የህብር ሬዲዮ ግንቦት 28 ቀን 2008 ፕሮግራም
<…የጤናዬ ሁኔታ አሳሳቢ ነው። እስር ቤት እያለሁ በሚደረግብኝ ተጽዕኖ በጊዜው ወደ መጸዳጃ ቤት አልሄድም በዚያ ሳቢያ ውሃም ሆነ ምግብ ብዙ አትወስድም። በሁለቱም ኩላሊቴ ላይ ከፍተኛ የጠጠር ክምችት አለ።ይወጋኛል። ሂሞራይዱ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። በቀዶ ጥገና ለማውጣት እንኳ አደገኛ ደረጃ ላይ ነው ብለዋል…በእስር ቤት መደብደብ ያንን ብዙም አልቆጥረውም ያ ለኔ ቀላል ነው ሰውን አስረህ ግን የተፈጥሮ ግዴታውን እንዳይወጣ መከልከል ምን አይነት ጭካኔ ነው? …በዚያ ስቃይ ላይ እያለሁ ደሜ እላዬ ላይ እየፈሰሰ ለምርመራ ብለው ይጠሩኝ ነበር…> ሀብታሙ አያሌው በአሁን ወቅት ስላለው የጤናው ሁኔታ እንዲሁም ስለተደረገለት የገንዘብ ድጋፍ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
<…በኦሮሚያ ተማሪዎች ሰላማዊ ጥያቄ ስላነሱ የተደበደቡት፣የታሰሩት ፣የተሳደዱት ያ ሁሉ እንግልት አልበቃ ብሎ ለቀሩት ፈተናው ይራዘም ሲባል በጉልበት በራሳቸው ጊዜ እንፈትናለን ሲሉ ፈተናው ወጥቶ በግድ እንዲሰርዙት መደረጉ የሰላማዊ ትግሉ እያደገ መሄድ ማሳያ ።ትልቅ እመርታ ነው…አሁንም ፈተና ለመፈተን ያወጡት ቀን የሙስሊሙን ማህበረሰብ ፍላጎት ወደ ጎን ያደረገ የአገሪቱን ብሔራዊ በዓል የዘነጋ ነው። በሮመዳን ወር በርካታ መንፈሳዊ ተግባራት የሚፈጸምበት ሙስሊሙ ማህነረሰብ የተለያዩ ጸሎቶችን የሚያደርግበት ወቅት ነው።በዚህ የሮመዳን ፍቺ ወቅት ፈተና እፈትናለሁ ማለት አግባብ አይደለም።ይሄ በክርስቲያን ወገኖቼ በዓል ቀንም ቢሆን እቃወማለሁ።ብሄራዊ ፈተናው በዚያ ቀን ሊሰጥ አይገባም ሊራዘም ይገባል ያ ሳይሆን ግን…> አክቲቪስትና ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
የዓለማችን የክፈለ ዘመኑ ያታላቆች ታላቅ የነበረው ጥቁር አሜሪካዊው ቡጢኛው መሐመድ አሊ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ አርብ እለት በተወለደ በ74 አመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። መሃመድ አሊ እንኳን ወዳጆቹ ጠላቶቹ እና ተፎካካሪዎቹ ሳይቀሩ ልዩ ክብር ነበረው ። ታዲያ ይህ የቦክሱን ዓለም ወደተሻለ ደረጃ እንዲደርስ ያደረገው የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ መሃመድ አሊ እንዴት ይታሰባል? የዓለማቸን ታላላቅ ሰዎችስ ሰለ መሃመድ አሊ ምን ይላሉ?(ልዩ ዘገባ)
ቀነኒሳ በቀለ በኦሮሞነቱ ሳቢያ በተደረገበት ተጽዕኖ በማራቶን ብድን ውስጥ እንዳይካተት መደረጉን መግለጹ ተዘገበ ዘገባውን አካተነዋል
ሌሎችም አሉን
ዜናዎቻችን
አርበኞች ግንቦት ሰባት ወያኔ ተገዶ በድርድር ስልጣን እለቃለሁ ካለና በዚህ የታጋዮችን ሕይወት ማትረፍ ከተቻለ ድርድሩን እቀበላለሁ አለ
የወጣቱ ፖለቲከኛ ሀብታሙ አያሌው የጤንነት ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል
እነ ሀብታሙ ማክሰኞ ለዐቃቢ ሕግ ይግባኝ ለብይን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ
የእንግሊዝ መንግስት በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እስራት ዙሪያ ከ ኢሕአዲግ ጎን መሰለፉ ቤተሰቦቻቸውን ክፉኛ አሳዘነ
“ የባለሰልጣናቱ አስተያየት ለእኔ የስድብ እና ፊቴን በጥፊ የተመታሁ ያህል መሰሎ ነው የተሰማኝ” ወ/ሮ የምስራች ሃ/ማሪያም የአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት
የቀድሞው የአየር ሀይል አዛዥ ሜ/ጄ አበበ ተክለሃይማኖት ሳሞራን ጨምሮ የስርዓቱ ወታደራዊ አዛዦች ጡንቻ መፈርጠም አደገኛ መሆኑን ገለጹ
የሙስሊሙንና የኦሮሞ አክቲቪስቶችን ጥያቄ ግምት ውስጥ ሳያስገባ ትምህርት ሚኒስቴር ማትሪክን በኢድ ወቅት እፈትናለሁ ማለት አገሪቱንና ሕዝቡን ለተጨማሪ ኪሳራ በመዳረግ ሀላፊነቱን ይወስዳል ተባለ
ሱዳን የኤርትራ ሰደተኞችን በዘምቻ ክ በማሰር ወደ አገራቸው የማባረሯ እርምጃ ከፈተና ተቃውሞ እና ሰጋት ፈጠረ
ኤርትራ የጸጥታው ምክር ቤት የጫነባት ማእቀብን ለማሰቀየር በቅረቡ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በማዘጋጀት ላይ ነች
የእስራኤል መንግስት በቤተ እስራለዊያን ላይ የሚያድረገውን የዘረኝነት አመለካከቱን እንዲቀየር ፕ/ቷ ጥሪ አቀረቡ
ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል በተደረገው ጉዞ ላይ ህይወታቸውን ያጡ ከ 1500 በላይ ቤተ እስራኤላዊያኖች ታወሱ
እና ሌሎችም ዜናዎች አሉን
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ፡30 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።
https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-060516