Hiber Radio: ኬኒያ ከኢትዮጵያ የመብራት ሃይል በርካሽ ለመግዛት በጥድፊያ ላይ ነኝ አለች፣በጋምቤላ ውስጥ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመው ግድያ በገለልተኛ ወገኖች እንዲጣራ ተጠየቀ፣ ሳውዲ አረቢያ 47 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ማሰሯን ገለጸች፣በኢትዮጵያ ወያኔ ስልጣን ላይ እስካለ በሕዝቡ መካከል የጎሳና የሀይማኖት ግጭት እንዳይከሰት አስቀድሞ የጥንቃቄ ስራ እንዲሰራ ጥሪ ቀረበ፣ የታላቁ ሰማዕት አርበኛና የሐይማኖት አባት አቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ ሐውልት ወደ ቦታው መመለስ የሕዝቡ የተቃውሞ ውጤት መሆኑ ተገለጸ፣ የዚካ ቫይረስ ያሰጋቸው የአሜሪካ ባለሰልጣናት ወንዶች ኮንዶም አሊያም መታቀብን እንዲከተሉ አሰጠነቀቁ እና ቃለ መጠይቅ ከአቶ ኦባንግ ሜቶና ከሐጂ ነጂብ መሐመድ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሌሎችም አሉን

የህብር ሬዲዮ ዋና አዘጋጅ ሀብታሙ አሰፋ፣ከላይ አቶ ኦባንግ ሜቶ፣በኦሮሚያና በጋምቤላ የነበረውን ተቃውሞና ግድያ ፣አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ከታች ሳራ ሙክታር፣ፕ/ት ኦባማ ፣ሐጂ ነጂብ እና የሴት ልጅ ግርዛት ተቃውሞ ማሳያ
የህብር ሬዲዮ ዋና አዘጋጅ ሀብታሙ አሰፋ፣ከላይ አቶ ኦባንግ ሜቶ፣በኦሮሚያና በጋምቤላ የነበረውን ተቃውሞና ግድያ ፣አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ከታች ሳራ ሙክታር፣ፕ/ት ኦባማ ፣ሐጂ ነጂብ እና የሴት ልጅ ግርዛት ተቃውሞ ማሳያ

የህብር ሬዲዮ ጥር 29 ቀን 2008 ፕሮግራም

<…በጋምቤላ ሰሞኑን የተከሰተው የጎሳ ግጭት ከዚህ በፊት በተለያዩ መንገዶች በሌሎችም አካባቢዎች ተከስቷል። ይሄ አይነቱ የጥላቻ እርስ በእርስ የመጋጨት ሁኔታ የመጣው ይሄ ስርዓት ከመጣ በሁዋላ ነውነገም በጋምቤላ የተነሳው አይነት የጎሳ ግጭት በሌሎች አካባቢዎች እንዳይከሰት ምን ማድረግ አለብን? ኢትዮጵያውያን ለመተማመን መነጋገር ችግሩን ለማስቀረት በጋራ መስራት በጋራ መቆም አለብን። ይህ ሳይሆን ግን…> አቶ ኦባንግ ሜቶ የትብብር ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር ስለ ወቅቱ የጎሳ ግጭትና ንቅናቄያቸው ስላቀደው የተለያዩ ኢትዮጵያውያንን ያሳተፈ የውይይት መድረክ እመልክቶ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…የፕሬዝዳንት ኦባማ የመስጊድ ጉብኝት የምርጫ ቅስቀሳውን ተከትሎ የሙስሊም ጥላቻ ያለባቸውን ድምጽ ለማግኘት ተብሎ የሚደረግ የሪፐብሊካን ተወዳዳሪዎች እንቅስቃሴ የፈጠረውን መጥፎ አመለካከት ለማክሰም ነው።ግን ፕሬዝዳንቱ አስቀድሞም የሚያደርጉት ንግግር ሙስሊሙ ህብረተሰብ እንደሌላው ሁሉ በነጻነት  መብቱ ተከብሮ እንዲኖር ነው።የመስጊዱ ግብኝታቸው በጣም አስደስቶናልበኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ጥረት ሙስሊሙና ክርስቲያኑ እንዲጋጩ የተለያዩ ጥረቶችን አድርገዋል።የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነሱ ሴራ የሚፈታ አይነት ህብረተሰብ አይደለም።ፍትህ የሌለበት አገር ላይ ህብረተሰቡን በጎሳ ፣በሀይማኖት ለመከፋፈል ለማጋጨት ሞክረው ሞክረው አልተሳካላቸውም ወደፊትም እስከመጨረሻው አይሳካላቸውም። የውሸት ቅስቀሳቸው ግን…> ሐጂ ነጂብ መሐመድ የፈርስት ሒጅራ ፋውንዴሽን ፕሬዝዳንት የፕ/ ኦባማ የመስጊድ ጉብኝትና በኢትዮጵአ ዛሬም ስላልቆመው የአገዛዙ የማጋጨት ሴራ ላይ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ   የተወሰደ ( ሙሉውን ያዳምጡት)

በአሜሪካኖች ዘንድ እና በመላው አለም እየተሰፋፋ የመጣው አሳሳቢው የሴት ልጆች ብልት ግርዛት ሲቃኝ ( ልዩ ዘገባ )

በሳን ፍራንሲስኮ የሁበር አሽከርካሪዎች ተቃውሞ 

 ሌሎችም

 ዜናዎቻችን

ኬኒያ ከኢትዮጵያ  የመብራት ሃይል በርካሽ ለመግዛት  በጥድፊያ ላይ ነኝ አለች

 ኢትዮጵያ፣  ሱዳን እና  ግብጽ ዛሬ ካርቱም ላይ  በአወዛጋቢው የህዳሴ ግድብ  ዙሪያ ይመክራሉ

በጋምቤላ ውስጥ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመው  ግድያ በገለልተኛ ወገኖች እንዲጣራ  ተጠየቀ

ታጣቂዎች በትልቁ የፉኝዶ  መጠለያ ካምፕ  ላይ  ታቂዎች ባደረሱት ጥቃት የሰዎች  ህይወት  ጠፋ

ሳውዲ አረቢያ 47 ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞችን ማሰሯን ገለጸች

ኖርዊይ ኤርትራዊያን ሰደተኖችን ወደ አገራቸው  ለማባረር መወሰኗ  ቅሬታ ቀሰቀሰ

በኢትዮጵያ ወያኔ ስልጣን ላይ እስካለ በሕዝቡ መካከል የጎሳና የሀይማኖት ግጭት እንዳይከሰት አስቀድሞ የጥንቃቄ ስራ እንዲሰራ ጥሪ ቀረበ

የታላቁ ሰማዕት አርበኛና የሐይማኖት አባት አቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ ሐውልት ወደ ቦታው ተመለሰ

የሐውልቱ መመለስ የሕዝቡ ተቃውሞ ውጤት መሆኑ ተገለጸ

የዚካ ቫይረስ ያሰጋቸው የአሜሪካ ባለሰልጣናት ወንዶች ኮንዶም አሊያም  መታቀብን   እንዲከተሉ አሰጠነቀቁ

በመሬት  ይዞታ ሳቢያ ሻሸመኔ ውስጥ በቅርቡ  ህይወታቸው ያለፈው ራስተፈሪያዊ አሟሟት ማህበረሰቡን አስቆጣ

አለማቀፍ  እገዳ የተጣለበት እና  ተፈላጊ ወንጀለኛው በኢትዮጵያ  ግዛት በኩል ተጉዟል መባሉ ጥያቄ አሰነሳ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-020716-021416

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *