በታምሩ ገዳ
የዴንማርክ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን ህጻናትን በማደጎ መልክ የማሳደግ/ የጉድፌቻ ስር አትን እና አያያዝን በቅርበት ከገመገመ በሁዋላ ሁኔታው “እጅግ አስንጋጭ እና እሳዛኝ” ሆኖ በማግኘቱ ከ ኢትዮጵያ ወደ ዴንማርክ የሚደረገውን የጨቅላ ህጻናት ዝውውር ፕሮግርምን ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ ማቋረጡን አሰታውቋል።
ዘ ሎካል ዴክ የተሰኘው ጋዜጣ ባለፈው እሮብ መጋቢት 9/ 2016 አኤአ እንዳሰነበበው በቅርቡ የአገሪቱ የማህበራዊ ጉዳይ የይግባኝ ቦርድ በኢትዮጵያ ውስጥ የመስክ ጉብኝት ያደረገ ሲሆን ቡድኑም በ ቆይታው “በጣም የሚያሳዘን እና የሚዘገንን የሕጻናት አያያዝ ለማየት ችለናል፣ በአገሪቱ የሚገኙ አንዳንድ ደላሎችም ሰለ ጭቅላ ሕጻናቱ ሁኔታ ቀጣይነት የሌለው /የተሳሳተ መረጃ ያቀብላሉ። የእነዚህ ወገኖች ዋንኛ አላማም የውጪ አገር ገንዘብ ማጋበስ ብቻ ነው ። ከዚህ በተጨማሪ እነዚህ ተወካይ ተብየዎቹ ለሕጻናቱ መጻኢ እድል መፍተሔ ከመፈለግ ወደ ውጪ አገር የሚጓዙበትን መንገድ በማመቻቸቸት እና ትርፍ በማነፍነፍ ስራ የተጠመዱ ሆነው ሰላገኝናቸው የዴኒሽ አለማቀፍ የሕጻናት አሳዳጊ ማእከል ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረውን ፕሮግራሙን ሙሉ በሙሉ ለማቁረጥ ተገዷል።” ሲል አቋሙን ገልጿል።
ኢትዮጵያዊያን እና ናይጀሪያዊያን እናቶች ከችግሮቻቸው የተነሳ የአብራክ ክፋዮቻቸው የሆኑ ህጻናት ልጆቻቸውን ለጉድፌቻ ድርጅቶች በርካሽ ዋጋ እንደሚሸጡ ያወሳው ዜና ዘገባው ከዚህ ሁኔታ የተነሳ ቀደም ባሉት ጊዜያት ዴንማርክ በተወሰነ ደረጃ የ ጉድፊቻ ፕሮግራሞቿን ለተወሰነ ጊዜያት በታቋርጥም እንደ ጎረቤቶቿ ስውዲን አና ኖሮዌይ እርግፍ አድርጋ አላቋረጠችም ነበር ተብሏል። የዴንማርክ የሶሻል ሚኒስተር የሆኑት ካረን ኤልማን አገራቸው አሁን ግን በጉድፌቻ ላይ ጠበቅ ያለ ህግ እንደምትከተል እና “በኢትዮጵያ ውስጥ በጉዲፌቻ ዙሪያ ያለውን እድገት ሰንከታተለው የቆየን ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ባለሰልጣናት ሳይቀሩ በዚህ ጉዳይ ላይ ከጥርጥሬ ውስጥ ወድቀዋል “በለዋል ።
በአጠቃላይ በአዲሱ መመሪያ መሰረት የዴንማርክ ዜግነት ያላቸው ወላጆች ከኢትዮጵያ ሕጻናትን በጉድፌቻ መልክ ለመውሰድ ከዚህ በሁዋላ ተስፋ እንዳያደርጉ/እንዳይጠብቁ የዴኒስ የአለማቀፍ የጉዲፊቻ ተቋም ገልጾ ድርጊቱም ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ውስጥ ሽሪኮቹ ከነበሩት ድርጅቶች ጋር ያለውን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ማቁረጡን አሳውቋል። ባለፈው የፈርንጆቹ 2015 የዴንማርክ መንግስት 100 ሕጻናትን በጉዲፌቻ መልክ ወደ አገሩ አንዲገቡ ያደረገ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 7ቱ ኢትዮጵያዊያን ጨቅላ ሕጻናት መሆናቸው የታወቀ ሲሆን በ2005 የአመልካቾች ቁጥር 1,183 እንደነበር ዘገባዎች ያስረዳሉ ። ምንም እንኳን ዴንማርክ ከ ኢትዮጵያ የወሰደቻቸው ሕጻናት እነ አሜሪካ እና አንዳንድ የ አውሮፓ አገራት በየጊዜያቱ ሕጻናትን ከሚያጋብሱት አንጻር ሲታይ አንሰተኛ ቢመሰልም ኮፕሃገን/ዴንማርክ የወሰደችው እርምጃ ግን በአስተማሪነቱ እና መል እክቱ ቀላል የሚባል አይደለም።
በተለያዩ ምክንያቶች ከኢትዮጵያ በገሃዱ መንገድ ለባእዳን ተላልፈው የሚሸጡ በርካታ ሕጻናት ለተለያዩ የሰነልቦና አና የአካል በደሎች እንደሚጋለጡ ፣ገሚሶቹ በአሳዳጊዎቻቸው ወሲባዊ ጥቃት እንደሚደርስባቸው ሕይወታቸውን አሰከ ማጣት እና ላልባሌ ኑሮዎች እንደሚጋለጡ የተለያዩ ዘገባዎች በአጽኖት ይናገራሉ።
ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።