Hiber Radio: የእንግሊዝ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለማሳፈን በሚሊዮን የሚቆጠር ፓውንድ አውጥቷል የሚል ወቀሳ ቀረበበት፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በቻይና ዕዳ ሳቢያ ጥንቃቄ ካልታከለበት ሊንኮታኮት እንደሚችል ታዋቂ የኢኮኖሚ ባለሙያ አስጠነቀቁ፣ በማዕከላዊ የታሰሩ የኦሮሞ ተወላጆች በረሃብ አድማ ሳቢያ ጉዳት ደርሶባቸው 31 ሆስፒታል ገቡ፣በጎንደር ኳስ ጨዋታ ለማየት በስታዲየም የተገኘው ሕዝብ አገዛዙ በወልቃይት ላይ የሚወስደውን ግፍ አወገዘ፣ ይለያል ዘንድሮ የኢህአዴግ ኑሮ ሲል ተቃውሞ አስምቷል፣በኢትዮጵያ የተከሰተው የረሃብ አደጋ አስከፊ እየሆነ መሄድ ዓለም አቀፋዊ ስጋት ሆነ ፣በኦሮሚያ እየተካሄደ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዛሬም አላባራም ፣በትግራይ የባጃጅ ሾፌሮች የጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ ታገደ የሚሉ ና ቃለ መጠይቅ ስለ ዋሽንግተኑ ጉባዔ ፣በኢትዮጵያ ስርዓቱ ገሎ ራሴ አጣራለሁ ስለማለቱ፣የአሜሪካ ምርጫ ቅስቀሳ የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን መራጮችን በተመለከተ ፣የቤልጂየሙ የሽብር ጥቃትና የቬጋስ ታክሲ ሊዝ ጉዳይ

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ መጋቢት 18 ቀን 2008 ፕሮግራም

<…መንግስት ራሱ ገዳይ ሆኖ በራሱ መዋቅር ውስጥ ያለ ከዚህ ቀደም ባለው ሪከርድ የመንግስትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመሸፋፈን ብቻ ሳይሆን ያንን የሚያጋልጡ ሪፖርቶችን የሚያወጡትን የሚያወግዝ የስርዓቱ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኦሮሚያ የተደረገውን ግድያ አጣራለሁ ማለቱ ተአማኒነትም ተቀባይነትም የሚያመጣ አይመስለኝም …የሰብዓዊ መብት ጥሰቱን መረጃ በተመለከተ ይሄ ተቋም መረጃዎችን ለማሸሽም ሆነ ለመደበቅ ከመሞከሩ በፊት ግን… >

አቶ ያሬድ ሀ/ማሪያም የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ለኢትዮጵያ ማህበር ዋና ዳይሬክተር ከቤልጂየም   በወቅታዊ አገዛዙ ራሱ ገሎ ራሱ አጣራለሁ ስላለው የኦሮሚያ የሰብዓዊ መብት ጥሰት   ጉዳይ ላይ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ   (የመጀመሪያውን ክፍል ያዳምጡት)

 <…የተለያዩ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ከተለያዩ ማህበረሰብ የመጡ የነገዋ ኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያሳስባቸው በሚያስማማቸውም በሚለያዩበትም ጉዳይ በቪዥን ኢትዮጵያው ጉዳዔ ላይ መክረዋል። ይሄ አስደሳች ነው   ኢትዮጵያውያን ለመተማመን መነጋገር አለብን ነው የእኛ መርህ እኔም በዚያ ተገኝቼ የሲቪል ማህበረሰቡ ሚናን በተመለከተ በተሰጠኝ ርዕስ ተናግሬያለሁ ይህ መሰሉ ውይይት በየቦታው መቀጠል አለበት የእኛም በሚኒሶታ በቅርቡ የምናደርገው ውይይት ጠቀሜታው ይሄው ነው።መነጋገር መቀራረብ መስማማት ያለብን ዛሬ ነው… >>

 አቶ ኦባንግ ሜቶ በዋሽንግተን ዲሲ ቪዥን ኢትዮጵያ ከኢሳት ጋር ያዘጋጁትን ጉባዔ አስመልክቶ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ ( ሙሉውን ያዳምጡት)

 <…የአሜሪካ ምርጫ በአሜሪካ የምንኖር ኢትዮጵያውያን የመምረጥ መብት ያለን መብታችንን ተጠቅመን መምረጥ አለብን…ከኢትዮጵያ የወደፊት ጉዳይ አንጻር ሳየው ከኦባማ አስተዳደር የክሊንተን የተለየ አይመስለኝም ። በበኩሌ ትራምፕ የሚያሸንፍ አይደለም ቢሆን ደስ የሚለኝ በርኒ ሳንደርስ ነው ግን የኔ ግምት… >

አቶ ከባዱ በላቸው ከዋሽንግተን ዲሲ የአሜሪካን የምርጫ አስመልክቶ ለኢትዮጵያ አሜሪካውያን መራጮች ያለውን ጠቀሜታ አስመልክቶ ላቀረብንላቸው ጥያቄ ከሰጡን ምላሽ( ሙሉውን ያዳምጡ)<… በምርጫው ውስጥ ያለንን ተሳትፎ ማሳደግ የመምረጥ መብታችንን መጠቀም እኛንም ሆነ ልጆቻችንን የሚመለከት ጉዳይ ነው ።የዲሞካራት ፓርቲን በተመለከተ አሁን ካለው የቅድሚያ የምርጫ ሒደት አኳያ ክሊንተን እየመራች ነው ።ፓርቲውን ወክላ ተወዳድራ ካሸነፈች የኦባማ አስተዳደር የሚከተላቸውን ጉዳዮች የምታስቀጥል ነው…የኔም ግምት…>

አቶ ዮሴፍ መንገሻ በቬጋስ የቀድሞው የኢትዮጵያ ራዕይ ማህበር ዋና ጸሐፊ ስለ አሜሪካ ወቅታዊ ምርጫ ከሰጡን ማብራሪያ የተወሰደ(ሙሉ ውይይቱን ያዳምጡት)

<…የታክሲ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ያወጣው በቬጋስ የታክሲ ሊዝ ስለሚደረግበት ሁኔታ የሚመለከተው በአግባቡ መታየት አለበት ። ዲፖዚት ያስቀምጣል ይላል ይሄ ዲፖዚት ምን ያህል ነው ከዲፖዚቱ ላይ ኩባንያው የሚቀንሰው ለእንዴት ላሉ ጉዳዮች ነው? ግልጽ አይደለም…>  

አቶ ቢኒያም ሰመረአብ የታክሲ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ያወጣውን የታክሲ ሊዝ ተግባራዊ ስለሚሆንበት ሁኔታ ከሰጠን ማብራሪያ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)የአውሮፓ ሕብረት እና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን አገሮች (ናቶ) መዲና በሆነችው ቤልጂየም ብራስልስ ከተማ የሰሞኑ የሽብር ጥቃት ጠንሳሾች ማንነት እና ዓለማቀፋዊ ምላሾቹ ሲቃኙ ( ልዩ ጥንቅር) ሌሎችም

 ዜናዎቻችን

የእንግሊዝ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለማሳፈን በሚሊዮን የሚቆጠር ፓውንድ አውጥቷል የሚል ወቀሳ ቀረበበት

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በቻይና ዕዳ ሳቢያ ጥንቃቄ ካልታከለበት ሊንኮታኮት እንደሚችል ታዋቂ የኢኮኖሚ ባለሙያ አስጠነቀቁ

በማዕከላዊ የታሰሩ የኦሮሞ ተወላጆች በረሃብ አድማ ሳቢያ ጉዳት ደርሶባቸው 31 ሆስፒታል ገቡ

በጎንደር ኳስ ጨዋታ ለማየት በስታዲየም የተገኘው ሕዝብ አገዛዙ በወልቃይት ላይ የሚወስደውን ግፍ አወገዘ

ይለያል ዘንድሮ የኢህአዴግ ኑሮ ሲል ተቃውሞ አስምቷል

በኢትዮጵያ የተከሰተው የረሃብ አደጋ አስከፊ እየሆነ መሄድ ዓለም አቀፋዊ ስጋት ሆነ

በኦሮሚያ እየተካሄደ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዛሬም አላባራም

በትግራይ የባጃጅ ሾፌሮች የጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ ታገደ

በአዲስ አበባ ታክሲዎች ዳግም የስራ ማቆም አድማ ያደርጋሉ የሚል ግምት አለ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-032716-040316

