በቅርቡ ከእስር የተፈታው የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አመራር አቶ ሃብታሙ አያሌው እስር ቤት እያለ በደረሰበት እንግልት በደረሰበት ህመም የተነሳ ለህክምናው ወጪ በሚል በዘ-ሐበሻ አዘጋጆች አስተባባሪነት በድረገጽ; በ ሕብር ራድዮ እና አዲስ ድምጽ ራዲዮ ድጋፍ የገንዘብ ማሰባሰብ ተደርጎ ነበር:: ኢትዮጵያውያን ይህን ጥሪ ከመላው ዓለም ተቀብለው $23,344 በኢንተርኔት አዋጥተው ለሃብታሙ አያሌው ጤናው እንዲመለስለት ተመኝተዋል:: ሃብታሙ የተዋጣለትን ገንዘብ ሰሞኑን ከተቀበለ በኋላ ከሕብር ራድዮ ዳይሬክተር ሃብታሙ አሰፋ ጋር ልዩ ቃለምልልስ አድርጎ ሕዝቡን አመስግኗል:: በ እስር ቤት የገጠመውን ልብ የሚነካ ሁኔታም ተናግሯል:: ያድምጡት – ሼር ያድርጉት