የህብር ሬዲዮ ሚያዚያ 10 ቀን 2008 ፕሮግራም
<… በጋምቤላ የተከሰተው ግድያ ድንገተኛ አደጋ አይደለም በተደጋጋሚ እየተሰነዘረ የነበረ ጥቃት ነው። ራሳቸው የሕወሓት ባለስልጣናት የሚያውቁት ነው። ጠረፍ ጠባቂ ማድረግ ሰራዊት እዛ መኖር ነበረበት ሀላፊነቱ የመንግስት ነው…መፍትሔው ይሄን ስርዓት መለወጥ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ላይ ጫና መፍጠር ሕዝቡ በአንድ ላይ ለመብቱ እንዲቆም ማድረግ ካልተቻለ ግድያው ትላንትም ነበር ዛሬ አለ ነገም…> አቶ ኦባንግ ሜቶ የትብብር ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች የተወሰደውን ግድያ አስመልክቶ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
<…ሰራዊቱ የሕወሃት ባለስልጣናትን ንብረት፣የነሱን ስልጣን ጠባቂ አድርገውታል። ኦሮሚያ ላይ ከፍተኛ ሰራዊት አላቸው፣በመሐል አገር በተለይም ከፍተኛ ቁጥር ያለው በሰሜን እዝ አለ ። ባለፈው በኤርትራ ወጣቶች ተወሰዱ ሲባል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት አንቀሳቅሰዋል ዛሬ ግን ሰው እንኳን ሞቶፈጣን እርምጃ አልወሰዱም በዚህ ጥፋት ተጠያቂዎቹ የሰራዊቱ አመራሮች ናቸው።ሰራዊቱ ግን በአሁኑ ወቅት እየጠየቀ ነው …> ኮሎኔል ደረሰ ተክሌ የቀድሞ የሰራዊቱ የጥናትና ፕላን ክፍል ሀላፊ በጋምቤላ የተከሰተውን ግድያ አስመልክቶ ለህብር ከሰጡት ማብራሪያ(ሙሉውን ያዳምጡት)
<…በጋምቤላ የተወሰደው ግድያ ከደቡብ ሱዳን ድንበር ጥሰው የገቡት የሙርሌ ታጣቂዎች ግድያ ሲፈጽሙ የዛሬው የመጀመሪያ አይደለም። ከሳምንት በፊት ፉኢዶ ላይ ሃያ አኙዋኮችን ገለው ከብት ዘርፈው አፍነው የወሰዱዋቸውን ሶስት ህጻናት ገለዋል። የወያኔ ባለስልጣናት ያሉት የለም። ሕዝቡን ትጥቅ አስፈትተው እርስ በእርሱ ከፋፍለው እየገደሉና እያስገደሉ ያሉት እነሱ ናቸው…ስርዓቱ ካልወደቀ ግድያው አይቆምም።…> አቶ ኡዶል ኡጁሉ የታህሳስ ሶስት መታሰቢያ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ዋና ጸሐፊ የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች በጋምቤላ በንጹሃን ላይ የፈጸሙትን ግድያ አስመልክቶ ከሰጡን ቃለ ምልልስ(ቀሪውን ያዳምጡ)
በሊቢያ በረሃዎች እና የባሕር ዳርቻዎች ላይ የዛሬ ዓመት በአረመኔዎቹ አይሲስ ታጣቂዎች በግፍ ስለተገደሉት 30 የሚጠጉ ወገኖቻችን ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? ቁርዓኑስ? ስለ ከፈሉት ሐይማኖታዊና ኢትዮጵያዊ ተጋድሎ የሚዘክር መሰናዶ(ልዩ ጥንቅር)
በኦሮሚያ ክልል የተነሳው ሕዝባዊ ንቅናቄ በአገዛዙ የመብት ረገጣ እየተዳከመ ነው? የተቃውሞ አመራሮች ተገቢውን አመራር ሰጥተዋል እና ሌሎችን ወቅታዊ ጉዳዮች አስመልክቶ ከቢቢኤኑ ዋና ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ሳዲቅ አሕመድና ከአንሃፋው ጋዜጠኛ በፍቃዱ ሞረዳ ጋር ያደረግነው ሰፋ ያለ ውይይት የመጀመሪያ ክፍል(ያዳምጡት)
ኦቲዝም እና ልጆቻችን ወላጅና ባለሙያ ምን ይላሉ ቃለ መጠይቅ ተካቷል(ያዳምጡት)
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
በጋምቤላ በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ለተገደሉት ከ200 በላይ ንጹሃንና ለታፈኑት ከመቶ በላይ ህጻናት የምዕራብ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል አብረሃ ማንጁስና ኤታማዦር ሹሙ ሳሞራ የኑሱ ተጠያቂዎች መሆናቸው ተገለጸ
ከግድያው የተረፉ እማኞች የክልሉን የዘገየ እርምጃ አውግዘዋል
አባዱላ ገመዳ ኢህአዴግ መቶ በመቶ በተቆጣጠረው ፓርላማ ተቀምጠው ጸሎት እንዲደረግላቸው መጋበዛቸው የስርዓቱ ደጋፊዎችን ጭምር አስቆጣ
የጋምቤላውን ጥቃት ተከትሎ ኢትዮጵያውያን የአገሪቱን ድንበር መጠበቅ የተሳነው አገዛዝ ላይ ቅሬታቸውን ማቅረብ ቀጥለዋል
የአረብ ኢሚሬት በአሰብ ወደብ ላይ ወታደራዊ ተቋም መገንባት ለኢትዮጵያ ስጋት መሆኑ ተነገረ
ኮስታሪካ በህገወጥ መንገድ ወደ ግዛቴ ገቡ ያለቻቸውን ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ዳግም ወደ ፓናማ ማባረሯ በሁለቱ አገሮች መካከል ውጥረት ፈጠረ
በጣሊያኑ ላምባዱሳ ደሴት አቅራቢያ ለሰጠሙት ወገኖቻችን ተጠያቂ የሆነው ግለሰብ ጣሊያን ውስጥ ቅጣቱን አገኘ
ለስልጣኑ የሰጋው የኢትዮጵያው አገዛዝ የፈለገውን ኮምፒዩተር ለመሰለልም ሆነ የዜጎችን የዲጂታል እንቅስቃሴ ለመገደብ ሕግ አርቅቆ አቀረበ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ፡30 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።
https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-041716-042416