በታምሩ ገዳ
እ ኤ አ በውርሃ ጥቅምት 2015 ከ ጎረቢት ከ ደቡብ ሱዳን ወደ ምእራብ አውሮፓዊቷ ቤልጂየም በመጓዝ የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቁት ኤርትራዊው አቶ ተስፋ ገብር ሃይሌ ደስታ የጠበቁት እና የሰነቁት የጥገኝነት ጥያቄ መልካም ዜና ይዞ አልመጣም ነበር።
“ኤሪ ጋዜት” የተባለ ድህረ ገጽ ሰሞኑን እንደ ዘገበው ከሆነ ቤልጂየም/ብራስልስ አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ እንደደረሱ የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ የሆነባቸው የ 52 አመቱ አቶ ተስፋ ገብር ይዘውት የነበረው መጠኑ ለጊዜው ያልተገለጸ ገንዘብ እና ንብረት በቤልጂየም የኢምግሬሽን እና የደህነነት ሃላፊዎች ከመነጠቅ አልፎ አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸው “ወደ መጣህበት ወደ ደ/ሱዳን እንባርሃለን “በሚል ስሜት ያለ ውዴታ በግዴታ እ ኤ አ በየካቲት 2 /2016 እጃቸው በካቲና ተጠፍሮ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሆነ አውሮፕላን ከተጫኑ በሁዋላ አ/አ ቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደረሱ ወደ ቤልጂየም ከማቅናታቸው በፊት የነበሩባት አገር (ደ/ሱዳን ) ለመመለስ ሀጋዊ የጉዞ ሰነድ አልባ በመሆናቸው ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግለሰቡን ወደ ሌላ አገር ለማሸጋገር ውክልና ስለ ሌለው ፣ ወደ ትውልድ አገራቸው ወደ ኤርትራም እንዳይመለሱ ቤልጂየም ከምእራባዊያን ጎረቤቶቿ ሊደረሰባት የሚችለው ብርቱ የሰበዊ መብት ጥሰት ተቃውሞን በመሰጋት አና ዋስትና ባለማግኘታቸው በአ/አ የ ቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ውስጥ በ ከብረት ከተሰራ ወንበር ላይ ያለ ብርድ ልብስ በብርድ እና በሙቀት እየተቀጡ መሆናቸው ተገልጿል።
በኖሮዊይ የሚገኙ የአቶ ተስፋ ገብር ቤተሰቦቻቸውን ዋቢ ያደረገው ዜና ዘገባው አቶ ተስፋ ግብር በቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ቆይታቸው ለየተለያዩ የሰነልቦና ችግሮች ከመጋለጣቸው ባሻገር ወደ ኤርትራ ወይም ወደ ደ/ሱዳን ካለሆነ ደግሞ ወደ ኡጋንዳ ሊባረሩ እንደሚችሉ የሚገልጹ ማሰፈራሪያዎችም እንደገጠሟቸው ተነግሯል ። የኢትዮጵያ አየር መንገድም ቢሆን የቤልጄየም መንግስትን ፍላጎት ለማርካት ሲል ብቻ የሰብ አዊ መብት ረገጣን ሸሽተው አውሮፓን መዳረሻ በማድረግ የተሰደዱት የአቶ ተስፋ ገብር እና መሰል ሰደተኞችን የምርጫ እና የጥገኝነት ፍላጎትን በመጣረስ የተፈጸመ በመሆኑ አየር መንገዱም ቢሆን ለከፋ ትችት የተዳረገ ሲሆን የወላጅ አባቷ የሰብእዊ መብት መጣስ ያሰጋት በኖሮዊይ አገር የምትኖረው የአቶ ተሰፋገብር ሴት ልጅ የ ኢትዮጵያ መንገድ የፈጸማቸው ድርጊቶችን በመኮነን ወላጅ አባቷ ቢቻል የፖለቲካ ጥገኝነት ወደ ጠየቁባት ወደ ቤልጂየም እንዲመለሱላት አሊያም በ አ/አ ለሚገኘው ለአለማቀፉ የሰደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR)ተላልፈው እንዲሰጡላት ተማጽናለች። አለም አቀፍ ዝና እና ክብር ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በግለሰቡ ላይ ስርቶታል ሰለ ተባለው የሰበዊ መብት ጥሰት ሆነ በአሁኑ ወቅት በርካታ አለማቀፍ አየርመንገዶች ከምእራብ አውሮፓ በገፍ የሚባረሩትን ሕገ ወጥ ሰደተኞችን “ ለመንገደኞቻችን ደህንነት ሲባል እንጭንም “የሚል አቋሟቸውን በሚያሰሙበት በአሁኑ ወቅት የኛው አየር መንገድ ለምን ይህንን መሰሉን አደጋ በራሱ እና በደምበኞቹ ላይ ለመጋበዝ እነደ ፈለገ እሰከ አሁን ድረስ የሰጠው ማብራሪያ ፣ ማስተባበያም ሆነ ይሁንታዊ ምላሽ አለተገኘም።
ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ ቤልጂየም ከዚህ ቀደም በአንድ ኢትዮጵያዊ የደህንነት አባል ላይ ተመሳሳያ ኢሰብ አዊ የመብት ረገጣ ያደረገች መሆኑ የሚታውስ ሲሆን ፍሬ ሃሳቡም በአጭሩ እንደሚከተለው ነው። አለም ሰገድ ተካ የተባለ አገዛዙን በመቃወም እ ኤ አ በወረሃ ጥር 27 / 2001 በእቃ መጫኛ አውሮፕላን ውስጥ በመደበቅ ወደ አውሮፓ ለመሰደድ ሲጥር አውሮፕላኑ ግብጽ ላይ ነዳጅ ለመሙላት ሲቆም አለምሰገድም አውሮፓ የደርሰ መስሎት ከአውሮፕላኑ ጉያ ብቅ ይላል። የ 28 አመቱ የደህንነት ሰራተኛው አቶ አለም ሰገድ ሁኔታን በድንጋጤ የተመለከቱት ፕይለቶቹ ለራሳቸውም ደህነነት በመፍራታቸው አቶ አለም ሰገድ ካይሮ ላይ እጁን ለግብጽ ኢሚግሬሽን ባለሰልጣናት እንዲሰጥ ለማግባባት ቢሞክሩም የግብጽ የደህንነት ባለሰልጣናት ግን ኢትዮጵያዊው የደህንነት ሰራተኛው ካይሮ ላይ እጁን መሰጠት አይችልም (አሻፈረን )በማለታቸው ሳቢያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፓይለቶቹም የአየር መንገዱ የደህንነት ክፍል አባሉ አቶ አለም ስገድን ሳይወዱ በግድ ወደ ቤልጂየም ይዘውት ይጓዛሉ።
ቤልጂየም/ብራስለስ አንደ ደረሱም በዘመኑ የኢ ሕ አዲጋዊ አጠራር የክልል ሶስት ተወላጅ በመሆኑ ብቻ በአገዛዙ ሹማምንቶች የተለያዩ በደሎች አንደሚደርሱበት ፣ ለህይወቱም እንደሚሰጋ ፣የደህነነት ሰራተኛ መሆኑን የሚያሳይ መታወቂያ በማሳየት በብራስልስ/ቤልጂም የፖለቲካ ጥገኝነት ያቀርባል። የአቶ አለምሰገድ ጉዳይን በግርድፉ የተመለከቱት የቤልጂየም የኢሚግሬሽን ሃላፊዎች የጥገኛ ጠያቂዎን ጉዳይ በአንክሮ ሳይመለከቱ የአቶ አለም ሰገድ ን መታወቂያ በመያዝ “በደል አደርሱብኝ “ወደ አላቸው የኢሕ አዲግ የ ደህንነት ሹማምንቶች ፋክስ በማድረግ የማብራሪያ ጥያቄ ያቀርባሉ። ከ አ/አ ገዢዎች በኩል “ የምትሉት ግለሰብ የእኛ አባል አይደለም፣ አሸባሪ ሊሆን ይችላል …ወዘተ ” የሚል ምላሽ በማግኘታቸው አቶ አለምሰገድ ተደብቆ ወደ ቤልጂየም ለመኮብለል በሞከረበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በቤልጂየም የደህንነት እና የኢሚግሬሽን ሰራተኞች በግዴታ ተጭኖ ወደ አ/አ ለመመለስ ይገደዳል። አቶ አለምሰገድ ከቦሌው አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርስም የጠበቁት ዘወትር የሚወዱት ቤተሰቦቹ ሳይሆኑ ፣ “በደል አደርሱብኝ “በማለት ጥሏቸው የሄደው የኢ ሕ አ ዲግ የደህነነት ሹማምንቶች ነበሩ። አቶ አለም ሰገድ ቦሌ እንደደረሰ ብዙም ሳይቆይ ወደ ማእከላዊ ወንጀል ምርመራ የወሰዳል። በዚህ ወቅት ነበር የቀድሞ የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ (ኢነጋማ ) የስራ አስፈጻሚ ኮሜተ አባላት ፣መብረቅ/መብሩክ ለተባሉት ጋዜጦች እና ለተለያዩ የነጻ ፕሬስ ውጤቶች ይሰሩ የነበሩት ፣በአሁኑ ወቅት ደግሞ በስድት አለም ከምድረ አሜሪካ ከላስ ቬጋስ ከተማ ዘውትር እሁድ በአካባቢው ሰአት አቆጣጠር 6፡30 pm (በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ 12፡30) በአማሪኛ ቋንቋ የሚተላለፈው እና በራሱ ድህረ ገጽ hiber radio .com እንዲሁም በመላው አለም ተደራሽነት እና ታዋቂነት ባላት በ ዘ ሃበሻ ድህረ ገጽ አማካኝነት መረጃ ለሚናፍቀው ህዝባችን የወቅታዊ መረጃዎች ምንጭ የሆነው የሕብር ራዲዮ መሰራቾች እና ዋና አዘጋጆች ለሁኔታው ልዩ ትኩረት በመስጠት ፣ የምርመራ ጋዜጠኝነት ክህሎታቸውን (ኢንቨስቲጊቲቭ ጆርናሊዝም ሪፖርቲንግ ) በመጠቀም ፣ጉዳዩንም ከሰብ አዊ መብት ጥሰት ጋር የተያያዘ መሆኑን በመገንዘብ እና ጉዳዩን ለአለማቀፉ ማህበረሰብ በተለይ ለዲፕሎማቲኩ ማህበረሰብ በፍጥነት ያሳውቃሉ ። የቤልጂየም የደህንነት እና የኢሚግሪሽን ሃላፊዎች ከኢሕ አዲግ የደህንነት ሹማምንቶች ጋር በመሆን በአቶ አለምሰገድ ላይ የፈጸሙት የሰበዊ መብት ረገጣዎችን የተመለከቱት በፓሪስ/ፈረንሳይ እና በጀርመን/በርሊን የሚገኙ የአውሮፓ የዲፕሎማቲክ አባላት በቤልጂየም ሕገወጥ እርምጃ በመደናገጥ ቤልጄየም የወሰደችው የተቻኮለ ፣ የተሳሳታ እና ግዴለሽነት የተላበሰው እርምጃዋን በአጽነኦት በመኮነናቸው የተነሳ የብራስልስ ም ባለሰልጣናት በሰሩት ሰህተተ በመጸጸት ሁኔታውን ለኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር እና የደህነነት ሹማምንቶች አበከረው በማስጠንቀቅ እና በመማጸን በአቶ አለምሰገድ ላይ ምንም አይነት የአካላዊ እና የስነልቦናዊ ተጽኖ እንዳይደርስበት በማሰገንዘባቸው አቶ አልምሰገድ ከታሰረበት የማእከላዊ እስር ቤት ብዙም ሳይቆይ እንዲፈታ፣ ቤልጂየምም በሰራቸው ትልቅ ስህተት አቶ አለምሰገድን በግልጽ ይቅርታ በመጠየቅ ፣ ለአቶ አለም ሰገድምም የሞራል ማካካሻ የሚሆን መጠነኛ የገንዘብ ጉርሻ መሰጠቱን የቀደሞዎቹ የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ አባላቱ እና የአሁኖቹ የህብር ራዲዮን አዘጋጆቹ ኢህአዲግ ዘውትር ነጻው ፕሬስን “የተቃዋሚዎች ልሳናት “አደርጎ ለመፈረጅ ቢሞክርም ፣ ነጻ ፕሬስ መኖር ለአገዛዙ ሰዎች ሳይቀር በጭንቀት ቀን እንደሚጠቅማቸው የአቶ አለም ሰገድ ገጠመኝን በናሙናነት በመጥቀስ በትውስታ መነጽራቸው. ይመለከቱታል ።
ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።