Hiber radio: የፈረንሳይ ፖሊሶች የኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች ጎጆዎችን በአሳት አጋዩ፣ታንዛኒያ ኢትዮጵያዊያን “ማፊያዊችን”በቁጥጥር ስር አደረግሁ አለች

france_006_ethio

በታምሩ ገዳ

በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ምድረ አውሮፓ በተለይ ደግሞ ወደ እንግሊዝ የመሰደድ ህልማቸውን ለማሳካት በጉዞ ላይ ያሉ እና በፈረንሳይ መዲና አቅራቢያ ጢሻዎች ውስጥ እጅግ ዘግናኝ በሆነ የስነልቦና እና አካላዊ ችግሮች ውስጥ የወደቁ በመቶዎች የሚቆጠሩ አትዮጵያዊኖች ጊዜያዊ መጠለያ ጎጆዎቻቸው በፈረንሳይ የአድማ በታኝ እና አፈራሽ ግበረሃይሎች ባለፈው ሰኞ አለት በአሳት አንዲጋዪ እና በቡልደዘሮች እንዲጠራረጉ ተደረገዋል። በሁኔታውም የተቆጡ ሰደተኞቹ ከጸጥታ ሃይሎች ጋር ተጋጭተዋል።የታሰሩም አሉ ተብሏል።

እንደ ሚድል ኢስት አይ ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ ሰደተኞቹን መጠለያዎች ለማፈራረስ ወደ ሰፍራው የተንቀሳቀሱ ሁለት ቡልደዘር መኪኖች እና ከሃያ በላይ አፈራሽ ገብረ ሃይሎች ተሰፋ ከቆረጡ ሰደተኞችጋር ግብግብ ውስጥ የገቡ ሲሆን ፖሊሶችም አስለቃሽ ጢስ በመጠቀም ሰድተኞቹን ከሰፍራው በማባረር ጎጆዎቻቸውን በእሳት አጋይተዋቸውል ሁኔታውንም የተቃወሙ አንድ ሰደተኛ እና “ድንበር ይለሽ” የተባለ አንድ የግበረ ሰናይ ሰራተኛ በ ፖሊስ ቁጥጥር ውለዋል። በአሁኑ ወቀት ከኢትዮጵያ ፣ ከ ኢራቅ ፣ ከ ሱዳን ፣ከኤርትራ ፣ ከሶሪያ ከ አፍጋኒስታን አና ከመሳሰሉት አገሮች የሚደርባቸውን የሰብ አዊ መብት ጥሰት ሸሸትው በ ፈረንሳዩ “ጃንግል” (ቁጥቋጦ) የተጠለሉት 4000 የሚጠጉ ሰደተኞች እጅግ አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ የሚኖሩ ሲሆን ሰሞኑን ከድንኳናቸው /ጎጆዎች ውስጥ ገሚሶቹ እንዳይፈርሱ ለፍርድ ቤት ሰሞኑን የቀረበው ተማጽኖ ውደቅ መሆኑን ተከትሎ ነበር የሰኞው እለቱ የማፍረስ እና የማቃጠል እርምጃ የተወሰደው። እንዳንድ ሰደተኞች ፖሊስ ጎጇቸውን እንዳያጋየው ለመከላከል ሲሉ ከጣሪያው ላይ በመወጣት ለመከላከል ጥረት አድርገው ነበር ። ብርቱው የአውሮፓ ክረምት ሲመጣ የሰደተኞቹ የመከራ ወቅት ይበረታል ተብሎ ተሰግቷል።

ሊ ሞንድ የተባለው የፈረንሳዩ ጋዜጣ ሰሞነኛው የማፍርስ ዘመቻው መሰረታዊ ተቋማት የሆኑት ት/ቤቶች ፣ መሰጊድ እና ቤተክርስቲያናት እንደማይፈርሱ ፍ/ቤት መወሰኑን ዘግቧል። ይሁን እና የፈረንሳይ ሕዝብ በተለይ ደግሞ ግራ ዘመም እክራሪዎች ሰደተኞቹ ተጠራርገው መሔድ አለባቸው የሚል አቋም እያሰሙ በመሆናቸው ውጥርቱ ከመቼውም ጊዜ በከፋ እየከረረ መጥቷል ተብሏል።

በተያያዘ የሰደተኞች ነክ ዜና በተለያዩ ጊዜያት በርካ ታኢትዮጵያዊያኖችን በታንዛኒያ በኩል ወደ ደ/አፍሪካ እና ወደ አውሮፓ እናሻግራችሁለን በማለት በማማለል ፣ ለእሰራት ለእካል ጉዳት እና ሕይወታቸውን ኣንዲያጡ እሰከ ማድረግ የደረሱ በረካታ ማፊያዎችን (ኢትዮጵያዊያን፣ሶማሊያዊያን፣ ታንዛኒያዊያን እና ደ/አፈሪካዊያን )የሕገወጥ ሰዎች አዘዋዋሪዎችን ሰሞኑን ታንዛኒያ ውስጥ በቁጥጥር ሰር መዋላቸውን እና “ማፊያ” ሰነሰለቱ መበጣጠሱን ተቀዳሚ የኢሚግሬሽን ሃላፊ የሆኑት ጆሲፍ ሙሉንቡ ሰሞኑን ለዜና ሰዎች የገለጹ ሲሆን ይህ ከወራት በፊት ከ 23 በላይ ኢትዮጵያዊያን ሰደተኖች መታሰራቸውን ተከተሎ የተ ካሔደው ህገወጥ የሰዎች አሸጋጋሪዎችን የማደኑ ዘመቻ ተጠናክሮ ኣንደሚቀጥል እና ሕዝቡም ከፖሊስ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅረበዋል።

የምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር ፣ታንዛኒያ ፣ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአገራቸው ሰርተው ለመኖር ተስፋ የቆረጡ በርካት ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች መሸጋጋሪያነት የሚጠቀሙባት ስትሆን ቀደም በሉት ጊዜያት (አኤአ በሰኔ 27/2012) ከ45 በላይ ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች በእቃ መጫኛ (ኮንቴይነር) ውስጥ ተጭነው ሲጓጓዙ ምግብ፣ወሃ እና አየር በማጣት እጀግ አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ መሞታቸው የበረካታ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ልብን ክፉኛ የሰበረ እና አለማቀፋዊ የ ዜና መወያያ ርእስ እንደነበር አይዘነጋም።

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *