የህብር ሬዲዮ ሰኔ 19 ቀን 2008 ፕሮግራም
<…የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ንዑስ ኮሚቴ በሁለቱም ፓርቲ አባላት ሙሉ ድጋፍ የተቀበለው ለሴኔቱ ተመርቷል ይህ ሕግ ሆኖ ሲወታ የአሜሪካና የሕወሓትን ግንኙነት ይለውጣል። ይህ እንዲሆን ግን የተደረገው ስትራቴጂ..በእርግጠኝነት የምናገረው በወልቃይት፣በቅማንት ፣ለሱዳን በተሰጠው መሬት ሳቢአ የተገደሉት ንጹሃን ቁጥር በኦሮሚያ ተቃውሞውን ተከትሎ ከተገደሉት በእጥፍ ይበልታል።ይህን ግን ተከታትሎ በኦሮሚያ እንደተደረገው የእያንዳንዱ ሟች ብቻ ሳይሆን በተለይ የአካባቢው ፖሊስም ሆነ ልዩ ሔኢል በግድያ ሲሳተፍ የገዳዩ ማንነት ጭምር ቢወታ ኖሮ ከኦሮሚአው ጋር አንድ ላይ ማቀናጀት ይቻል ነበር ግን ያ አልሆነም። በአማራ የተፈጸመውን ግድያ ተከታትሎ የዘገበው የለም። ስራ አልተሰራም ይሄ ቢሰራ ኖሮ…> ጃዋር መሐመድ የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ዳይሬክተር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
በፍሎሪዳ የኢሚግሬሽን እስር ቤት ዛሬም የሚገኙ ወገኖቻችንን እንድረስላቸው ቃለ መጠይቅ ከእስር ቤቱ ከወጣ ከአንዱ ጋር (ሙሉውን ያዳምጡት)
ሁለት ኩላሊቱን ያጣ ኢትዮጵአዊን ለመርዳት በቬጋስ የተጀመረ ወገን ለወገን ጥሪ
የአሜሪካ ፖለቲከኞችን ከማነታረክ እስከ ማፋጠጥ የሄደው ልዩ የሆነው የመሳሪያ ባለቤትነት መብትን የተቃወሙ የአሜሪካ የሕዝብ እንደራሴዎች ለሃአ አምስት ሰዓት የዘለቀ ተቃውሞና ውጤቱ ሲዳሰስ
በሕዝበ ውሳኔ ምክንያት ከአውሮፓ ሕብረት የወጣችው እንግሊዝ ከፍተኛ ተቃውሞና ድጋፍ በማስተናገድ ላይ ትገኛለች ከሁለት ሚሊዮን በላይ ዜጎች ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ጠይቀዋል ልዩ ዘገባ
ሌሎችም አሉን
ዜናዎቻችን
እስራኤል በኤርትራ ወታደራዊ ቤዝ እንደሌላት ተገለጸ፣
ጃዋር መሐመድ በሻሸመኔም ሆነ በሌሎች ቦታዎች የሚደረገው ግድያ የሕወሓት የተቀነባበረ ሕዝብን ከሕዝብ የማጋጨት ሴራ መሆኑን ገለጸ
፣የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ እውነተኛ አመራሮች አዲስ ፓርቲ አልመሰረትንም አሉ
በስማችን አይነገድ ሲሉ ተቃውመዋል
የአማራ ወጣቶች ከሕወሃት ጥቃት ራሳቸውን አደራጅተው እንዲከላከሉ ጥሪ ቀረበ
የዛምቢያ መንግስት የ19 ኢትዮጵያውአን ስደተኞችን አስከሬን የኢትዮጵያ መንግስት ካልወሰደ በአገሬ እቀብራለሁ አለ
ለኢትዮጵያ የተለገሰ 68 ሚሊዮን ኮንደም ደረጃውን ባለመጠበቁ እንዲጣል ተጠየቀ
እና ሌሎችም ዜናዎች አሉን
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ፡30 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140
https://soundcloud.com/user-437567080/hiber-radio-062616
It’s perfect time to make a few plans for the future and it’s time
to be happy. I’ve read this post and if I may just I desire to counsel you some attention-grabbing issues or suggestions.
Perhaps you could write subsequent articles regarding
this article. I want to learn even more things approximately it!