Hiber Radio: ኢትዮጵያዊው ነጋዴ ደ/አፍሪካ ውስጥ ሊዘረፈው የመጣ ሌባን ገደለ ተብሎ ለእስራት ተዳረገ

south-africa-zono-002

በታምሩ ገዳ

በደቡብ አፍርሪካ ከሜዲናይቱ ጆሃንሰበርግ ሰሜናዊ አቅጣጫ ከምትገኘው ዲፕስሎት ከተባለችው ከተማ ውስ ጥ በንግድ ስራ የተሰማራው የ 35 አመቱ ኢትዮጵያዊ ንብርቱን ለመዝረፍ ከመጡ ወሮበላዎች መካክል አንዱን ደብድበህ ገደለሃል የሚል ወንጀል ቀርቦበት ከሕግ ጥላ ስር እንደሚገኝ ተዘገበ።

ኒወስ 24 የተባለ ድህረ ግጽ የፖሊስ ምንጩን ዋቢ በማድረግ እሮብ እለት እንደዘገበው ከሆነ ለጊዜው ስሙ ያለተጠቀሰው ኢትዮጵያዊው ነጋዴ ማክሰኞ እለት ለመታሰሩ እና በበነጋታው ሃሙስ እለት ከ ፍርድ ቤት ለመቅረቡ ምክንያት የሆነው ሟቹ እና ዘራፊው ከግብረ አብሩ ጋር ከኢትዮጵያዊው ነጋዴ ሱቅ በያዘነው አመት ውስጥ ጨለማን ተገን አድርገው እኩለ ለሊት ላይ ዘልቀው በመግባት የጦር መሳሪያቸውን/ሽጉጥ በማውጣት እና በማሰፍራራት ከመደብሩ ውስጥ መጠኑ በውል ያልተገለጸ ገንዘብ እና የተለያዩ ሸቀጦችን ዘርፈው ለመወጣት ሲሉ በወቅቱ ከመደብራቸው ውስጥ ተኝተው የነበሩት ተከሳሹ ኢትዮጵያዊው ነጋዴ እና ጓደኛው ከዘራፊዎቹ አንደኛውን በጣሪያ ላይ ለማምለጥ ሲጣጣር በመያዝ እንደ ደበደቡት እና ጩሀቱንም የሰሙ ጎረቤቶች (ኢትዮጵያዊያኖች?) ከመቀሰፈት ደረሰው ሌባውን ደጋግመው በመውገራቸው ሌባውም ከድብደባው የተነሳ ምንም ኣንኳን የህክምና ባለሙያዎች ወደ ስፍራው ቢመጡም የሌባውን ህይወት ሊታደጓት አልቻሉም። ሌባውም ብዙም ሳይቆይ ሞቷል የሚል የአይን ምስክሮች ከፖሊስ ዘንድ ቀርቧል።

ከተፈጠረው ዝርፊያ እና ደብደባ የተነሳ አካባቢው ሊጊዜው ውጥረት ውስጥ ቢገባም ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ/ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞችን ለህግ እንደሚያቀረብ ቃል በመግባቱ ለጊዜው ሰላም ወርዷል ይላል ዘገባው።

የኢትዮጵያዊው ነጋዴ እጣፈንታ ምን አንደሚሆን ለጊዜው በውል ያልታውቀ ሲሆን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየውን ያልተደላደለ ፖለቲካዊ ምህዳር እና ያልተመጣጠነ የኢኮኖሚያዊ መዋቅር ተስፋ ያሰቆረጣቸው በሺዎች የሚቆጥሩ ኢትዮጵያዊያኖች በኬኒያ፣ በታንዛኒያ፣ በዛምቢያ ፣በማላዊ እና በመሳሰሉት አገሮች እጅግ ዘግናኝ የሆነ ግፍ እና በደል እየደረሰባቸው የተስፋይቱ ምድር ከሚሏት ደ/አፍሪካም ሲደርሱ ያቺ የ ነጻነት ታጋዩ፣ የመጀመሪያው የ የአገሪቱ ጥቁር ፕ/ት የኒልሰን ማንዴላ አገር ከአፓርታይድ የአገዛዝ ቀንበር ነጻ ትወጣ ዘንድ በትጥቅ ትግሉ ወቅት ጉልህ ሚና ለተጫወተችው ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ልጆች ምድራዊ ገነት መሆኗ ቀርቶ ምድራዊ ሴኦል በመሆን ያ ሁሉ ውለታ ተረስቶ ”አትጵያዊያኖችን ጨምሮ ሰደተኞች ከአገራችን የውጡልን!! ፣አይናቸውንም ልናየው በጭራሽ አንሻም!! ወዘተ” በሚሉ የአገሪቱ ወጣት ጥቁር ዜጎች ከደበደባ አንስቶ ንብረታቸውን መነጠቅ ፣ማቃጠል፣ በህይወታቸውም እሰከ መቃጠል እና ስደስት የሚድረሱ ወገኖቻቸንን መግደላቸው እና በተመለከተ የተለያዩ አለማቀፍ የዜና አውታሮች ዋንኛ የመወያያ አጀንዳቸው አንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው ። ሰሞነኛውም መጠፎ አጋጣሚ ቢሆን ምን ይዞ ኣንደሚመጣ ለጊዜው መገመት ያዳግታል። ለማንኛውም እንደ አሸዋ የተበተኑት ወገኖቻቸን ወደ እናት አገራቸው በሰላም እስኪመለሱ ድረሰ ባሉበት ሰላም እንዲበዛላቸው መጸለዩ እና ደግ ደግ መመኘቱ አይከፋም።

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *