Hiber radio: ለመሆኑ ከ መለስ ዜናዊ እና ከ ኢሳያስ አፈወርቂ ባለ “ራእዪ መሪ” ማንኛው ናቸው?“መለስ ዜናዊ የአባይ ወንዝን ለመገደብ እንዳይሞክር አስጠንቅቄው ነበር” ፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ

Isayas_meles_01

በታምሩ ገዳ

ሰሞኑን “ቤላ አፍሪካ ” በተባለ ድሀረ ገጽ ላይ ማሊክ ሳር( Malick Sarr ) የተባሉ ጸሃፊ በአወዛጋቢው በሕዳሲው ግድብ ዙሪያ የኤርትራው ፕ/’ት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የቀደሞው የኢትዮጵያው ጠ/ሚ/ር መለሰ ዜናዊ ፍቅር በፍቅር በነበሩበት እ ኤ አ በ 1993 ካይሮ /ግብጽ ላይ በተካሔደው የአፍሪካ ህብርት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ሲገናኙ መለሰ ዜናዊ ለ ቀደሞው የትግል አጋራቸው ለአቶ ኢሳያስ አፈውርቂ አንድ ያለተጠበቀ ሃሳብ ሹክ አሏቸው እርሱም ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ትልቅ የኢሊትሪክ ሃይል ማመንጫ (የህዳሴው ግድብን) ለመገንባት ህልም አንዳላት እና ይህንንም ውጥን ለግብጽ ባለሰልጣናት እዚያው ካይሮ ከተማ ውስጥ ፊት ለፊት ለመናገር መወጠናቸውን ነበር ። በ ጸሃፊው ምልከታ “በብዙዎች ዘንድ ታላቁ እና ባለ ራእዩ መሪ” ተብለው የተጠቀሱት አቶ ኢሳያስ ግን የዚያን ጊዜው የቅርብ ወዳጃቸው ፣ አጋራቸው እና የ ገበናቸው ሸፋኝ የነበሩት የመለሰን ‘ድንገተኛ ሃሳብን “ከመደገፍ “መለስ ዜናዊ በዚህ ጥርጣሬ እና ገዙፍ ወጪ በተሞላበት ፕሮጀክት ላይ ከሚንጠለጠል ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በይበለጥ በመያሰፈልገው ጉዳይ ላይ አንዲያተኩር መክሬው ነበር “ ሲሉ ጸሃፊው አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ በቅርቡ ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች ሰጡት የተባለውን ቃለምልልስን ተንተርሰሰው አሰነብበውናል። ጸሃፊው ዝቅ ሲሉም “የመለሰ ዋና አላማ የነበረው ቀደምት የኢትዮጵያ መሪዎች ለዘመናት ሲያልሙት የነበረው የአባይ ወንዝን የመገደብ ህልምን በሰተመጨረሻ እውን ማድረግ ነበር ። አቶ ኢሳያስ በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ አሰተያየታቸውን ሲያራዘሙ የሀዳሴው ግድቡ ከጥንስሱ የረጅም ጊዜ ጥናት እና በግዙፍ ግድቦች ላይ የሚከሰተውን ወጪን የሚቀንስ ስትራቲጂካዊ ፋይዳ ያለው ሳይሆን ፖለቲካዊ የዘት ይዞ የተወጠነ ነበር “ማለታቸውን ጸሃፊው ማሊክ ይናገራሉ። ለጠቅ በማድረግም አቶ መለስ “ የህዳሴው ግድቡን በመገንባት ሱዳኖችን እና ግብጾችን የማንበርከክ ህልም ነበራቸው ። ወንዙን የመገንባት ውጥን እስከ ፈረንጆቹ 2011 ድረስ ሳይጀመር አዝግሟል። ይሁን እን ጂ አቶ መለስ ራእያቸው/ሕልማቸውን በተግባር ሳይመለከቱ ወደ ወዲያኛው አለም ሄደዋል ። ” በማለት ጸሃፊው ያወሳሉ። ኢትዮጵያ የበለጸጉ አገራት ቁጥር አንድ ተመጽዋች አገር መሆኑዋን የጠወሱት ጸሃፊው “ይህቺ መናጢ እና ሕዝቧ ከበርካታ ችግሮች ጋር የሚፋለሙባት አገር /ኢትዮጵያ 5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚገመት ገንዘብ በማፈሰስ ለምን በርካታ ፖለቲካዊ ደንቃራዎች ያሉበት የአባይ ወንዝን ለመገንባት ወሰነች?” የሚል ጥያቄ በብዙዎች ህሊና ውስጥ ይመላለሳል።” የሚሉት ጸሃፊው እውን የሕዳሲው ግድብ ግንባታ ተግባራዊ ይሆናል? ብለው በመጠየቅ ግምታቸውን ሲሰነዘሩ “የግድቡ ግንባታ እውን እንደማይሆን ይልቁንም ከተጠበቀው በላይ የአገሪቱን ባጀት እንደሚበላ ፣ ለዚህም ሲባል በውጪ ከሚገኘው ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ የቦንድ ሸያጭ ደጎስ ያለ ገንዘብ ለማግኘት ቢታቀደም እቅዱ ኢሕአዲግ ካሰበው በላይ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ በተለይ በአሜሪካ እና በካናዳ በሚኖሩት ሕዝቦቿ መካከል ተቃውሞ ጋብዟል። ምእራባዊያን ለጋሾች እንኳን ቢሆኑ ከግብጽ እና ከሱዳን ጥቅም ጋር የሚያጋጫቸውን ፣ በአካባቢያዊ ውህደት ላይ ችግር ይፈጥራል ብለው በሚያስቡት ግንባታ ላይ እጃቸውን አንደማያሰገቡ እና ለግንባታውም ቢሳቢስቲም አይወረውሩም ። “ሲሉ ጸሃፊው ያጣቅሳሉ ። ይህን ይበሉ እንጂን መለስ ዜናዊ ሕዳሴውን በተመለከተ ግንባታው በሚካሂድበት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመሰረት ድንጋይ ሲጣል በሰጡት አሰተያየት “ የግድቡን ስራ ተግባራዊ ለማደረግ ሁሉም የገንዘብ ምንጫችን ውጤት አልባ ሆኗል። ይህም ውጥን ለሁለት አማራጮች ዳርጎናል። አነርሱም የግንባታውን ፕሮጀክትን እርግፍ አርጎ መተው አሊያም የተከፈለውን መሰዋትነት ተከፍሎ ለግንባታው የሚውል ገንዘቡን ማሰባሰብ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ የትኛውን ምርጫ እንደሚመርጥ ጥርጣሬ የለኝም ።”ማለታቸውን ጸሃፊው በመጣጥፋቸው ላይ አሰነብበውናል። በሰተመጨረሻም በአሁኑ ወ ቅት የአባይ ወንዝን የመገንባቱ ሕልም ምናልባት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ሟቹ መለሰ ዜናዊን በአንድ ወቅት ሊያስጠነቅቋቸው አንደሞከሩት ወደ አስቀያሚ ሕልምነት /Ugly illusion/ ገና አልተለወጠም ሲሉ ጸሃፊው አስተያየታቸውን ይቋጫሉ። የዚህ የ ባለ ራእይነት ፣ የሕልም አላሚነት እና የዛቻ ነገር ከተነሳ ዘንዳ አቶ መለሰ እና አቶ ኢሳያስ ከህዳሲው ግድብ ግንባታ ውጥን በፊት በቀደሞ የአሜሪካው ፕ/ት ቢል ክሊንተን ዘመን “የአፍሪካ መጻኢ ተስፋዎች/new breed of African leadres “ ተብለው ከተተነበየላቸው ከኡጋንዳው ፕ/ት ዮዊሪ ሙሲቪኒ፣ ከሩዋንዳው ፕ/ት ፖውል ካጋሚ እና ከኮንጎው ጆሰፍ ካቢላ ጋር ተካተው ነበር ። ፕ/ት ክሊንተን በጊዜው ትንቢታቸውን እና ተሰፋቸውን በተጠቀሱት አራቱ የአፍሪካ መሪዎች ላይ ሲያሳርፉ “አነዚህ የህዝባቸው ጭቆና እና መረገጥ ያነገፈገፈቸው እና ለህዝባቸው ነጻነት ሲሉ ዱር ቤተ ያሉት ወጣት መሪዎች “ለሕዝባቸው የዲሞክራሲ ትሩፋቶች የሆኑት ሃሳብን በነጻ የመግለጽ መብት ፣ መሪዎችን በጠመንጃ ሳይሆን በድምጽ እና በካርድ መሾም እና ማውረድ የሚችሉ ፣ ነጻ ገበያን የሚያሰፋፉ ህዝባቸውን ከሙስና ፣ከረሃብ ፣ከጦርነት እና ከሰደት የሚታደጉ ወጣት መሪዎች ናቸው ።”የሚል ግምት ነበራቸው ። ዛሬም ላይ ቆም ብለን የእነዚህ መሪዎች የግል ሰብእና እና የትግል ጉዞን ሰነቃኘው በእጆቻቸው ላይ የመቶ ሺዎች ንጹሃን ዜጎች ደም እንዳለ ፣ትላንት የነበረው ሰደት እና ርሃብ ዛሬም ከእኛ አንዳልራቁ፣ የመበታተን አደጋው ከትላንቱ ዛሬ አንደከፋ በሚነገረበት ወቅት ላይ መድረሳችን እየታወቀ በአንደ ወቅት “አንቱ” ያልናቸው ባለሰልጣናት ሳይቀሩ “ፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ ባለ ራእይነታቸው ለኤርትራ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያም አንድነት እና ትንሳኤ ዘውትር የሚተጉ ታላቅ መሪ ናቸው “ ብለው በአደባባይ ሲሰብኩን የመታዘባችን ያህል በሌላኛው ጠርዝም የሚገኙ አፍቃሪ መለሰ ዜናዊዎች” ሟቹ ጠ/ሚ/ር መለሰ ዜናዊ በመቶ አመት አንዴ ከሚፈጠሩ ልዪ መሪዎች ተረታ ይመደባሉ “ የሚል ፍልስፈና ቢጢ ሊመግቡን ሲጥሩ ተሰተውለዋል። ግን ግን “ከዘንጀሮ ቆንጆ… “ የሚባለው እንዳለ ሆኖ ከአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ እና ከአቶ መለስ ዜናዊ ማንኛው ናቸው “ለዚህ ትወልድ ጥያቄ መላሽ እና ባለ ራእይ መሪ?” ፣ ማንኛቸው ለሕዝባቸው ምን መልካም ፣አሊያም የሃዘን እና የመከራ ዘመንን አመጡለት….? ብሎ መጠየቁ ፣ ከጭፍን ጥላቻ እና አምልኮ ርቆ በምትኩ በቅን ልቦና መወያየቱ አይከፋም ።

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *