“ኤጲስ ቆጶስ ሆይ ለማስተማር ትጋ፣የበደለውንም … ወደ ቤ/ክን መልሰው እንጂ…”ፍትሃ ነገስት
በታምሩ ገዳ
ለሰበከተ ወንጌል መሰፋፋት እና ለሃዋሪያዊ ተልእኮ ሲባል ወደ ሰሜን አሜሪካ፣ ካናዳ፣ አወሮፓ፣ ምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ፣ አወስትራሊያ ፣ኒውዚላንድ እና የመሳሰሉት አህጉራት እና አገሮች በመጓዝ በመንፈሳዊ ርሃብ እና ጉስቁልና የሚሰቃዩ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮችን በማጸናናት እና በማበረታት የሚታወቁት አባ ወልደትንሳአኤ አያልነህ ለከፈሉት መሰዋትነት እና በመከፈል ላይ ላሉት መንፈሳዊ እና ሃዋሪያዊ አገልገሎት በወጪ አገር የምትገኘው የኢ/አ/ተ/ቤ/ክ ሰሞኑን አዲስ የመንፈሳዊ አባትነት ሹመት እና ሓላፊነት አንደሰጠቻቸው ታወቀ።
ባለፈው እሁድ እ ኤ አ ሰኔ 5/ 20 16 በሎሳንጀለስ ከተማ በምትገኘው እና ኣባ ወልደተንሳኤ አብዛኛውን ጊዜያት በክህነት እና በሰብከተ ወንጌል የሚያገለግሉባት የድንግል ማሪያም የ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የተካሄደው የቅዳሴ መረሃ ግብርን ለጥቆ የሰልጣነ ክህነቱ እና የምስራች ዜናው ለምእመናኖች በአውደ ምህረቱ ላይ የተበሰረ ሲሆን በእለቱ በ ስፍራው የነበሩ በርካታ መእመናኖችም እዲሱን የ እባ ወልድትንሳኤን ሹመት የደልዎ ወይም”አባታችን ይገባዎታል” በማለት ደሰታቸውን በእልልታ እና በጭብጨባ ገልጸዋል። ከወጣው መርሃ ግብር መረዳት እንደተቻለው በ ስላጣነ ክህነት ዋስጥ ከፈተኛ ማረግ የሆነው አባ ወልደተንሳኤ የተሰጣቸውን የ ኤጲስ ቆጶስ ማእረግን እና ሃላፊነትን በመጪው ቅዳሜ ሰኔ 18 /2016 እኤ አ በካሊፎርኒያው ፣ኦክላንድ፣ በሚደረገው ልዩ መንፈሳዊ ፕሮግራም ላይ ታላላቅ የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች እና ምእመናኖች ፊት በመቅረብ የሚሾሙ እና ተጥጨማሪ ሃላፊነቶችን የሚቀበሉ ሲሆን ከዚሁም ጋር በተያያዘ ኣባ ወልደትንሳኤ ከአለማቀፍዊ እና ሃዋሪያዊ ተልእኳቸው መልስ አብዛኛውን ጊዜያት የሚያገለግሉበት የሎሳንጀለስ ድንግል ማሪያም ቤተክርስቲያን መእመናኖች እና በርካታ የመንፈስ ልጆቻቸውም በከብረ በአሉ እና ሹመቱ ላይ ለመገኘት በኮንትራት እወቶቡሶች እና በግል መኪኖቻቸው በመጓዝ የክብረ በአሉ ታዳሚዎች እና የበረከቱም ተሳታፊዎች ለመሆን በዝግጅት ላይ መሆናቸው ታውቋል። ከዚያም በሁዋላ የደንግል ማሪያም ቤተክርስቲያን እና ምእመናኖቿ ለብጹነታቸው ልዩ “የእንኳን ደስ ያሎት እና እንኳን ደስ ያለን የምስጋና መረሃ ግብር ” ከ ባአለ ስሜቱ በሁዋላ በቀጣዩ ሳምንት ማዘጋጀቷ ተገልጿል።
ኣባ ወልደተንሳኤ ቤተክርስቲያኒቱ እና ልጆቿ በሚፈልጓቸው ጊዜያት እና ቦታዎች “ደከመኝ ፣ሰለቸኝ” ሳይሉ ፣ ግላዊ ክብር እና ሙገሳን ሳይሹ በተጠሩበት እና የመምህራን እጥረት እና ክፍተት አለ ብለው በሚያምኑባቸው የአለም ዳርቻዎች በመጓዝ ሃዋሪያዊ ተልእኳቸውን ከሚወጡ ታዋቂ የወንጌል ገበሬዎች መካከል አንዱ ሲሆኑ ቅዱስ መጽሃፍ እንደሚለው ሰጋ ለባሽ ሁሉ ሃጢያተኛ እንደ መሆኑ ሁሉ አንዳንዴ እርሳቸውን ጨምሮ ከካህናቶች በኩል ሰህተቶች ሲፈጸሙ በግንባር ቀደምነት ወጥተው የሚቃወሙ ፣የሚያወግዙ እና ይቅርታን የሚያስቀድሙ ፣በገሃዱ አለምም ቢሆን የህግ ጥሰቶች ሲኖሩ ፣ ደሃዎች እና ደካሞች ሲገፉ ዘር ቀለም ሳይለዩ ሁሉንም ወገኖችን የሚገስጹ መንፈሳዊ አባት ሰለመሆናቸው እንዲሁም ህገ ኦሪትን ከ ሕገ ወንጌል ጋር በማጣቀስ በቀልድ እና በምሳሌ መልክ የምእመናኖችን መንሰፈን እና ልቦችን በእግዜ አብሔር ቃላት የሚያረሰረሱ ታላቅ የወንጌል መምህር /ገበሬ እንደሆኑ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ብዙዎች ይመሰክሩላቸዋል።
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሃይማኖት እና ስርአት መሰረት የኤጵስ ቆጶስነት ሹመት የሚሰጠው አንድ አገልጋይ ሰለ ሃይማኖቱ፣ስለ እወቀቱ፣ስለ አኗኗሩ፣ስለ መልካም ምግባሩ በ መእመናኖች እና በጳጳስ ሲረጋገጥለት ብቻ እንደሆነ የቤተክርስቲያኒቱ ዋንኛ መተዳደሪያ የሆነው ፍተሃ ነገስት ይደነግጋል።የ አንድ ኤጵስ ቆጶስ ሃላፊነቱም ከ ብዙ በጥቂቱ “ኤጲስ ቆጶስ ሆይ ለማስተማር ትጋ።መጽሃፍትን ሁሉ ለመተርጎም ብትችል ህዝብህን ትምህርት አጥግባቸው።በብዙ ትምህርት ባለጠጎች ይሆኑ ዘንድ ከህጎችህ ብርሃን አብራላቸው።የበደለውን አውግዘህ ብትለየው በውጭ አትተወው ወደ ቤተክርስቲያን መልሰው እንጂ።የጠፋውንም ፈልግ።ስለ ሃጢያቱ ብዛት እድናለሁ ብሎ ተሰፋ የማያደረገውን በሁሉ ጠፍቶ ይቀር ዘንድ አትተወው።እንዲህም ኤጲስ ቆጶስ የሃጡን ሃጢያት ሊሸከም ይገባዋል።” ይላል።
በውጪ አገር የምትገኘው የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ ሰሞኑን ለተለያዩ ታላላቅ መንፈሳዊ አገልጋዮቿ ሹመት እና ማእረግ እንደሰጠች የታወቀ ሲሆን ለአብነት ያህል አባ ሳሙኤል ከዲንቨር ፣አባ ጽጌ ከ ሎሳንጀለስ ቅድስት ማሪያም (ስላውስን አጥቢያ)፣አባ ሳሙኢል ከካንዳ፣ አባ ወልደተንሳኤ ከሎሳንጀልስ ድንግል ማሪያም(ሜን ስትሪት አጥቢያ)፣ አባ ተሰፋሚካኤል ከብዙ በጥቂቱ ተጠቃሾች ናቸው ።ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በምእራብ አውሮፓ ሎንዶን ከተማ ወስጥ የሚኖሩ አቶ ያእቆብ አድማሱ ለዚህ ጸሃፊ እንደገለጹት “ በርካታ ታላላቅ አባቶች በእድሜ መግፋት እና በጤንነት መታወክ ምክንያት ከመደበኛ መንፈሳዊ አገልግሎታቸው መስተጓጎላቸው የግድ በመሆኑ እና የቤተክርስቲያኒቱ ሃዋሪይዊት ተልእኮም እየተበራከተ እና እየተስፋፋ በመምጣቱ ሳቢያ ተጨማሪ እና አዳዲስ አገልጋዩችን መሾም እና ክፍተቱን መሙላት ተገቢ እና ለ ነገ የማይባል ጉዳይ ነው።” በማለት አሰታያየታቸውን ሰጥተዋል።
በሎሳንጀለሰ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በድንግል ማሪያም ቤ/ክ ለበረካታ አመታተ የተገለገሉባት እና በመገልገል ላይ የሚገኙት፣ በክርስትና ሰማቸው ቤተማሪያም የተባሉ አንድ ምእመን በበኩላቸው የእባ ወልደትንሳኤ መሾምን በተመለከተ ለዚህ ጸሃፊ በሰጡት አስተያየት ” አኛ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው አባታችን የደል ዎ /ይሁን ብለናል” በማለት ደስታቸውን የገለጹ ሲሆን ሰለ አጠቃልይ የእምነቱ ተከታዮች በሰጡት የግሌ አሰተያየት ነው ባሉት ”ይህቺ በተከታዮቿ ብዛት ከሩሲያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተከታዮች በመቀጠል በአለም ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምተገኘው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን ከተመሰረተች ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ለትምህርት፣ ለፍትህ ፣ ለአንድነት እና ለመሳሰሉት አገራዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ፋና ወጊ በመሆን አስከ ዛሬው ትወልድ ድረስ ያደረሰች ታላቅ ባለውለታ የእምነት ተቋም መሆኗን በማንኛውም ወገን በኩል ለአፈታ እንኳን ሊዘነጋ አይገባም። ክብር ለሚገባው ክብር የመስጠት ባህል ሊለመድ ይገባል። የሃይማኖት አባቶችም ቢሆኑ ዘመን አመጣሹ ልዩነቶቻቸውን እና የመወጋገዝ ዘያቸውን ወደጎን በማድረግ ቤተከርስቲያኒቱ ስርእቷን እና ወጓን ጠበቃ ቀደምት አባቶች ሰለእምነታቸው ሲሉ የከፈሉትን መሰዋእትነትን ወደኋላ መልስ ብለው በመመልከት እና የቆሙበትንም ምድር በማጤን በ21ኛው ክፍለዘመን ውስጥ በሚደረጉ ማንኛውም እንቀሰቃሴዎች ላይ ግንባር ቀደም ሚና ተጫዋች እንድትሆን የማድረግ ታላቅ ሃላፊነት እንዳለባቸው መገንዘብ ይኖርባቸዋል።” በማለት የታናሽነት ምክራቸውን ሰጠተዋል።
ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።