የህብር ሬዲዮ ሚያዚያ 30 ቀን 2008 ፕሮግራም
እንኳን ለእናቶች ቀን አደረሳቹ!
አራት ለኦሮሞ ሕዝብ ነጻነት የሚታገሉ ተቃዋሚ ድርጅቶች በቅርቡ በሚኒሶታ ላይ ባደረጉት ስምምነት በጋራ ለመታገል ወስነዋል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣የተባበረው የኦሮሞ ነጻነት ግንባርና የኦሮሚያ ነጻ አውጭ ግንባር ናቸው። አቶ አሚን ጁዲ ድርጅቶቹ በጋራ ለመታገል ባደረጉት ስብሰባ ላይ ድርጅታቸውን በመወከል ተገኝተዋል። ስለ ትብብሩ ከአቶ አሚን ጁዲ እና ከጋዜጠኛ በፍቃዱ ሞረዳ ጋር ተወያይተናል። (ሙሉውን አድምጡት)
<…እንገድልሃለን ሬሳህ ነው ከዚህ በሁዋላ ወድቆ የሚገኘው ብለውኛል። ሲ.ኤም.ሲ አካባቢ በቀድሞ ማስተር ፕላን ሕጋዊ የሆነና መንገድ ሲዘረጋ መፍረስ ያለበት የስርዓቱ ደጋፊዎች ህንጻ ሳይነካ በአዲስ ማስተር ፕላን በሚል ሌሎች በቀድሞው ፕላን ሕጋዊ የሆኑት ለመንገድ ተብሎ የተወሰነው ክፍል ሲፈርስ እዛ አካባቢ በመገኘቴ ሰባት ፖሊሶች ይዘው ለሰዓታት አቆይተው ከስልኬ ላይ ያነሳሁዋቸውን በረሃብ ሳቢያ የተፈናቀሉ ዜጎች ፎቶ ወደራሳቸው ወስደው ለምን አነሳህ ለማን እንደምትሰጥ እናውቃለን በማለት እንደሚገሉኝ ዝተዋል…>
የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ አበበ ውቤ ክትትልማ ማስፈራራት እየተደረገበት መሆኑን ገልጾ ለህብር ከሰጠው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)
በካናዳ አልበርት ግዛት የተከሰተውን የሰደድ እሳት አደጋና በዚያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን አስመልክቶ የከተማው ነዋሪ ከሆነው ጋዜጠኛ ሰይፉ መኮንን ጋር ያደረግነው ቆይታ (ሙሉውን አድምጡት)
የአፍሪካ አምባገነኖች የስልጣን ሙጢኝ በሽታን ኮፊ አናን በቅርቡ በኢትዮጵያ ተገኝተው ያወገዙበት ስብሳባ ሲቃኝ (ልዩ ጥንቅር)
በቬጋስ የሕወሃት አገዛዝ የጠራው ስብሰባ ስለደረሰበት ተቃውሞ ቃለ መጠይቅ
በአዲስ አበባ ቤታቸው ያለማስጠንቀቂያ የፈረሰባቸው ነዋሪዎች አሉበትን ሁኔታ በተመለከተ ከአካባቢው ያደረግነው ቃለ መጠይቅ ይዘናል
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
ደቡብ ሱዳን ለከበባ ገባሁ ያለው የኢትዮጵያ ጦር በግዛቴ ውስጥ የለም አለች
የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ የጸጥታ ሀይሎች ሊገድሉት መዛታቸውንና ክትትል እየተደረገበት መሆኑን ገለጸ
ኦብነግ ኢትዮጵያ እየታመሰች ነው ይላል
ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ዮናታን ተስፋዬ ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ ጠየቀ
በአዲስ አበባ ሕገ ወጥ ጥቅም ጠይቀው ያልተሳካላቸው ባለስልጣናት ያለ ማስጠንቀቂያ ሕገ ወጥ ያሏቸውን ከሰማኒያ በላይ ቤቶች አፈረሱ
በቬጋስ የሕወሃት አገዛዝ በብአዴን ስም የጠራው ስብሰባ ጠንካራ ተቃውሞ ገጠመው
የኤርትራ መንግስት ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች እስራኤል ውስጥ ተጋጩ
የቢን ላዲንን ዱካ ለአሜሪካኖች የጠቆሙት ዶ/ር በእስር ቤት እየማቀቁ ነው
ሌሎችም ዜናዎች አሉ
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ፡30 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።
https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-050816-051516