የህብር ሬዲዮ የካቲት 27 ቀን 2008 ፕሮግራም
እንኳን ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን አደረሳችሁ!
<በአሁኑ ወቅት በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይ ስርዓቱ በራሱ ሕገ መንግስት እንኳ የተፈቀደውን አማራ ነን ስላሉ የተፈጸመውን ግፍ እዚህ ቦታው ተገኝቼ ስሰማ በእውነት ይህ ሁሉ ግፍ የሚፈጸመው ለምንድነው? የወልቃይትን ትግል ያስተባብራሉ ያሉ ተገለዋል፣ታስረዋል፣ታፍነው ተወስደዋል፣በሱዳን ወታደሮች እንዲገደሉ ተደርገዋል፣በርካታ ሴቶች በአንድ ወንድ ተደፍረዋል ሌላም ብዙ ግፍ ተፈጽማል። የሚታየው ስርዓቱ ይህንን የሕዝብ ጥያቄ መመለስ ካልቻለ ጸቡ ከወልቃይት ብቻ ሳይሆን ከመላው አማራ ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ጋር ነው……የኦሮሞ ወገኑ እየተገደለ ሌላው ሁኔታውን ለምን ቁጭ ብሎ ያያል የሚለው በፊት ግራ አጋብቶኝ ነበር አሁን ግን ግራ አያጋባኝም። …በአሁን ሰኣት ተቃውሞና ችግር ኦሮሚያ ላይ ብቻ አይደለም ችግር የሌለበት ቦታ የለም።መንግስት የትን ነው የሚያስተዳድረው አዲስ አበባን ብቻ? ሕዝቡ ተበታተነውን ተቃውሞ በአንድ ላይ የሚአስተባብረው መሪ ይፈልጋል ተቃውሞው መሪ የለውም ሕዝቡ ነው በራሱ በቃኝ ብሎ እየመራ ያለው…>
ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው የቀለም ቀንድ ዋና አዘጋጅ ከአገር ቤት ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ሰፋ ያለ ቃለ ምልልስ የተወሰደ(ሙሉውን አዳምጡት)
<…ዶ/ር ማይ ገነት ለሴቶች መብት ተቆርቋሪ.ለሰብዓዊ መብት ተማጋች ብቻ አይደለችም በአጠቃላይ ለማህበረሰቡ ተቆርቋሪ ነጭ። ሴቶች ወደ አመራር እንዲመጡ ብዙ ደክማለች…> ወ/ሮ ወሰንለሽ ደበላ የቀድሞ የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ስለ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ እና ባለፈው ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት ስለተለየችው ዶ/ር ማይገነት ከተናገረችው(ቃለ መጠይቁን ያዳምጡት)
<…እነ አበበ ቢቂላ ፣ማሞ ወልዴ፣ፋጡማ ሮባ፣ደራርቱ ቱሉ፣ምሩጽ፣የዲባባ ልጆች፣እነ ሀይሌ ፣ቀነኒሳና ሌሎቹምአገራቸውን በክብር እንዳላስጠሩ ዛሬ አበረታች እጽ በመውሰድ ስማቸው የሚጠራ አትሌቶች መኖራቸው ያሳፍራል በአንድ በመንደር ልጆች የተያዘው ስልጣንን ተገን ያደረገው ባለሙያ አልባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ይፍረስ..>
አ/አ ውስጥ በገሃድ ሲሸጥ ከርሞ ለእውቅ እና ለብርቅዩ አትለቶቻችን እንቅፋት የሆነው በአለም ላይ የታገደው ጉልበት ሰጪ መድሐኒት ያሰከተለው በሔራዊ እና አለማቀፋዊ መዘዝ ሲዳሰስ ከልዩ ዘገባው የተወሰደ ሙሉውን ያዳምጡት
የአሜሪካ አከራካሪና አስተዛዛቢ አቋም በአጼ ሀይለስላሴ፣በደርግና በወያኔ ዘመን ከኤርትራ መገንጠል በፊትና በሁዋላ ዲፕሎማሲዋና ድጋፉዋና ማዘናጊያዋ የቀድሞ ዲፖሎማቶቿ ምስክርነት ሲፈተሽ(ልዩ ዘገባ )
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
መንግስት አገሪቱን እየመራ ነው ማለት እንደማይቻል ተገለጸ
ሕዝቡ ተቃውሞውን አስተባብሮ ዳር የሚያደርስ መሪ ይፈልጋል አማራጭ አጥቶ በራሱ እየተመራ ነው ተባለ
በወልቃይት ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ ካላቆመ ሁኔታው ወደ አደገኛ አቅጣጫ ሊቀየር ይችላል ተብሏል
ግብጾች በአባይ ጉዳይ ዛሬም ከፍተኛ ስጋት እንዳላቸው ተገለጸ
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በኦሮሚያ ለተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ የሀይል አማራጭና በኦህዴድ ላይ የተያዘው ሹም ሽር ውጤት እንደማያመጣ ገለጹ
በአዲስ አበባ በሆስኒ ሙባረክ ላይ ግድያ ያሴሩት የሱዳኑ አል ቱራቢ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ድሪም ላይነር አውሮፕላን አዲስ አበባ ላይ እንግዳ የሆነ ሰው ሰራሽ ችግር ገጠመው
ከአደጋው ጋር በተያያዘ አንድ የአየር መንገዱ ሰራተኛ ጉዳት አግኝቷቸዋል ተብሏል
ሱዳን ወደ ኤርትራ ታፍነው የተወሰዱ ኢትዮጵያዊያን ታጋቾችን ለማስለቀቅ የገላጋይነት ሚና መጫወቷ ተነገረ
ፓርላማው አጠገብ የሚገኘው በፌዴራል ፖሊስ ጠዋት ማታ የሚጠበቀው የፌዴሬሽን ም/ቤት መጋዘን መዘረፍ አነጋጋሪ ሆነ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።
https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-030616-031316