One Comment on “Hiber Radio: የእንግሊዝ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለማሳፈን በሚሊዮን የሚቆጠር ፓውንድ አውጥቷል የሚል ወቀሳ ቀረበበት፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በቻይና ዕዳ ሳቢያ ጥንቃቄ ካልታከለበት ሊንኮታኮት እንደሚችል ታዋቂ የኢኮኖሚ ባለሙያ አስጠነቀቁ፣ በማዕከላዊ የታሰሩ የኦሮሞ ተወላጆች በረሃብ አድማ ሳቢያ ጉዳት ደርሶባቸው 31 ሆስፒታል ገቡ፣በጎንደር ኳስ ጨዋታ ለማየት በስታዲየም የተገኘው ሕዝብ አገዛዙ በወልቃይት ላይ የሚወስደውን ግፍ አወገዘ፣ ይለያል ዘንድሮ የኢህአዴግ ኑሮ ሲል ተቃውሞ አስምቷል፣በኢትዮጵያ የተከሰተው የረሃብ አደጋ አስከፊ እየሆነ መሄድ ዓለም አቀፋዊ ስጋት ሆነ ፣በኦሮሚያ እየተካሄደ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዛሬም አላባራም ፣በትግራይ የባጃጅ ሾፌሮች የጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ ታገደ የሚሉ ና ቃለ መጠይቅ ስለ ዋሽንግተኑ ጉባዔ ፣በኢትዮጵያ ስርዓቱ ገሎ ራሴ አጣራለሁ ስለማለቱ፣የአሜሪካ ምርጫ ቅስቀሳ የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን መራጮችን በተመለከተ ፣የቤልጂየሙ የሽብር ጥቃትና የቬጋስ ታክሲ ሊዝ ጉዳይ”

  1. አስበኝ አስታውሰኝ !!!

    እኔ ነኝ ባልመጣ፣
    በልተህ ስትጠጣ፣
    ተኝተህ ስትመኝ፤
    በሰብዓዊነትህ አስበኝ፤
    አስታውሰኝ።
    ተፈጥሮ በእምቢታ በሰው ሰራሽ ሲያይል፤
    የረሃብን ጉንፋን በአይኔ አፍጥጬ ሥስል።
    የምበላው ጠፍቶ የውሃ ጠብታ፤
    የእንስሳት ሽንት ለጥም ያጣሁኝ ላንዳፍታ።
    እኔ ነኝ…
    ከቀመሰ የበላው ይጠግባል ይባላል፤
    ውሃ ከሚጎነጭ ያቀረረ ይሻላል።
    ከውሃው ከቅምሻው ምንም ስለሌለኝ፤
    በድርቅ ተሰድጄ ሞት የሚያስተውለኝ።
    እኔ ነኝ…
    መራመድ የመልችል ለመሸሽ ይቅርና፤
    ሆዴን ጠኔ ይዞት ብጎብጥ የማልቀና።
    በሬሳ ላይ የማዘግም ተስፋዬን ሳልቆርጥ፤
    ጩኸቴ እንዲሰማ በአፅሜ፡ክንድ ስቧጥጥ፤
    እኔ ነኝ…
    ከሙታኖች መንደር መቃብር ይከብዳል፤
    የሞት ከተማ ግን ይበልጥ ያስብዳል።
    ፍጥረት ጥም አነቀው በአቅሙ ተናነቀ፤
    የቻለው ታገለ ያቃተውወደቀ።
    እኔ ነኝ…
    እንዲያ በሞት አድማስ ተቆላልፎ ጋራው
    የገደል ማሚቶ ሲያፏጭበት ዙሪያው
    ፍጥረት እርጭ ብሎ ሲነድ በቃጠሎ
    ወደ ሰማይ ቢያዩት ጥምብ፡አንሳ አይኑን ተክሎ፤
    ዕርቃነ፡ፍጥረቱን ሜዳው ተሸልቶ ስንጥቅጥቅ ብሎ።
    ግቢ፡ነብስ ውጪ፡ነብስ ሲያደርቀኝ ሁለቴ፤
    አልቀመጥ ቆሜ ሲቃ ቢይዘኝ ሞቴ፤
    እያለ ጉልበቴ ከዳኝ ሰውነቴ።
    እኔ ነኝ…
    የልጆቼ ጭቃ ድንግሉ ለም አፈር፤
    ኩኩሉ ያሉበት ያደን ለምለም ሰፈር፤
    ከብቶች የዋሉበት ዘመድ ቤተሰቡ አገር ያደገበት፣
    ርጥብ ሜዳ ጋራ፤
    አልሆን ሲል ለአዝመራ፣
    ይሻል መስሎኝ ብሶ የፀሐይ ጠራራ፤
    ይባስ እያየለ አያ ሞትን ጠራ።
    እኔ ነኝ…
    ሰው በሰብዓዊነት ዙሮ ቢመለከት፤
    ራሱን በልቡ በአዕምሮው ቅን ቢከት፤
    መስተዋቱ ሰው ነው ከሥራ ቀጥሎ፤
    ለችግር መድሃኒት ለውድ ሕይወት ብሎ።
    እያሉ አባቶች ከመከሩኝ መሐል፤
    ት ዝ አለኝ ይበልጡን ይህ የሙት ኃይለ፡ቃል
    እኔ ነኝ ባልመጣ፣
    በልተህ ስትጠጣ፣
    ተኝተህ ስትመኝ፤
    በሰብዓዊነትህ አስበኝ ! ! ! 
    አስታውሰኝ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *