዋል። በሌላ ጎኑ አሜሪካ ለ ሰው አልባዎቹ አውሮፕላኖቹ አብራሪዎች(ባለሙያዎች) የምተከፍለው ከፈተኛ የሆነው ውሎ አበል እና ጉርሻ(ቦነስ) ወገቧን እያጎበጠው በመሆኑ ፒንታጎን ኢትዮጵያ ውስጥ የነበራት ጓዟን ጠቅልላ ፣ወጪዎቿንም ሰብሰብ አድርጋ የአክራሪዎች ጥቃቶች ወደ በረቱባቸው ወደ መካከለኛው ምስራቅ አካባቢ ለማዛወር ተገዳለች የሚሉ ዘገባዎች ተደምጠዋል። ሰው አልባዎቹ አውሮፕላኖች በሚሰማሩባቸው ምርጥ ኢላማዎች እና አካባቢዎች ተፈላጊ እና ቁልፍ የሆኑ አሸባሪዎችን እያነፈነፉ የመግደላቸውን ያህል ፣ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ከሸብር ተግባራት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት በሌላቸው ንጹሃን እና ሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚያደርሷቸው ተደጋጋሚ ግድያዎች በሰበዊ መብት ተሟጋቾች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ማሰተናገዱ አልቀረም።”ወደ ግጭቶች አካባቢ ወታድሮቼን በጭራሽ አልክም” የምትለው አሜሪካ ግን ምንም ይባል ምን፣ ምንም ይሁን ምን ከ ሰው አልባዎቹ አውሮፕላኖችን ከመጠቀም ውጪ ሌላ ጊዜያዊ አማራጭ የለኝም ያለች ትመሰላለች።

በሌላ ወታደራዊ እና አካባቢያዊ ነክ ዜና አሜሪካ በኢትዮጵያ የነበራት የሰው አልባ አውሮፕላኖቿ ካምፕ መዝጋቷን ሰትገልጽ ሌላኛዋ የ ሰሜን አትላንቲክ የቃል ኪዳን (ኔቶ )አባል አገር የሆነችው ቱርክ በጎረቤታቸን ሶማሊያ ውስጥ “ከሶማሊያ አልፎ ለአጠቃላዩ የአፍሪካ አገራት ጥቅም የሚሰጥ” ዘመናዊ የጦር ሃይል ት/ቤት እና ማሰልጠኛ ማእከል ለመቆርቆር በሂደት ላይ መሆኗን አስታውቃለች ።ካለፈው 2010 አኤአ ጀምሮ ከሶማሊያ ጋር ወታደራዊ ግንኑነቷን ያጠናቀረችው አንካራ(ቱርክ) ከተለያዩ ወዳጅ እና ለጋሽ አገራት በተዋጣ የወታደራዊ የደንብ ልብሶች እና ጫማዎች የሚነቀሳቀስው የሶማሊያ የ መከላከያ ጦርን አንድ ወጥ በሆነ የደንብ ልብስ ለመተካት ማቀዷን በሶማሊያ ጉዳይ በቱርክ የወጪ ጉዳይ ሚንስተር ከፍተኛ ሃላፊ የሆኑት ኢሚል ቲኪን ሰሞኑን ለዜና ሰዎች ገልጸዋል። ቱርክ በቅርቡ ግምቱ ከ 400 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወታደራዊ እርዳታ ለሶማሊያ መንግስት መርዳቷ ታውቋል ።

ህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

One Comment on “Hiber radio: አሜሪካ የሰው አልባ የጦር አውሮፕላኑዋን ከኢትዮጵያ ስታስወጣ ቱርክ ወታደራዊ ጓዟን ጠቅልላ ከጎረቤት ገባች፣ የኢትዮጵያ ገዢዎች እንደሚሉት አሜሪካ ወታደራዊ ቤዟን በእነሱ ጥያቄ ዘጋች?”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *